በኒዠር ዴልታ የነዳጅ ዘይት እጣ ፈንታ
ቅዳሜ፣ ኅዳር 6 2018
ከጎርጎሮሳዊው 1950ዎቹ አንስቶ ፣ ከናይጀሪያውከኒዠር ዴልታ ነዳጅ ዘይት እየወጣ ቢሆንም የተፈጥሮ ሀብቱ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ያበለፀገ አይመስልም።ይልቁንም የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ መርሀ ግብር በጎርጎሮሳዊው 2011 ዓ.ም. ያደረገው ግምገማ የነዳጅ ማውጣት ኦኒዠር ዴልታ የሚገኘውን ጎኒላንድን ምን ያህል እንደበከለው ግልጽ አድርጓል። የናይጄሪያ ፌዴራል መንግሥትም በዚህ ሰበብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።
በኦጎኒላንድ በነዳጅ መፍሰስ ምክንያት የሚደርሰውን የአካባቢ ብክለት ለመፍታት የሃይድሮካርቦን ብክለት ማገገሚያ ፕሮጀክት (HYPREP) ጀምሯል። የተወሰነ እፎይታ ቢኖርም፣ የጽዳት ሂደቱ አዝጋሚ ነው፣ ዋነኛ ባለድርሻ አካላት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ አለመስማማታቸው ግን ቀጥሏል። አንዳንድ የወንዝ ዳርቻ ማህበረሰቦች፣ የማዕበል ጅረቶች እና የቦዶ ዌስት የባህር ዳርቻዎች በከፍተኛ ሁኔታ የተበከሉ ናቸው። የውሃ ፍሰቶችን ለመቆጣጠር እና ካርቦን ለማከማቸት አስፈላጊ የሆኑት የማንግሩቭ እፅዋት ወድመዋል። የተለያዩ ማህበረሰቦች የሚገኙባቸው የውሃ አካላት የዓሣን ቁጥር በሚቀንሱ ሃይድሮካርቦኖች ተበክለዋል።
ለብዙ ማህበረሰቦች ዋነኛ የመጠጥ ውሃ ምንጭ የሆነው የከርሰ ምድር ውሃ፣ አሁንም በቤንዚን መሰል መርዛማ ንጥረ ነገሮች በጣም ተበክሏል። በዚህም ምክንያት፣ የተጎዱ እርሻዎች አነስተኛ ወይም መበላት የማይችል የሰብል ምርት ይሰጣሉ። በአቅራቢያው የሚገኘው የኦጎኒላንድ ዋና ከተማ ቦሪ ፣ከቀድሞው አሁን ሕይወት ዘርቷል። ንግዶችና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እየተስፋፉ ነው። በቅርቡ ወደ 100 የሚጠጉ የኦጎኒ ወጣቶች በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም እና በአለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም (GEF) የተጀመረውን የሶስት ወራት የማጠናከሪያ ስልጠና ፕሮግራም አጠናቀዋል። ከፀሐይ የሚገኝ ኃይል እንዴት እንደሚገጠም፣ የጥገና ስርዓቶች እና የንግድ ሞዴሎች ተምረዋል።
ነገር ግን እንደዚህ ያሉ እድሎች በጣም ጥቂት ናቸው። DW በተለያዩየኒጀር ዴልታማህበረሰቦች ውስጥ ካሉ ወጣት ኦጎኒዎችን አነጋግሯል፤ እነዚህም ከዚህ ቀደም የወደፊት ተስፋቸው ጠፍቶ ነበር ። ከጎርጎሮሳዊው 1993 ወዲህ የተቋረጠው የኦጎኒላንድ የነዳጅ ቁፋሮ እንደገና እንዳይጀመር ብዙዎች ፍርሀት አላቸው። የ27 ዓመቷ ወጣት ሥራ ፈጣሪ ጎድስጊፍት ስቴላ በደቡባዊ ኮኖ የቡዌ ማህበረሰብ አባል ለዶቼቬለ እንደተናገረችው የንግድ ተስፋዋ ቀንሷል። የአካባቢው ወጣቶች የሚገኙበት ሁኔታ ያሳስባታል። እርስዋ እንደምትለው በአካባቢው ለወጣቶቹ ምንም ሥራ የለም ። ይህ ደግሞ ማህበራዊ ዝቅጠትን ያበረታታል ፤የአካባቢ ብክለት የገበሬዎችን እና ዓሣ አጥማጆችን መተዳደሪያቸውን ዘርፎባቸዋል። በዚህ የተነሳም ወደ ቦሪ እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል።እርስዋ እንደምትለው በአካባቢው ሰዎች በረሀብ እየሞቱ ነው። በሕይወት ያሉት ደግሞ ሕይወታቸውን ለማቆየት ዘረፋን አማራጭ አድርገውታል።
«ነገሮች በትንሹ እንኳን አልተለወጡም ። ሌሎች ግን ሳያውቁ ሰዎች በረሀብ እየሞቱ ነው። ይህ አሁንም እየደረሰ ነው። ሰዎች አሁን ኑሮን ለማሸነፍ በጠራራ ፀሐይ ሳይቀር ዘረፋ ያካሂዳሉ። ሰርተው ገንዘብ ማግኘት ሚችሉበት እድል ካለ፣ የተሻለ እቅድ ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁ። ግን ለጊዜው፣ የኦጎኒ ሰዎች ምንም እቅድ የላቸውም። ሁሉም በመሰላቸው ይሯሯጣሉ። መሬታችን በሙሉ ቢጸዳ እና ወደ እርሻ ብንመለስ ኖሮ ነገሮች እንደዚህ አይሆኑም" የቢኤም-ጓራ ማህበረሰብ አባል የ36 ዓመቱ የኤሌክትሪክ ቴክኒሻን ጆኤል ይጋሌ የነዳጅ ቁፋሮ እንደገና መጀመር የለበትም ባይ ናቸው። «እኔ እንኳን እንዲጀመር አልፈልግም። ምክንያቱም እኔ እስከማውቀው ድረስ በኦጎኒ የመብት ረቂቅ ሕግ ውስጥ ሊፈቱ የሚገቡ መሠረታዊ ነገሮች አልተስተካከሉም። እነዚያን ጉዳዮች አላስተናገዱም፣ እነዚያን ጉዳዮች አላስተናገዱም። ታዲያ እንዴት እንደገና ይመጣሉ? ይህ የኦጎኒ ዘይት በእጁ ብዙ ደም አለው። እርስዎ እኔን ተረድተውኝ ከሆነ አላውቅም ። ይህ የኦጎኒ ዘይት ብዙ ደም አለው። ሕዝባችን ሞቷል፣ ብዙ ሰዎች፣ የኦጎኒዎች ሕይወት ብቻ አይደለም የጠፋው።በተቃውሞው ወቅት ከ4,000 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ታውቃላችሁ፣ ስለዚህ በዚህ ጊዜ የፌዴራል መንግሥት በመጀመሪያ የራሱን ድርሻ መወጣት አለበት።እንደ እውነቱ ከሆነ፣ አንዳንድ መስፈርቶች አሉን፣ ኦጎኒዎች የመብቶች ረቂቅ ሕግን ማስገባት ነበረባቸው፣ ስለዚህ እነዚያን ጉዳዮች መከታተል አለባቸው ። ኦጎኒዎች መብቶችን በሚመለከተው ረቂቅ ሕግ እንዲካተቱ ያቀረቧቸው መስፈርቶች አሉ። እነዚህን ጉዳዮች በቅድሚያ መመልከት አለባቸው።»
በነሐሴ 1990 የፀደቀው የኦጎኒ መብቶች ሕግ በኦጎኒላንድ ውስጥ የበለጠ ራስን በራስ የማስተዳደር እና ሀብቶችን የመቆጣጠር ኃላፊነትን ይጠይቃል። ይጋል እንደሚሉት ይህ የነዳጅ ፍለጋ ቁፋሮ አሳዛኝ ትዝታዎችን እንደሚመልስ ጠቁመዋል።"ለእኔ በጣም ከባድ ነው፣ ስራ የለም፣ ድህነት ያስጨንቀኛል፣ ከየትኛውም ቦታ የሚመጣ እርዳታ የለም፣ መሬታችንና ውሃችን ተበክሏል፣ በወንዙ ውስጥ ዓሣ የለም" ይላሉ ይጋል።
ሆኖም ታዋቂው ልምድ ያለው የኦጎኒ መገናኛ ብዙሀን ባለሞያ ባሜኔ ታኔም ለDW እንደተናገረው አብዛኛዎቹ የኦጎኒ ነዋሪዎች ደህንነቱ በተጠበቀ እና በኃላፊነት ከተከናወኑየነዳጅ ፍለጋ እንዲካሄድ ይፈልጋሉ። እናም ይህ የሚደረግ ከሆነ ተጨባጭ ጥቅሞችም አሉ። ታኔምየናይጄሪያ መንግስት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ምክንያታዊ የሆነ ጥንቃቄ እንዳሳየ ተናግሯል። «የኦጎኒ ህዝብን የሚያገናኘው ዋና መንገድ፣ የምሥራቅ-ምዕራብ መንገድ፣ አሁን እንደገና በፍጥነት እየተገነባ ነው። ህዝቡ በዚህ ደስተኛ ነው። ነገር ግን ብዙ መደረግ አለበት። ሃይፕሪፕ የተባለው ድርጅት ደረጃውን የጠበቀ መደበኛ ሆስፒታል እየገነባ ነው። የውሃ ፕሮጀክት በከፍተኛ ደረጃ ዝግጅት እየተደረገበትና እየተሰራ ነው። ይህን ማህበረሰቦቻችን የሚያዩት ነው። ይህም አስደናቂ ነው"
በብዙ አጋጣሚዎች ግንባታዎችና እና የመሠረተ ልማት ጥገና ጊዜ ይወስዳል። እ.ኤ.አ. በ2011፣ የተባበሩት መንግስታት በነዳጅ የበለፀገውን የኒጀር ዴልታን ከብክለት ለማጽዳት 30 ዓመታት እንደሚወስድ ገምቷል። ከብዙ የተተዉ ወይም ችላ የተባሉ የነዳጅ ተቋማት ጋር፣ ወደ መኖሪያ አካባቢዎች የሚፈስ ድፍድፍ ዘይት አሁንም አስጊ ነው፣ እና የነዳጅ ዘይት ሌቦች በሕገ ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ነው። ሌሎችም ለዚህ ጥፋት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ አልጠፉም። እነዚህም ይህም አዲስ ፍሳሽ እና አዲስ ብክለት ማስከተላቸው አልቀረም። ያም ሆኖ ካና የሚገኘው የአካባቢ መንግሥት የነዳጅ ቁፋሮ እንዲጀመር ያለውን ድጋፍ ገልጸዋል። በኦጎኒ ህዝብ እና በፌዴራል መንግስት መካከል ሙሉ ስምምነት ሊኖር እንደሚገባም አሳስበዋል።
ቤሎ መሐመድ/ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ