1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ናይጄሪያ ፤“የክርስቲያን ዘር ማጥፋት” ወይስ የትርክት ቀውስ?

ፀሀይ ጫኔ
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 29 2018

በናይጄሪያ ክርስቲያኖች ላይ «የዘር ማጥፋት» ዘመቻ እየተካሄደ ነው መባሉ ሞቅ ያለ ክርክር አስነስቷል፣ ተንታኞች እንዲህ ያሉት ትርክቶች የሀገሪቱን የሰላም ግንባታ ጥረቶችን ሊያዳክሙ እና መለያየትንና አለመተማመንን ሊያባብስ ይችላሉ ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። ትራምፕ ግን አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ትወስዳለች ብለው እያስፈራሩ ነው።

በናይጄሪያ የሚገኙ የካቶሊክ መነኮሳት
በናይጄሪያ የሚገኙ የካቶሊክ መነኮሳት ለሰላምና ለደህንነት ሲጸልዩ በ 2020 ምስል፦ KOLA SULAIMON/AFP

ናይጄሪያ ፤“የክርስቲያን ዘር ማጥፋት” ወይስ የትርክት ቀውስ?

This browser does not support the audio element.


በጥቅምት ወር የአሜሪካ ሴናተር ቴድ ክሩዝ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው  X ላይ የናይጄሪያ ባለስልጣናት "የእስልምና አክራሪዎች በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙትን የጅምላ ግድያ ችላ እያሉ ወይም እየፈቀዱ  ነው" ሲሉ ጽፈዋል። ባለፈው ወር ክሩዝ  በክርስቲያኖች ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ናይጄሪያ ለይ ማዕቀብ ለመጣል ረቂቅ ህግ አቅርበው ነበር።በወቅቱ የማስታወቂያ  እና የብሔራዊ አቅጣጫ ሚኒስትር መሐመድ ኢድሪስ ናይጄሪያ የደህንነት ችግሮች እንዳሉባት አምነዋል። ነገር ግን "ሆን ተብሎ በክርስቲያኖች ላይ የሚሰነዘር ስልታዊ ጥቃት ተብሎ መገለፁ የተሳሳተ እና ጎጂ ነው ብለዋል።

በተለይም በናይጄሪያ በአብዛኛው ሙስሊም በሆነበት ሰሜናዊ ክፍል ያለው ደህንነት ለዓመታት እየተባባሰ መጥቷል። ቦላ ቲኑሁ ፕሬዝዳንት ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ ወደ 10,000 የሚጠጉ ሰዎች ተገድለዋል በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ታፍነዋል። ይህ ጥቃት እስከ 3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል።በሰሜን-ማዕከላዊ ክልል የሚገኙት ቤኑዌ እና ፕላቱ በጣም የተጎዱ ቦታዎች ናቸው።በነዚህ ቦታዎች  የታጠቁ ቡድኖች ሰዎችን ገድለዋል። አፍነውም ወስደዋል። ሕንፃዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ክሊኒኮችን እና የአምልኮ ቦታዎችንም አወድመዋል።
ተንታኞች እና በሕይወት የተረፉ ሰዎች እንደሚሉት የጥቃቱ መነሻዎች የመሬት አለመግባባቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ድህነት እና ደካማ አስተዳደር እንዲሁም ሃይማኖት ነው።

በናይጄሪያ፡ ገበሬዎች መካከል ያለው ክፍተት

ናይጄሪያ በክልሎች ውስጥ የደህንነት ተግዳሮቶች እያጋጠሟት ነው። በሰሜን ምስራቅ የቦኮ ሃራም ጥቃት እየተባባሰ ነው። አክራሪ ታጣቂ ቡድኑ በ2002 ዓ/ም ከተመሰረተ ጀምሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል። በ2014 ዓ/ም  ቡድኑ በናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት ከ250 በላይ ልጃገረዶችን ከትምህርት ቤት አፍኖ ወስዶ ነበር።የወንጀል ቡድኖች እና አጋቾች በሰሜን ምዕራብ አካባቢ ይንቀሳቀሳሉ። ብዙውን ጊዜ በገጠር፣ በቂ አገልግሎት በማያገኙ ማህበረሰቦች ውስጥ ያሉ ሰዎችን ዒላማ ያደርጋሉ።እንደ ቤኑ፣ ፕላቱ፣ ናሳራሳ እና ደቡባዊ ካዱና ያሉ የናይጄሪያ ግዛቶችን ጨምሮ፣ በማህበረሰብ እና በአርብቶ አደር ጥቃት ብዙ ሰዎች ተገድለዋል።በሐምሌ ወር፣ አጥቂዎች በቤኑዌ የምትገኘውን የልዋታ የአርሶ አደሮች መንደር በመውረር ቢያንስ 160 ሰዎችን ገድለዋል።

በ2022 በናይጄሪያ ደቡብ ምዕራብ ኦንዶ ግዛት በሚገኘው የቅዱስ ፍራንሲስ ዛቪየር ቤተክርስቲያን በተፈጸመው ጥቃት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።ምስል፦ Rahaman A Yusuf/AP/picture alliance

ለም በሆነው የናይጄሪያ ክልል በገበሬዎች እና በአርብቶ አደሮች መካከል ቀውሱ እየጠነከረ እንዲመጣ አድርጓል። በአካባቢው በአብዛኛው ክርስቲያን ገበሬዎች እና ሙስሊም የፉላኒ አርቢዎች ረጅም የውጥረት እና የግጭት ታሪክ አላቸው።
በሁለቱም ወገኖች የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና የበቀል እርምጃዎች ከአስርተ ዓመታት በፊት የተከሰቱ ሲሆን ገዳይ ሆነዋል።የክርስቲያን ገበሬ ማህበረሰቦች ጥቃቱን ችላ በማለት እና እውቅና ባለመስጠት መንግስትን ይከሳሉ።በአቡጃ የሚገኘው የኩካህ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አባ አታ ባርኪንዶ፣ "የክርስቲያን የዘር ማጥፋት" ትርክት መንግስት ዜጎቹን ለመጠበቅ ባለመቻሉ የመጣ እንደሆነ ያምናሉ።
«በናይጄሪያ የተከሰተውን ነገር ክርክር እንዲሸፍነው አልፈልግም፤ ይህ የአስተሳሰብ ጉዳይ ነው»  ብለዋል ባርኪንዶ።እነዚህ ነገሮች  ታሪካዊ ናቸውም ይላሉ። ግን ሆን ተብሎ በመንግስት የተፈፀመ ነው ብለው አያምኑም። 
 «እነዚህ ነገሮች  ታሪካዊ ናቸው።በእኔ አስተያየት፣ የናይጄሪያ መንግሥት ክርስቲያኖችን የመግደል ወይም የመንግሥት ተዋናዮችን ሆን ብሎ የማሰማራት ዓላማ ያለው አይመስለኝም።በእርግጥ እንደዚያ አይመስለኝም። ሰዎች ለመግለጽ የሚሞክሩት መንግሥት ዜጎቹን ለመጠበቅ አለመቻሉን እንደሆነ አምናለሁ፤ የተገደሉት ወይም ዒላማ የሆኑት አብዛኛዎቹ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ደግሞ፤ ያን እይታ እንዲቀጣጠል ያደርጋል።»ብለዋል።

ከጥቃቱ የተረፉት ሰዎች ምን ይላሉ?

በግንቦት ወር ጸጥ ባለ እሁድ ምሽት፣ ኮምፎርት ኢስፋነስ፤ በፕላቱ ግዛት ቦኮስ አካባቢ በሚገኝ ትንሽ ኩሽናዋ ውስጥ እራት እየሰራች ሳለ፤ በውጭ በኩል በፍጥነት የሚሮጥ ሰው ድምጽ ሰማች። ባለቤቷ ዳናሊ ነበር። ወደ ግቢያቸው ሮጦ ሲገባ እያለቀሰና አቧራ ተሸፍኖ ነበር። የታጠቁ ሰዎች ወደ አካባቢያቸው መቅረባቸውን ሰምቶ ነበር። እጇን ይዞ ልጆቹን ወደ ደህና ቦታ ይዛ እንድትሄድ ነገራት። ከዚያም፤ ስትል ለDW  የሆነውን ታብራራለች።
«ከሸሽን በኋላ ከታናሽ ወንድሙ ጋር ቤት ቆየ። [ታጣቂዎች] ቤት ሲያገኛቸው ገደሏቸው። ቤቶቻችን ተቃጥለዋል፤ አሁን ደግሞ ለልጆቻችን ምግብና መጠለያ አጥተን እየተሰቃየን ነው። አሁን የሚበሉት ነገር የለም።ትምህርት የለም። ስራ የለም። ምንም ነገር የለም።»በማለት ገልፃለች።

ካሪማቱ አሚኑም በዚህ ቀውስ ባለቤቷን አጥታለች። በታህሳስ ወር መጨረሻ ሐሙስ ጠዋትላይ እርሻ ቦታቸው ላይ ስታገኘው፤በአካባቢው በሚገኝ ገበያ  ለምሽቱ የሚሆን ጥቂት ነገሮችን እንድትገዛ ጠየቃት።ካማሪቱ ለDW እንደለፀችው ፤ያኔ ነበር ለመጨረሻ ጊዜ ባለቤቷን በህይወት ያየችው። ጥቃቱ የአንድ ቡድን ብቻ አይለም ትላለች።«ይህ የአንድ ቡድን ብቻ ​​አይደለም.ዛሬ የፉላኒ ቤቶች ሲቃጠሉ፣ ነገ የክርስቲያን ማህበረሰብ ቤቶችም ይቃጠላሉ። ሁለቱም ወገኖች ሰዎችን እና ቤቶችን እያጡ ነው።»ስትል ተናግራለች።

የክርስቲያን-ሙስሊም አለመተማመን

በክልሉ ውስጥ ላሉ ብዙ ማህበረሰቦች፣ ጥቃቱ አርብቶ አደሮች እና በአርሶ አደሮች  መካከል ከሚደረግ ግጭት ያለፈ ነው። ጉዳዩን የሚያዩት ከመሬታቸው ለማባረር የሚደረገው ዘመቻ አካል አድርገው ነው።ይህም በፉላኒ ጎሳ አባላትላይ ያላቸውን እምነት ማጣት ያሳያል።ይህም በሰሜን እና በመካከለኛው ናይጄሪያ ውስጥ ከተስፋፋው እና የአካባቢውን መዋቅሮች እና የፖለቲካ ስርዓቶችን ካናወጠው ታዋቂው የእስልምና አክራሪነት ዘመን ጀምሮ ነው።ተንታኞች እንደሚሉት፣ ይህ ጥልቅ  ታሪክ በክልሉ ውስጥ ያለውን ዘመናዊ ግጭት መቀርጹን ቀጥሏል። ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ያልተሸነፉ ብዙ ቡድኖች የዛሬውን ቀውስ እንደ መሬት ወይም ሀብት ክርክር ብቻ ሳይሆን የክርስቲያን-ሙስሊም አለመተማመንን የሚያባብስ  የቀጠለ ታሪካዊ ጥቃት አድርገው ይተረጉሙታል። በሰኔ ወር፣ በቤኑ ግዛት የቲቭ ጎሳ መሪ የሆኑት ጄምስ ኦርቴሴ ሎሩዛ  አያትሴ የአርሶአደር -አርብቶ አደርን ትርክት ውድቅ አድርገውታል። «እዚህ ቤኑዌ ውስጥ የምጋፈጠው በአሸባሪዎች እና በሽፍቶች የተሰላ፣ በሚገባ የታቀደ፣ ሙሉ በሙሉ የተስፋፋ የዘር ማጥፋት  እና የመሬት ወረራ ዘመቻ ነው።» ብለዋል።

በ2010 በናይጄሪያ ጆስ ውስጥ በክርስቲያኖችና በሙስሊሞች መካከል በተነሳ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋልምስል፦ AP

አስፈላጊ ውይይት?

በፓን አፍሪካ የመልካም አስተዳደር ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ሳሙኤል ማሊክ፣ በተለይም በሰሜን-ማዕከላዊ ናይጄሪያ ክፍሎች የሚፈጸሙ አንዳንድ ጥቃቶች ሃይማኖታዊ ድምፀት ሊኖራቸው እንደሚችሉ ያምናሉ። ነገር ግን "ክርስቲያኖችን ለማጥፋት በመንግስት የሚመራ ወይም የተቀናጀ ዘመቻ መኖሩን የሚያሳይ ምንም ዓይነት ተዓማኒነት ያለው ማስረጃ የለም፣። ይላሉ። በአንፃሩ እሳቸው እንደሚሉት በናይጄሪያ የሚታየው የጸጥታ ችግር  የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ነው።«የአስተዳደር ውድቀቶች፣ ሙስና፣ ድህነት፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚፈጠሩ የኑሮ ጫናዎች፣ ዓመፅ እና የተደራጀ ወንጀል፣ እና ይህ እንደ ዘር ማጥፋት ወንጀል መግለጹ እነዚህን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ያቃልላል።»
የ«ክርስቲያኖች የዘር ማጥፋት» ዘመቻ ያሉ ትርክቶች በአገሪቱ ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን የሚያባብሱትን ዋና ዋና መነሻዎች ይደብቃል ሲሉም ይገልፃሉ።በሃይማኖቶች መካከል ያለውን የእርስ በርስ ግጭት እና በማህበረሰብ ደረጃ የሚደረጉ የሰላም ግንባታ ጥረቶችንም ሊያዳክሙ ይችላሉ የሚል ስጋትም አላቸው።

በዮላ ናይጄሪያ የደረሰ የቦኩሃራም የሽብር ጥቃትን ሰዎች ሲመለከቱ።ምስል፦ Reuters/Stringer

በአብዛኛው በተወሰኑ የምዕራባውያን ተሟጋችነት እና የሃይማኖት ቡድኖች የሚቀርበው 'የዘር ማጥፋት' ትርክት የተለዬ አንድምታ አለው። «የውጭ መንግስታት፣ በተለይም ዩናይትድ ስቴትስ፣ ገንቢ እና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ ከማድረግ ይልቅ በናይጄሪያ ላይ ቅጣት እና  አቋም በመያዝ  ጫና ያሳድራል።» ብለዋል።

«ከዚህም በላይ፣ የናይጄሪያን መንግሥት በሃይማኖታዊ ግድያ ተባባሪ አድርጎ በመግለጽ ዓለም አቀፍ ተቀባይነትን ያሳጣል። ይህም የጸጥታ ችግርን ለመቅረፍ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ለማግኘት አስቸጋሪ ወይም የማይቻል ያደርገዋል።»ብለዋል።
አታህ፤ ትረካው መለያየትንና አለመተማመንን ሊያባብስ እንደሚችል ይስማማሉ።ነገር ግን ስለ ጥቃቱ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ለውይይት ሊረዳ ይችላል ብለዋል፡- «ከዘር ማጥፋት ክስ ባሻገር ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው። በአጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ ስላለው ደህንነት እና አለመረጋጋት ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልገን በጣም አስፈላጊ ጉዳዮችን እያስነሳ ነው።»የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

ፀሐይ ጫኔ
እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW