በአለም አንጋፋዉ የአየር ማረፍያ ለጡረታ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 25 2001ማስታወቂያ
የዛሪ ሰማንያ አመት ግድም ታሪካዊ አከፋፈት እንደተደረገለት ሁሉ የአየር ማረፍያዉ ታሪካዊ መዝግያ ተደርጎለት ለጡረታ በቅቶአል። በዛሪዉ የባህል መድረካችን ስለ በርሊኑ ቴምፕሎሆፍ የአዉሮፕላን ማረፍያ በጥቂቱ የምንዳስሰዉ ርእሳችን ይሆናል። ሌላዉ የበጋዉ ወራት አልፎ ዝናብ የበዛበት ጭጋጋማዉ የክረምቱ መንደረሪያ የሆነዉ ወራት ሲገባ በምዕራባዉያኑ ዘንድ የሚከበረዉ ሃለዊን የተሰኘዉ ጥንታዊ የሆነ ባህላዊ በአል ባለፈዉ አርብ ምሽት ተከብሮአል። የሃለዊን በአል ምንን አስመልክቶ ይከበራል? በአሉስ እንዴት ይከበራል? ጀርመናዉያንስ እንዴት ያከብሩታል? ለሚለዉ በዛሪዉ የባህል መድረካችን የሚዳስሰዉ ነዉ። ሌላዉ ባለፈዉ ቅዳሜ በዚህ በጀርመን አለ ሃይሊገን እየተባለ ስለሚጠራዉ የካቶሊካዉያን የቅዱሳን መታሰብያ ቀን ሌላዉ ዛሪ በጥቂቱ የምናየዉ ርእሳችን ነዉ ያድምጡ