በአሙሩ ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያአቸው መመለስ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 27 2016
በአሙሩ ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያአቸው መመለስ
በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ውስጥ ባለፉት 3 ዓመታት በነበረው ጸጥታ ችግር ከ45ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው ቆይተዋል፡፡ ከወረዳው 16 ከሚደርሱ ቀበሌዎች ተፈናቅለው ኦቦራ እና አጋምሳ የተባሉ ከተማ ላይ የነበሩ ሰዎች በሙሉ ወደየቤታቸው መመለሳቸው የወረዳው አደጋ ስጋት ስራ አመራር/ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጅረኛ ረጋሳ አስታውቋል፡፡ ያነጋርናቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው አጋምሳ በሚባል ከተማየሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎች የተወሰኑት አሁንም አለመመሳቸውን ገልጸው በርካታ ቁጥር ያለው ሰው ደግሞ ወደ ገጠሩ አካባቢመመለሱን ተናግረዋል፡፡ከምስራቅ ወለጋ ዞን ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች እየተመለሱ ነው
በወረዳው 45ሺ 9 መቶ 15 ሰዎች ከ16 ቀበሌዎች ተፈናቅለው ቆይቷል
በግጭት ከተጎዱ የሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አንዱ በሆነው አሙሩወረዳ ባለፉት ዓመታት 45ሺ 915 ሰዎች ተፈናቅለው በሁለት ከተሞች ውስጥ ተጠልለው እንደነበሩ የወረዳው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ጽ/ ቤት ትኃላፊ አቶ ጅረኛ ረጋሳ ከ16 ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ሰዎች በወረዳው ከተማ ኦቦራ እና አጋምሳ የተባሉ ከተሞች ውስጥከ2 ዓመት በላይ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡በሁለቱም ከተሞችላይ የነበሩ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀድሞ ቤታቸውመመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡
‹‹ አሁንም ሰዎች ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡ ባጠቃላይ 45ሺ 9 መቶ 15 ሰው የተፈናቀሉ አሁን ተመልሷል፡፡ምሥራቅ ወለጋ፤ ተፈናቃዮች እርቅና ርዳታው ወደ ግብርና ስራየገቡም አሉ ነገር ግን ለሰው ልጅ መሰረታዊ የሆኑ ቤትና ሌሎች ነገሮች የተሟሉ አይሉም የወደሙ ቤቶች አሉ፡፡ ሰብአዊ ድጋፍ አልተቋረጠም፡፡ በየወሩ እየመጣላቸው ነው ድጋፍ ከሰው ቁጥርጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ብዙ ሰዎች ቅሬታ እያቀረቡ ነው፡፡
የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸው
በአሙሩ ወረዳ ኦቦራ ከተማ ውስጥ ለሶስት ዓመታት መኖራቸውን የነገሩን አንድ ነዋሪ ምግርና ጆጅ ከተባሉአካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸውንገልጸዋል፡፡ በዚህ አካባቢ የተመለሱ ሰዎች ወደ ግብርና ስራመግባታቸውን ተናግረዋል፡፡የጸጥታ ስጋት የሚስተዋልባቸው አካባቢዎችና ቤታቸው የወደመባቸው ሰዎች ደግሞ በከተማው ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡በወረዳው አጋምሳ ከተማ የሚገኙ ሌላው ነዋሪም በርካታቁጥር ያላቸው ተፈነቅለው የነበሩ ሰዎች ወደ ቀድሞ ቤታቸው መመለሳቸው በመጥቀስ የተፈናቀሉ ዜጎች ሙሉ በሙሉአለመመሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ነዋሪው በቂ የሰብአዊ ድጋፍ አለመኖሩንና የመድኃኒት እጥረት እንዳለ በተደጋጋሚአንስተዋል፡፡በቤኒሻንጉል ወደ መኖርያቸዉ እየተመለሱ የሚገኙት ተፈናቃዮች
በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳን ጨምሮ አቤ ደንጎሮና ጃርዳጋ ጃርቴ የተባሉ ወረዳዎች በነበሩ የጸጥታ ችግሮች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለው ቆይተዋል፡፡ የአሙሩ አጎራባች በሆነው የምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳምበመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ 50ሺ የሚጠጉ ዜጎች ወደቤታቸው መመለሳቸውን የዞኑ አደጋ ስጋት ስራአመራር ጽህፈት ቤት ገልጸዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ