1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአማራ ክልል በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረግ ዝርፊያ መጨመር

ኢሳያስ ገላው
ሐሙስ፣ መጋቢት 11 2017

በመሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ የሚፈፀም ስርቆት እየተባባሰ መምጣቱና በሀገር እድገት ላይ የሚያሳድረዉ ተፅኖ ከፍተኛ መሆኑ ተነገረ። በአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን በመብራት ቴሌኮም ዉሀ እና የባብር መሰረተ ልማት ላይ የሚደረግ ዝርፊያ በየጊዜዉ እየጨመረ ነዉ ያሉ አስተያየት ሰጭዎች አጥፊዎችን የመከታተል ስራ መሰራት አለበት ብለዋል።

Äthiopien Infrastruktur Diebstahl
ምስል፦ Esayas Gelawe/DW

መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረግ ዝርፊያ በአማራ ክልል

This browser does not support the audio element.

በመሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ የሚፈፀም ስርቆት እየተባባሰ መምጣቱና በሀገር እድገት ላይ የሚያሳድረዉ ተፅኖ ከፍተኛ መሆኑ ተነገረ። በአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን በመብራት ቴሌኮም ዉሀ እና የባብር መሰረተ ልማት ላይ የሚደረግ ዝርፊያ በየጊዜዉ እየጨመረ ነዉ ያሉ አስተያየት ሰጭዎች አጥፊዎችን የመከታተል ስራ መሰራት አለበት ብለዋል። በአካባቢዉ በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘዉ ጦርነት ለዝርፊዉ የራሱ አስተዋፅኦ እንዳለዉ የገለፁ የህግ ሙያተኛ በመሰረተ ልማት ዝርፊያ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን ህጉ በአግባቡ ስለማይቀጣ ስርቆቱ ተባብሶል ብለዋል። 

በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ እየደረሰ ያለዉ ስርቆት በምስራቅ አማራ እየጨመረ መጥቷል

በአማራ ክልል በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረግ ዝርፊያ መጨመር

በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርስ ዝርፊያ በአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን ከዕለት ዕለት እየጨመረ መምጣቱን የአካባቢዉ ኖሪዎች ይናገራሉ በተለይም በመብራት ቴሌኮም ዉሀና የባቡር ትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርስ ዝርፊያየማህበረሰቡን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚጎዳ ነዉ ይላሉ። <<በጣም የሚያሳዝን ነዉ ጤና መብራት መንገድና ቴሌኮም ላይ መሰረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ዝርፊያዎች በቀጥታ ማህበረሰብ ላይ ጫና አላቸዉ። 

በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ሰላምና ደህንነት  ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ መንግስቱ አራጋዉ ቡባቡርና ዉሀ መሰረተ ልማት ላይ እየተደረገ ያለዉ ዝርፊያ መጨመሩን ገልፀዉ በጥልቅ ጉድጓድ ዉሀ ቁፋሮ ሙብራትና ቴሌኮም መሰረተ ልማት ዘርፈዉ እጂ ከፈንጂ የተያዙ እንዳሉ ሁሉ የጠፉም አሉ ይላሉ። የባቡር መገጣጠሚያ ብለኖችን አርልፎ ተርፎም አሁን ለማህበረሰባችን መንግስት በብዙ ሚልየን ብር አዉጥቶ የንፁህ መጠጥ ዉሀ እንዲገባላቸዉ ዉሀ በሌለበት የገጠሩ ቀበሌያችን አካባቢ እነዛን በስራ ላይ ያሉትን ሌቦች እየቆረጡ እያመጡ በኪሎ ለመሸጥ ቁራሊዮ ለሚሰሩ ተደብቀዉ ሲሸጡ ባለን መረጃና ክትትልበተለያየ ጊዜ እጂ ከፈንጂ የያዝናቸዉ አሉ በባዶ ቤትም ጥለዉ የጠፉ አሉ። 

ስርቆት፣ ዘረፋ፣ እገታና ሥርዓተ አልበኝነት በትግራይ

የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች መዘረፍ በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ተፅኖ አድርሶል

በኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምስራቅ ሪጂን የፊክስድ ኔትወርክ ክፍል ኃላፊየሆኑት አቶ ቀለም ታረቀኝ በኢንተርኔት መሰረተ ልማት ላይ የሚደርስ ዝርፊያበተጠቃሚዉ ላይ የጥራት ችግር እያመጣ መሆኑን ገልፀዉ አሁን ላይ ዝርፊያው ወደ ኃይል ሳጥኖች እና ሌሎች ቁሳቁሶች ላይ ነዉ ይላሉ። አብዘሀኛዉ የኢንተርኔት አገልግሎት ኮፐርና የፋይበር ሚድያዎችን ይጠቀማል ስለዚህ በዋናነት የደምበኞች አገልግሎት የሚሰጡ የኮፐር ኬብሎች እየሰረቁ ይጠቀሙበታል ደሴ ከተማ ቢያንስ ከ3000 እስከ4000  ደንበኞችን ማስጠቀም የሚችል የኮፐር ኬብል ሰርቀዉታል በዚህ አንድ አመት ዉስጥ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች በዉጭ ምንዛሬ ነዉ የሚገዙት በጣም ትልቅ ተፅኖ አላቸዉ አሁን ላይ ከኩፐርና የተለያዮ ነገሮች አልፈዉ ሀይል ማስተላለፊያ ሳጥኖች እየተሰረቁ ነዉ። እየተዘረፉ በአገለገለ እቃ ስም እየተሸጡ የሚገኙ የተለያዮ መሰረተ ልማቶች መንግስት በከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ የዕለት ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና አለዉ ይላሉ ኮማንደር አበባዉ አሻግሬ የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ፤

በአማራ ክልል በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረግ ዝርፊያ መጨመርምስል፦ Esayas Gelawe/DW

<<የእለት ኑሯችን ላይ ተፅኖ የሚያሳድሩ ማቴርያሎች ከዉጭ በከፍተኛ ምንዛሬ የሚገቡ ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጡ ናቸዉ  ስለዚህ በየጊዜዉ መሰረተ ልማት ዉድመት የሚደርስባቸዉ ከሆነ ሁላችን የሚነካ በህይወታችን አሉታዊ ተፅኖ የሚያሳድር በመሆኑ ማህበረሰቡ የራሱ ንብረት ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት ሊንከባከባቸዉ ይገባል>>

ጦርነትና የህጉ ቀላል ቅጣት ዝርፊያዉ እንዲባባስ በምክንያት ተጠቅሶል

አሁን ላይ በአካባባዉ በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘዉ ጦርነት ለማህበረሰቡ አገልግሎቶ የሚሰጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በቂ ጥበቃ ስለማይደረግላቸዊ ለዘራፊዎች ጥሩ ጊዜን ፈጥርል ይላሉ  አቃቤ ህግ አቶ ይርጋ ደመቀ፤ <<ፖለቲካል ኢኮኖሚዉ ትንሽ ተመቷልተ የተመታዉ አንደኛ ጦርነት ላይ ነዉ ያለነዉ ሁለተኛ ሰላም የለም ሰላም አለመሆኑ በዚህም በዚያም ያለዉ ፀብ አጫሪ ሁኔታ ለሌቦች ጥሩ ምክንያት ሁኗል ለሚሰርቁ ሰዎች>>

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ50 ሚሊዮን ብር ንብረት ተሰረቀበት

እንደ ሀገር የመሰረተ ልማት ስርቆት ላይ የተሳተፉ ሰዎች በህጉ የሚቀጡት ቅጣት አነስተኛ መሆን አጥፊዎችን ሊያስተምር አልቻለም የሚሉት አቶ ይርጋ ህጉ እንደገና ሊፈተሽና ሊሻሻል ይገባል ይላሉ። <<እንግዲህ የሀገሪቱ ህግ አልተሻሻለም አሁን ለምሳሌ  ቻይና የሞት ቅጣትም ሊፈረድበት ይችላል በተለይ ከፍተኛ ፕሮጀክቶች መሰረተ ልማት ላይ ወንጀል የፈፀመ ወንጀለኛ ዝም ብሎ በሦስት ወር በስድስት አመት አይቀጣም በከፍተኛ ቅጣት እንዲቀጣ ብሎ ህጉን አሻሽሎታል የኛ አልተሻሻለም እንግዲህ ዝቅተኛ ከአስር ቀን እስከ ሃያ አምስት አመት ድረስ ይህም ለስርቆት አይደለም ሰዉ ለገደለ ነዉ በመሰረተ ልማት ላይ ብዙም የለም እኛ ጋር አልተለመደም ህግም የለም፤>>

ኢሳያስ ገላዉ 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW