1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ውግያው ቀጥሏል፤ ነዋሪዎች

ዓርብ፣ ነሐሴ 26 2015

በአማራ ክልል ትናንትና እና ዛሬ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የነበሩ ውጊያዎች ጋብ ያሉ ቢሆንም በበርካታ አካባቢዎች ግን አሁንም ውግያ ተጠናክሮ መቀጠሉን የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ውግያ ተጠናክሮ ከቀጠለባቸው አካባቢዎች በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት እና ደምበጫ መካከል፤ ዛሬ ደግሞ በአዴት ተጠቃሽ ናቸው

Äthiopien | Kämpfer der Fano-Miliz in Lalibela in der nördlichen Amhara-Region
ምስል Solan Kolli/AFP/Getty Images

በአማራ ክልል ከሰሞኑ ውግያው የቀጠላበው እና የተረጋጉት አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው?

This browser does not support the audio element.

በአማራ ክልል ትናንትና እና ዛሬ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የነበሩ ውጊያዎች ጋብ ያሉ ቢሆንም በበርካታ አካባቢዎች ግን አሁንም ውግያ ተጠናክሮ መቀጠሉን የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።  የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ውይይት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።ውግያ ተጠናክሮ ከቀጠለባቸው አካባቢዎች በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት እና ደምበጫ መካከል ተጠቃሽ ሲሆኑ ፤ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በተለይ አንጌሌ በተባለው አካባቢ በመንግስት ጦር እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተጠናከረ ውጊያ ሲደረግ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። እዚያው አካባቢ ከሞጣ ወደ ፈረስ ቤት በሚወስድ መንገድ ወይን ውሃ በተባለ አካባቢ በተመሳሳይ ውግያ ሲደረግ እንደነበር ተገልጿል። በየአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ውይይት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል። ክልሉ በደቡብ  ጎንደር ርስቴ ወረዳም በተመሳሳይ በመንግስት ጦር እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ዛሬ ከባድ ውግያ ሲደረግ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአማራ ክልል ግጭት፤ የጅምላ እስር እና የመገናኛ አውታሮች ሽፋንበሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት በሰሜን ሸዋ እንሳሮ ወረዳ እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም ዞን ኤልማና ዲንሳ ወረዳ ለበርካታ ሰዎች ህልፈት ምክንያት የነበረ ከባድ ውጊያ ሲደረግ መሆኑን ዶይቼ ቬለ ተረድቷል። ነገር ግን  የሰዎች ሞት ከመገለጹ ባለፈ ከማን ወገን ምን ያህል ሰው ሞተ ወይም የተገደሉት ሰዎች ሰላማዊ ይሁኑ ታጣቂዎች የተረጋገጠ መረጃ ማግኘት አልተቻለም። በአካባቢው በአዴት እና በለሚ ከተሞች አሁንም ድረስ መንገዶች ዝግ መሆናቸውን የአይን ምስክሮች ተናግረዋል። በአዴት ከተማ ዛሬ ዓርብ ከቀኑ ዘጠን ሰዓት አካባቢ ውጊያ መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ግጭት በሰነበተባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ዛሬ ከሰሞኑ የተሻለ መረጋጋት ቢኖርም በሌሎች ከተሞች ከትናንት ጀምሮ ውጊያ መኖሩን ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ።በሌላ በኩል ሰሞኑን ብርቱ ውግዪ ሲደርግባቸው ከነበሩ አካባቢዎች በደብረ ታቦር ከተማ ወደ መረጋጋት ተመልሶ በከተማዋ ውስጥ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ባለ ሶስት እግር የህዝብ ማመላለሽ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገልጿል። በሌላ በኩል ደግሞ  በክልሉ በአዲሱ ርዕሰ መስተዳድር የተሾሙት የክልሉ የቢሮ ኃላፊዎች የስራ ርክክብ ማድረግ መጀመራቸው ተገልጿል።በአማራ ክልል አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ተሾመ

በጎንደር ከተማ መረጋጋት ተፈጥሮ መደበና እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ሁኔታ እየተመለሱ መሆኑን ዶይቼ ቬለ ያነጋገገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።ምስል Nebiyu Sirak/DW
ፎቶ ከማህደር ፤ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚደረረገው ጦርነት በበርካታ አካካቢዎች ተጠናክሮ መቀጠሉን ነዋሪዎች ተናግረዋልምስል Awi zone communication office

ታምራት ዲንሳ 

ዓለምነው መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW