1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ተሾመ

ዓርብ፣ ነሐሴ 19 2015

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ አረጋ ከበደን አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።ከለውጡ ወዲህ በሰው እጅ የተገደሉትን ዶ/ር አምባቸው መኮንንን ጨምሮ የአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ ሲያደርግ የዛሬው ለ6ኛ ጊዜ ነው። ሌሎች ሹም ሽሮችንም ያካሄደው ጉባኤው ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ  አቶ አረጋ ከበደን አዲሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል
የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ  አቶ አረጋ ከበደን አዲሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል

አቶ አረጋ ከበደ አዲሱ የአማራ ክልል ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

This browser does not support the audio element.

አቶ አረጋ ከበደ አዲሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነዉ ተሾሙ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በጤና ችግር ምክንያት የስራ መልቀቂያ አስገብተዉ ነበር የተባሉት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ መሰናበታቸዉ ተነግሯል። ሌሎች ሹም ሽሮችንም ያካሄደው ጉባኤው ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ባሕርዳር-ግጭት፣ዉጥረትና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአማራ ክልል
በአማራ ክልል ለተፈጠሩ ችግሮች መነሻው የቆዩ የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ ባለመሰጠቱ እንደሆነ፤ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ  ተናግረዋል። አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ዛሬ በተጠራው አስቸኳይ የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ "ያደሩ የአማራ ክልል የማንነት፣ የወሰንና ሌሎች  ጥያቄዎችን በወቅቱ ባለመፍታታችንና ያልተፈቱበትን ምክንያት በየወቅቱ ባላማሳወቃችን ክልሉንና የክልሉን ህዝብ ለቀውስ ዳርገናል" ሲሉ ተናግረዋል። 

በጤና ችግር ምክንያት የስራ መልቀቂያ አስገብተዉ ነበር የተባሉት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ መሰናበታቸዉ ተነግሯል

የአማራ ማንነትና የወሰን ጥያቄዎች
አሁንም ያደሩ የክልሉን ህዝብ ጥያቄዎች ለመፍታት ቀን ከሌት ይሰራል፤ የክልሉ ህዝብ  ጥያቄዎችም ሕግን መሰረት አድርገው ይፈታሉ ሲሉ አፈጉባኢት  ወይዘሮ ፋንቱ ተናግረዋል። ወ/ሮ ፋንቱ፤ ጥያቄ ያላችሁ አካላት ጥያቄያችሁን በኃይል ለመፍታት ከመሞከር በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ሁኑ ሲሉ መጠየቃቸዉ ተነግሯል።

የተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ

ከለውጡ ወዲህ በሰው እጅ የተገደሉትን ዶ/ር አምባቸው መኮንንን ጨምሮ የአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ ሲያደርግ የዛሬው ለ6ኛ ጊዜ ነው። የአማራ ክልል የፍትህ ስርዓት ፈተናዎች
ስለ ሹም ሽሩን ምክርቤቱ ስለተነጋገረባቸው ሌሎች ጉዳዮች የተጠየቀው የባህርዳሩ ዘጋቢያችን አለምነው  መኮንን አስቸኳይ ጉባኤው ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግሯል። 

ዓለምነው መኮንን 

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ዘገባና ትንታኔ

ዘገባና ትንታኔ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW