በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ የዓይን እማኞች አስተያየት
ማክሰኞ፣ መስከረም 8 2016
ማስታወቂያ
በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ዛሬም ውጊያዎች እንዳሉነዋሪዎች እየተናገሩ ነው፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራጎዳና በተባለች ከተማ ባለፈው እሁድ በተቀሰቀሰ ግጭት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ከአካባቢዉ አመለጥን ያሉ ሰዎች ከዶቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ እስከ ቀኑ 6፡30 የነበረውን ሁኔታ አስተያየቶችን አሰባስበናል፡፡የአማራዉ ክልል ቀዉስ ጥላ ያጠላበት የ 2016 ዘመን መለወጫ በአማራ ክልል ስላለሁ ወቅታዊ ሁኔታ ከኦሮሚያም ሆነ ከአማራ ክልል የመንግስት አካላት ተጨማሪ አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ