1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ

ሰኞ፣ ነሐሴ 29 2015

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የመረጋጋታቸው ዜና በመንግሥት አካላት ቢነግርም አሁንም ከባድ ውጊያ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን ከየስፍራው ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል።

ፎቶ ከማኅደር፤ ባሕር ዳር ከተማ
በአማራ ክልል ለጸጥታ ዘርፉ አዳዲስ ሰዎች መሾማቸው ተሰምቷል። ፎቶ ከማኅደር፤ ባሕር ዳር ከተማምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ

This browser does not support the audio element.

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የመረጋጋታቸው ዜና በመንግሥት አካላት ቢነግርም አሁንም ከባድ ውጊያ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን ከየስፍራው ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል። በተለይም በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ አንዳንድ አካባቢዎች ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ውጊያዎች መኖራቸው ተሰምቷል።የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ውይይት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል። በዛሬው ዕለትም ድኩል ቃና እና በረቅ በተባሉ ቀበሌዎች ከፍተኛ  ውጊያ እንደነበር የገለጹት የመረጃ ምንጮች መሬት የሚያንቀጠቅጥ ያሉት የከባድ መሳሪያ ድምጽ መስማታቸውን ተናግረዋል። መረጋጋት በታየባቸው አንዳንድ ከተሞች የመሠረታዊ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ባይባልም የተጀመሩባቸው ከተሞች እንዳሉም ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። እንደ ደብረ ማርቆስ በመሳሰሉት የባንክ አገልግሎት መጀመሩም ተገልጿል። በአንጻሩ አሁንም ባለው የመገናኛ ዘዴዎች ችግር መረጃ ማግኘት ያልተቻለባቸው አካባቢዎች አሉ። ይኽ በእንዲህ እንዳለም በአማራ ክልል ለጸጥታ ዘርፉ አዳዲስ ሰዎች መሾማቸው ተሰምቷል። ይኽን አስመልክቶ የጸጥታ ዘርፍ ቢሮ ኃላፊው አቶ ደሳለኝ ጣሰው በዛሬው ዕለት በጠሩት ስብሰባ ጋዜጠ|ኞችም ተገኝተዋል። ኃላፊው አሁን ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ሊያጠናክር ይችላል በሚል በጸጥታው ዘርፍ አዲስ አደረጃጀት መፈጠሩን አመልክተው ተሿሚዎቹን ይፋ አድርገዋል። በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ውግያው ቀጥሏል፤ ነዋሪዎችበዚህም መሠረት ደስዬ ደጀን አዲሱ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ የምሥራቅ ጎጃም ዞን የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ ምክትል ኮሚሽነር እና የሰው ኃይል አስተዳደር ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን አመልክተዋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት ደጀኔ ልመንህ ደግሞ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል፤ እንደዚሁም ኮሎኔል ግርማ ገሠሠ አዲሱ የክልሉ ሚሊሺያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊነት መሾማቸውን የአማራ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ቢሮ ኃላፊው ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የመረጋጋታቸው ዜና በመንግሥት አካላት ቢነግርም አሁንም ከባድ ውጊያ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን ከየስፍራው ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል። ፎቶ ከማኅደር፤ ጎንደር ከተማ ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW