1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአማራ ክልል የመልሶ ግንባታዎች መጓተት

ዓለምነው መኮንን
ሐሙስ፣ የካቲት 27 2017

የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በነበረው ጦርነት በአማራ ክልል በ94 ወረዳዎች ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሶ እንደነበር አስታውሰው በክልልና በፌደራል መንግሥት በተደረጉ ጥናቶች ውድመቱ በአማራ ክልል ብቻ 10 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚደርስ ነው የገለጡት። ውድመት ከደረሰባቸው94 ወረዳዎች ግንባታ የተጀመረው በ28ቱ ብቻ ነው።

Äthiopien Addis Abeba | Amhara National Regional state Bureau of Finance
ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል የመልሶ ግንባታዎች መጓተት

This browser does not support the audio element.

በሰሜኑ ጦርነት በሶስቱ ክልሎች 20 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት ወድሟል

የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ በአማራ፣ በትግራይና በአፋር ክልሎች ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳቶች መመዝገባቸውን የፌደራል መንግሥት ያደረገውን ጥናት መነሻ በማድርግ የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለዶይቼ ቬሌ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን እንዳሉት በ3ቱ ክልሎች 20 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ንብረት ወድሟል፣ ግማሽ ያክሉ ደግሞ በአማራ ክልል የተመዘገበ እንደሆነ አስረድተዋል።

በነበረው ጦርነት በአማራ ክልል በ94 ወረዳዎች ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሶ እንደነበር ያስታወሱት ምክትል ቢሮ ኃላፊው በክልልና በፌደራል መንግሥት በተደረጉ ጥናቶች ውድመቱ በአማራ ክልል ብቻ 10 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚደርስ ነው የገለጡት። በአማራ ክልል ውድመት ከነበረባቸው 94 ወረዳዎች ግንባታ የተጀመረው በ28ቱ ብቻ ነው.በአማራ ክልል ጉዳት ከደረሰባቸው 94 ወረዳዎች መካክል በ28ቱ ብቻ በዓለም ባንክና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ድጋፍ  የመልሶ ግንባታ እንደተጀመረ ነው የገለጡት።
አሁን በክልሉ ያለው ጦርነት ተጨማሪ የህብት ውድመት እያስከተለ፣ ተጨማሪ መልሶ ግንባታ የሚፈልጉ ቦታዎች እየሰፉ መሄድና የርጂ ድርጅቶች መቀንስ የመልሶ ግንባታ ሥራውን በተፈለገው መጠን እንዳይጓዝና አስቸጋሪ እንዳደረገውም አቶ አታላይ አብራርተዋል።ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው የአማራ ክልል ጦርነት ማብቂያው የት ነው?

በክልሉ 175 የሲቪክ ማህበረስብ ድርጅቶች ይገኛሉ

 

በአማራ ክልል በአሁኑ ሰዓት 175 የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች 17.5 ቢሊዮን ብር ካፒታል አስመዝግበው በተለያዩ ተግባራት ተሰማርተው እንደሚገኙ  ምክትል ቢሮ ኃላፊው ገልጠዋል።
“ ከአንድ ዓመት እስከ 5 ዓመት የሚደርስ የተፈረመ ስምምነት ነው፣  ይህን ይዘው በሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት፣ በዘላቂ ልማት፣ በመልሶ ግንባታ ዘርፎች  ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡”
በክልሉ በልማት ሥራ ከተሰማሩት ድርጅቶች መካክል የተለያዩ ሰበቦችን እየሰጡ ክልሉን እየለቀቁ የሚሄዱ እንዳሉ አመልክተው እነሱ በግልፅ ባይናገሩትም ለመልቀቃቸው ምክን ያቱ በክልሉ ያለው የሠላም እጦት ስለመሆኑ መገመት አያስቸግርም ብለዋል።ጦርነት ያወደማቸው የጤና ተቋማት ተስፋ 

“በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ ያልገቡ ድርጅቶች አሉ” የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ

በአማራ ክልል ያለውን ውስጣዊ ግጭት እንደምክንያት በመቁጠር በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ ያልገቡ ድርጅቶችም እንዳሉ አልሸሸጉም።
አሁን በክልሉ እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ከዚህ በፊት ከነበረው ውድመት ጋር ተዳምሮ  በክልሉ ያለውን ማህበራዊና እኮኖሚያዊ አቅም በእጅጉ ሊጎዳው እንደሚችልም አቶ አታላይ ተናግረዋል።

ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW