1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመከላከያና የፋኖ ግጭት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 27 2015

ሰሞኑንም በሰሜን ሸዋ ዞን ፣ ሸዋ ሮቢት፣ በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ዙሪያ አካባቢዎች፣ በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲና አማራ ሳይንት አካባቢዎች ግጭቶች ተከስተው ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል፡፡በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ ዙሪያ የነበረው የተኩስ ድምፅ ዛሬ የቆመ ቢሆንም ነዋሪዎቹ ስጋት እንዳላቸው ይገልፃሉ፡፡

Karte Äthiopien Amhara ETH

በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በመከላከያና በፋኖ መካከል ግጭቶች መኖራቸውን የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተናግረዋል።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ትናንት በሰጠው መግለጫ የህብረተሰቡን ሰላም ያናጋሉ ባላቸው አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡አለምነው መኮንን ከባህርዳር ተጨማሪ ዘገባ አለው። 
ከጥቂት ወራት ወዲህ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች አለመረጋጋቶችና የሰላም መደፍረስ  እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ ሰሞኑንም በሰሜን ሸዋ ዞን ፣ ሸዋ ሮቢት፣ በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ዙሪያ አካባቢዎች፣ በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲና አማራ ሳይንት አካባቢዎች ግጭቶች ተከስተው ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል፡፡የአማራ ክልል ርምጃና መግለጫ
በዋግኽምራ ማኅበረሰብ አስተዳደር የጋዝ ጊብላ ወረዳ አስ ከተማ ነዋሪ አሁን ስለ አካባቢው ሰላም መደፍረስ በስልክ ነግረውናል፡፡ “ከጋዝጊብላ 08 ቀበሌ ላይ ከላሊበላ 60 ኪሎሜትር፣ ከጋዝጊብላ ደግሞ 27 ኪሎሜትር ላይ መከላከያ በከባድ መሳሪያ እየደበደበ ነው፣ ተኩሱ ትናንተ  12 ሰዓት ላይ ነው በፋኖና መከላከያ መካከል የተጀመረው፡፡  ”
በሰሜን ወሎ ዞን የላሊበላ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው በላስታ ወረዳ አንዳንድ አካባቢዎች ውጊያዎች እንዳሉ አስረድተዋል፡፡
“አሁን በ4ቱም አቅጣጫ በጋሸና በወልዲያ መስመር፣ በዋግ ሰቆጣ በኩልም (መከላከያ) እየመጣ ነው፣ መከላከያው እየቀረበ ነው፣ ጋዝ ጊብላ፣ አስ ከተማን አልፎ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ነው ያለው ከትናንትና ምሽት ጀምሮ”
ከትናንት ጀምሮ ደግሞ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስትና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እንዳለ አንድ የዓይን እማኝ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡
“ከፍተኛ ጦርነት ነው ያለው የጨረቃ ላይ ነበረ፣ ፈረስ ቤት ላይም ውጊያ አለ፣ ብር ወንዝ ላይ ነው ከፍተኛ ውጊያ ያለው”
በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ ዙሪያ የነበረው የተኩስ ድምፅ ዛሬ የቆመ ቢሆንም ነዋሪዎቹ ስጋት እንዳላቸው ይገልፃሉ፡፡በአማራ ክልል እያሳሰበ ያለዉ አለመረጋጋት የቆቦና አካባቢውን አሁናዊ ሁኔታ በተመለከተ አንድ የቆቦ ተማ ነዋሪ አስተያየታቸውን አካፍለውናል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማም ባለፉት ቀናት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ውጊያ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪ አመልክተዋል፣ በደብረታቦር ከተማ ደግሞ ትናንት ምሽት ተኩስ የነበረ ሲሆን ዛሬ ህብረተሰቡ ውይይት ላይ እንደሆነ አንድ የከተማዋ ነዋሪ ተናግረዋል፡ከዚህ በተጨማሪ በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንትና ወግዲ በተባሉ አካባቢዎች ባለፉት ቀናት ተመሳሳይ ግጭቶች እንደነበሩ ነዋሪዎቹ ለዶይቼ ቬሌ በሰጡት አስተያየት አመልክተዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ትናንት በሰጡት መግለጫ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ታጥቀው የህብረተሰቡን ሰላም ያውካሉ ባሏቸው አካላት ላይ መከላከያ ሰራዊት የጀመረውን እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ምስል S.Getu/DW
ምስል Maria Gerth-Niculescu/DW
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ዘገባና ትንታኔ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW