1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአማራ ክልል የዋጋ ንረትና ጫናው

ኢሳያስ ገላው
ሰኞ፣ የካቲት 3 2017

በከፍተኛ ደረጃ የስኳር ዘይት ዱቄት ዋጋ ጨምሯል ዘይትበከ5 ሊትር ላይ 300ብር ጭማሪ አለዉ4800ብር ይገዛ የነበረዉ 5200 ገብቷልዱቄትም 1000ብር ገብቷል ተቆጣጣሪ የለ ምንም የለም ሰዉ በጣም ችግር ላይ ነዉ ያለዉ፤ ይላሉ ለዶቼቬለ አስተያየት የሠጡ ኗሪዎች። ችግሩ ዝቅተኛ ደመወዝ በሚከፈሉ የመንግስት ሠራተኞች ላይ ጎልቶ ይታያልም ይላሉ።

በአማራ ክልል የሚታየዉ የዋጋ ንረት ያሳደረዉ  ጫና
በአማራ ክልል የሚታየዉ የዋጋ ንረት ያሳደረዉ ጫና ምስል፦ Shewangizaw Wegayoh/DW

በአማራ ክልል የሚታየዉ የዋጋ ንረት ያሳደረዉ  ጫና  

በመሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ ከሰሞኑ በአማራክልል ደቡብ ወሎና ሰሜን ወሎ አካባቢዎች እየታየ የመጣዉ የዋጋ ጭማሬ ተከትሎ በኑሯቸዉ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ለዶ ቼቨሌ ሀሳባቸዉን ያጋሩ የወልድያና ደሴ ከተማ ኗሪዎች ተናገሩ። ነጋዴዎች የያዘዉን እቃ ወይ መንገድ ተዘጋ ሲባል ወይ  የሆነ ነገር ሆነ ሲባል ስልክ ተደዋዉለዉ ቀጥታ  ጭማሪው የተወሰነ ሳይሆን በጥፍ ነዉ የሚጨመረዉ ሳይበላ፤ በከፍተኛ ደረጃ ስኳር ዘይት ዱቄት ጨምሯል ዘይት ከ5 ሊትር ላይ 300ብር ጭማሪ አለዉ4800ብር ይገዛ የነበረዉ 5200 ገብቷልዱቄትም 1000ብር ገብቷል ተቆጣጣሪ የለ ምንም የለም ሰዉ በጣም ችግር ላይ ነዉ ያለዉ፤ ከቀን ወደቀን የመሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ጭማሪ እየታየባቸዉ ነዉ የሚሉት ለዶቼቬለ አስተያየት የሠጡ ኗሪዎች ችግሩ ዝቅተኛ ደመወዝ በሚከፈሉ የመንግስት ሠራተኞች ላይ ጎልቶ ይታያል ይላሉ። 

ሁሉም ግብአቶች ከሚገባዉ በላይ እየጨመሩ ነዉ ያሉት በዚህ ሁኔታ ላይ አኗኗራችን እንዴት እንደሆነ ግራ ነዉ የሚገባዉ ለምን እኔ ያሉት መንግስቶች ከደርግ ጀምሮ አዉቃለሁ ግን አሁን ባለንበት ሁኔታ ግን አንድ ነገር ከጨመረ በዚያዉ እየጨመረ ነዉ እንጂ ሲቀንስ አላየሁም፤  ምሳዉን ሳይበላ የሚዉል ሰዉ አለ የኔ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ እቤቱ ሳይሄድ የሚዉል ሰዉ አለ ያላትን ነገር ከርሱ ይቅር ብሎ ለልጆቹ የሚሰጥ የቤት ኪራይ ሲደርስበት ሱቢሂ ወጥቶ ከመሸ የሚገባ ሰዉ አለ። 

በየዕለቱ በገበያ ዉስጥ እየታየ ያለዉ የዋጋ ጭማሬ የንግዱ ማህበረሰብ የፈጠረዉ አይደለም የሚሉት በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ መሀመድ ሊበን በአማራ ክልል የተፈጠረዉ የሠላም መደፍረስ ህጋዊ ባልሆነ ኬላዎች የሚከወን ቀረፅ ለሸቀጦች ጭማሪው ምክንያት ነዉ ይላሉ።

በአማራ ክልል የሚታየዉ የዋጋ ንረት ያሳደረዉ ጫና ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

<በቃ ነዳጂ ሲጨምር አስር ብር ሀያብር ታስጭን የነበረዉ እቃ በአንድ ጊዜ 300  ብር 500 ብር ታስጭናለህ ስለዚህ አንተም ደግሞ ህብረተሰቡ ላይ ትጨምራለህ ወደ ሰሜን ወሎ እንጭን ነበር አሁን ግን የጦርነት አካባቢ በመሆኑ እረብሻ ስላለ እንደ ድሮዉ ስራ የለም  በየቦታዉ ኬላ አለ ራሱ አሁን አስጭነህ የምታመጣዉ እቃ እዚህ ቦታ የኬላ ከፍለናል እየተባለ በየቦታዉ የቀረጥ ወረቀት ነዉ የሚያመጡልህ። 

በክልሉ በተፈጠረ የፀጥታ  ችግር ምክንያት የትራንስፖርት መቆራረጥ ተፈጥሯል

በደቡብ ወሎ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋየ መለስ በበኩላቸዉ በአካባቢው እየተፈጠረ ላለ የዋጋ ንረት በፀጥታዉ ምክንያት ሸቀጦችን ከቦታ ቦታ በተፈለገዉ መጠን ለማንቀሳቀስ ባለመቻሉ ምክንያት የተፈጠረ ነዉ ብለዋል።  ፀጥታዉ በራሱ ፈተና ነዉ አሁን እንደልብህ ምርት አጓጉዘህ ከተለያየ ቦታ ስለማታመጣ እዚህ አካባቢ ያሉ አቅራቢዎች ዎጋ ያስወድዱብሀል እንደ ገና ከባህርዳርም አካባቢ ምርት ዉሰዱ ተብለን እንዴት እናምጣዉ ቢኖር መንገዱ ነፃ ቢሆን ገበያው ላይ ተፅኖ እንፈጥራለን። 

የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማትቢሮ በበኩሉ በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በቀጥታ ከአከፋፋዮች ምርት እንዲሸምቱ ለህብረት ስራ ማህበራት ከ1 ቢልየን ብር በላይ በማቅረብ የማረጋጋት ስራ መሰራቱን ወይዘሮ አትክልት ሀሳቤ የቢሮ ምክትል ኃላፊ ይናገራሉ። መሰረታዊ ፍጆታ የምንላነዉ ምግብና ምግብ ነክ የሆኑ ነገሮች ላይ የበለጠ ለመስራት እንዲያስችለን ከ1ቢልየን ብር በላይ በጀት ከነዚህ ከሸማች ማህበራት ወይም ምርቱን በቀጥታ ገዝተዉ ለተጠቃሚዎች የሚያደርሱ በጀት እንዲያገኙና ስራ እንዲሰሩ በማድረጋችን በርካታ የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሆኑበት ሁኔታ ነዉ ያለዉ። 

በአማራ ክልል የሚታየዉ የዋጋ ንረት ያሳደረዉ ጫና ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

ህጋዊ ያልሆኑ የቀረጥ ኬላዎች መብዛት 

በአማራ ክልል በተለያዮ አካላቶች ህጋዊ ባልሆነ መልኩ የተፈጠሩ ኬላዎች ከፍተኛ ቀረጥ በንግዱ ማህበረሰብ ላይ መጣላቸዉ ለችግሩ መባባስ ምክንያት ነዉ ቢባልም የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ግን በክልሉ ገቢዎች ቢሮ በኩል ለገቢ ማሳደጊያ የተፈጠሩ የኬላ ቀራጮችን በመግባባት የማስቆም ስራ እየተሰራ ነዉ ይላል። ኬላዎቹ ህጋዊ ሁነዉ የተቋቋሙ አይደሉም አብዘሀኛዎቹ የሚወሰደዉ በክልሉ በገጠመዉ የፀጥታ ችግር ምክንያት ህጋዊ ባልሆነ አካል ኬላ የመክፈት ሁኔታዎች አሉ እሱ ትክክል አለመሆኑን ከገቢዎች እንደ አንድ የገቢ ማስገኛ መንገድ የመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ አሁን እያስተካከልን ነዉ። 

ኢሳያስ ገላዉ 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW