1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በብሔራዊ ምክክር እንዲሳተፉ ተጨማሪ ጥሪ ቀረበ

ዓለምነው መኮንን
ቅዳሜ፣ መጋቢት 27 2017

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በብሔራዊ ምክክር እንዲሳተፉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ጥሪ አቀረቡ። ኮሚሽኑ በክልሉ የሚያካሒደው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ዛሬ ተጀምሯል። “አለመገናኘት እያጋደለን ነው” የሚሉ አንድ ተሳታፊ “ ከመማከር ሰላም አለ” ሲሉ ሒደቱ መፍትሔ ያመጣል የሚል ተስፋቸውን ገልጸዋል

መስፍን አርዓያ የኢትዮጵያ ምክክር ዋና ኮሚሽነር
የምክክር ኮሚሽኑ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንዲሳተፉ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ፕሮፌሰር መስፍን ተናግረዋል። ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በብሔራዊ ምክክር እንዲሳተፉ ተጨማሪ ጥሪ ቀረበ

This browser does not support the audio element.

በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ በባሕር ዳር ሲጀመር የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አረአያ ልዩነቶችን በኃይል ለመፍታት በተደረጉ ጥረቶች በአማራ ክልል ከፍተኛ የማህበራዊ፣ የሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ተመዝግበዋል ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት በአማራ ክልል በተፈጠርው ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ሆነዋል፣ በርካታ እናቶች በህክምና እጦት ለከፍተኛ የጤና ቀውስ ተዳርገዋል ፡፡
ችግሮችን በመለየትና የማያግባቡ ነጥቦችን ለይቶ በማውጣት በጉዳዮቹ ላይ ተወያይቶና ተመካክሮ መፍታት ተግቢ መሆኑን የጠቀሱት ፕሮፌሰር መስፍን ከዚያ ውጪ ያሉ አማራጮች ዘላቂ መፍትሔ አያመጡም፣ ካመጡም ዘላቂነት የላቸውም ነው ያሉት።

የአጀንዳ ማሰባሰብ በአማራ ክልል

በክልሉ ትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ኃይሎች ወደ ምክክር መድረኩ እንዲመጡ ኮሚሽኑ  ሠፊ ሥራ ሲስራ ነበር ያሉት ኮሚሽነሩ አሁንም ታጣቂዎቹ ወደ ምክክሩ እንዲመጡ በድጋሜ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዛሬ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የምክክር መድረኩ በይፋ ሲከፈት ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች ምክከሩ ውጤት ያመጣል የሚል እምነት አላቸው፣ በምክክር መድረኩ ያልተገኙ ወገኖችም ጥያቄዎቻቸውን አቅርበው ችግሮች ከአፈ ሙዝ መለስ በንግግር እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

በአማራ ክልል በተጀመረው ሒደት በሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ይታደማሉምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት የሠላም ጥረትና ጥሪ

በምክክር መድረኩ በአማራ ክልል ክሚገኙ 267 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች መካከል ከ263ቱ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተመረጡ ከ4ሺህ 500 በላይ ተወካዮችና ከለሎች ማህበራት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ከሀይማኖት ተቋማት፣ ከተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ከተፈናቃዮች፣ ከአካለል ጉዳተኞችና ከሌሎችም አካላት የተወከሉ፣ በአጠቃላይ ከ6ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉ ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 4/2017 ዓም በሚቆየው ምክክር፣ የአጃንዳ መረጣና በብሔራዊ ደረጃ የሚወከሉ ተሳታፊዎች እንደሚለዩ ታውቋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW