1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ለመኖሪያ ቤት ቦታ ካሳ ክፍያ ተከለከልን አሉ

ሐሙስ፣ ሰኔ 19 2017

ከ2009 ዓ.ም የካቲት 17 ጀምሮ በአማራ ክልል ያሉ መምህራን ተደራጅተው የቤት መስሪያ ቦታ ሲያገኙ የክልሉ መንግስት ከ21 በላይ ለሚሆኑ መምህራን የቦታ ካሳ ክፍያ ፈጽመው ከ3ኛ ወገን ነጻ የሆነን ቦታ አስረክቧል።ሆኖም ደሴ ባህር ዳር ጎንደር ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደርና ምእራብ ጎጃም ያሉ መምህራን የመሬት ካሳ ክፍያ አልተሰጠንም ያላሉ፡፡

Äthiopien Dessie 2025 | Treibstoffknappheit beeinträchtigt den Transport
ምስል፦ Isayas Gelaw/DW

በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን መመሪያ እየፈቀደልን ለመኖሪያ ቤት ቦታ ካሳ ክፍያ ተከለከልን አሉ

This browser does not support the audio element.

ከ2009 ዓ.ም የካቲት 17 ዓ.ም ጀምሮ መምህራን ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ በወጣው መመሪያ መሰረት በአማራ ክልል ያሉ መምህራን ተደራጅተው የቤት መስሪያ ቦታ ሲያገኙ የክልሉ መንግስት ከ21 በላይ ለሚሆኑ መምህራን የቦታ ካሳ ክፍያ ፈጽመው ከ3ኛ ወገን ነጻ የሆነን ቦታ አስረክቧል ይሁን እጂ እንደ ደሴ ከተማ ባህር ዳር ከተማ ፣ ጎንደር ፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር እና ምእራብ ጎጃም ያሉ መምህራን በያዝነው አመት የመሬት የካሳ ክፍያ ሳይከፈላቸው እንደቆዩ ይገልፃሉ፡፡ መምህራኖቹ የካሳ ክፍያውን ከኪሳቸው አውጥተው በመክፈላቸው ዛሬ ላይ በተቀበሉት ቦታ ላይ ቤት መስራት እንደተቸገሩ ይናገራሉ። 
“እኛ ከኪሳችን አውጥተን ነው ካሳ ከፈልነው ያ ይመለስልን ነው ጥያቄያችን በመምሪያው መሰረት ነውየተደራጀነው መመሪያውም እንዳለ ነው ደብዳቤም አለን ክልሉ ነው የሚመልሰው ይክፈለን”  
በደሴ ከተማ የመኖሪያ ቤት እንዲሰጣቸው ተደራጅተው የቤት መስሪያ ይሰጠን የሚሉ መምራኖችም የምናገኘውን ደመወዝ ያላገናዘበ ቤት የመስራት ምርጫ እየቀረበልን ነው ይላሉ፡፡ 
“ባለ 1(አንድ) ምኝታ ብንመርጥ 830,000 (ስምንት መቶ ሰላሳ ሽህ ብር) ነው እሱን እንኳን ባንክ ጋር ቢያይዙልንበወር ለረዥም ጊዜ 11,000 (አስራ አንድ ሽህ ብር) መክፈል ይጠበቅብናል፡፡ የኛ ደመወዝ ደግሞ ከ5,000 እናከ6,000 አይበልጥም” 

 ባለፉት 4 ዓመታት በተደጋጋሚ መምህራኖቹ መብታችን እንዲከበር አወያዩን ምላሽ ስጡን እያልን ብንጠይቅም የከተማ አስተዳደሩ በሰላማዊ መንገድ ሀሳባችንን ለመግለጽ ያቀረብነውን ጥያቄም ከልክሏል ይላሉ መምህራኑ ።
“እንደከተማ አስተዳደርም እንደ ክልልም ጥያቄያችንን ለእናንተ እናቅርብ መድረክ አዘጋጁልን የሚል ጥያቄ አቅርበን ነበር እስከ ሰኔ19 የማይመለስ ከሆነ ሰልፍ እንወጣለን ብለን ነው ያስቀመጥነው ነገር ግን ምላሽ የለምጸጥ ብለዋል”   የደሴ ከተማ ትምህር መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቅር አበበ በበኩላቸው መምህራኑን ከ2009 -2012ዓ.ም በወጣው መመሪያ ውስጥ የሚካተቱ ባለመሆናቸው የካሳ ክፍያው አልተገባቸውም  ይላሉ.። .“ከ2009 እስከ 2012 ለ3 ዓመታት ተብሎ የወጣ መመሪያ አለ ከዚያ ውጭ መሬት የተቀበሉት በ2014 ዓ.ምስለሆነ መረጃቸውን ለክልል ልከናል ግን በዚህ የጊዜ ገደብ የተጠቃለሉ ስላለሆኑ አልተፈቀደላቸውም”።

የደሴው ወ/ሮ ስሂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅምስል፦ Esayas Gelawe/DW

የአማራ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝደንት አቶ ታጀበ አቻም የለህ የክልሉ መንግስት 30,000 ለሚደርሱ መምህራን ከ700,000,000 (ከሰባ መቶ ሚሊየን ብር በላይ) ካሳ በመክፈል የቤት ባለቤት እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ አሁንም ከመመሪያ ውጭ ናቸው የተባሉ መምህራንን ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ እየሰራን ነው ይላሉ፡፡ 
 “ከዚህ ቀደም በሁለት ዙር ከ21,000 በላይ መምህራን 518,000,000  ወጭ አድርጎ የክልሉ መንግስት ካሳከፍሏል በመሃል ላይ የክልሉ መንግስት ያራዘመት ደብዳቤ ስለነበር ከመመሪያ በኋላ የተደራጁ መምህራን ቦታ ከተገኘ ካሳ ሊተካላቸው ይገባል የሚል ጥያቄ ስናቀርብ ቆይተናል፡፡ መረጃ እያጣራን ነው በነበረው አግባብ ጥያቄያቸው ይመለሳል”
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ም/ ኃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደር እና ዞኖች መምህራኑን ያደራጁበት መንገድ ክፍተት ያለበት በመሆኑ እሱን በማስተካከል መረጃ የማደራጀት እና በጀት የማስፈቀድ ተግባር እየሰራን ነው ሲሉ ይገልፃሉ፡፡ “አንዳንድ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች በመዘግየታቸው እና አደረጃጀቱ ችግር ያለበት በመሆኑ ከህግ አንፃር ተቸግረናል የነሱን መረጃ አጣርተን ለክልሉ መንግስት አቅርበን በጀት ለማስፈቀድ እየሰራን ነው”
ኢሳያስ ገላው 
ኂሩት መለሰ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW