1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል የቀጠለዉ ዉግያ

ሰኞ፣ የካቲት 25 2016

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ጦር ሰራዊትና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት እንደቀጠለ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናገሩ። በሰሜን ሸዋ፤ ሸዋሮቢት ከተማ ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ የታየዉ ጦርነት ዛሬ ጋብ ያለ ይመስላል፤ ይሁንና ነዋሪዎች ስጋትና ጭንቀት ላይ ናቸዉ። መርዓዊ ከተማ እና ዙርያዋ ከባድ ዉግያ አለ ተብሏል።

በአማራ ክልል የቀጠለዉ ዉግያ
በአማራ ክልል የቀጠለዉ ዉግያ ምስል AP/picture alliance

ጦርነቱ በተለያዩ አማራ ክልል ከተሞችና ቀበሌዎች የቀጥሏል መርዓዊ ላይ አስር የአብነት ተማሪዎች ሰሞኑን ተገድለዋል።

This browser does not support the audio element.

በአማራ ክልል የቀጠለዉ ዉግያ

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ጦር ሰራዊት እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት እንደቀጠለ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናገሩ። በሰሜን ሸዋ ፤ ሸዋሮቢት ከተማ ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ ይካሄድ የነበረዉ ጦርነት ዛሬ ጋብ ያለ ይመስላል ያሉ አንድ የከተማዋ ነዋሪ፤ ሰዎች ቤታቸዉ ዉስጥ ስጋት ጭንቀት ላይ መሆናቸዉን ተናግረዋል። በሌላ በኩል መርዓዊ ከተማ እና በከተማዋ ዙርያ ከፍተኛ ዉግያ ከተቀሰቀሰ 10 ቀናት እንደሆነዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዚህ ዉግያ ከመራዊ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ አስር የአብነት ተማሪዎች እና ገበሪዎች መገደላቸዉን ፤ መኖርያ ቤቶችም በእሳት መጋየታቸዉን የአይን እማኞች ተናግረዋልል።  

የሸዋሮቢት ወቅታዊ ሁኔታ

ካለፉት ቀናት ወዲህ በሰሜን ሸዋ በተለይ ሸዋሮ ሮቢት ከተማ እየተካሄደ የነበረዉ ጦርነት ዛሬ ጋብ ያለ ይመስላል ያሉ አንድ የከተማዋ ነዋሪ ሰዎች ከቤታቸዉ እንዳልወጡ እና ስጋት ጭንቀት ላይ መሆናቸዉን ተናግረዋል። የዓይንን እማኙ እንዳሉት ትናንት እና ከትናንት በስትያ በከተማዋ ይሰማ የነበረዉየማያቋርጥ የከባድ እና ቀላል መሳርያ ድምፅ ዛሬ ጋብ ያለ ይመስላል፤ ይሁንና ከቤታችን መዉጣት አልቻልንም ብለዋል። ስለሆነም ከተማዋ በመንግሥት እጅ ስር አልያም በፋኖ እጅ ስር ስለመዉደቅዋ የምናዉቀዉ ነገር የለም። በአሉ ግን መንግስት እጅ ስር ነዉ መባሉን ሰምተናል ብለዋል።

በመርዓዊ ከተማ እና አካባቢዋ የቀጠለዉ ዉግያ

በሌላ በኩል አማራ ክልል ሰሜን ጎጃም መርዓዊ ከተማ እና ዙርዋ ላይ ከአስር ቀናት ወዲህጀምሮ ከፍተኛ ዉግያ እየተካሄደ ነዉ ያሉን  ሌላዉ የአካባቢዉ ነዋሪ ናቸዉ። ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት እስከ ቀኑ ስምንት ሰዓት ድረስ  ዛሬ  መራዊ ከተማ እና ዙርያዋ ላይ ከፍተኛ ዉግያ እየተካሄደ ነዉ፤ በከተማዋ እና በከተማዋ ዙርያ ጦርነቱ ዳግም ከተቀሰቀሰ ዛሬ አስር ቀናት ሆነዉታል። በዚህ ዉግያ በከተማዋ ዙርያ በአንድ ቤተክርስትያን ዉስጥ የሚገኙ አስር የአብነት ተማሪዎችን ጨምሮ ሁለት ገበሪዎች እና ሌሎች አምስት ነዋሪዎች ባለፈዉ ረብዕ ፤ በዘፈቀደ ተገድለዋል ሲሉ የዓይን እማኙ ተናግረዋል።   ዛሬም በመራዊ ከተማም ሆነ በከተማዋ ዙርያ ጦርነቱ በከፍተና ሁኔታ እንደቀጠለ ነዉ።  

በአማራ ክልል የቀጠለዉ ዉግያ ምስል Awi zone communication office

ደንበጫ ከተማ አንጻራዊ ሰላም

በደንበጫ ከተማ ሰሞኑን ትንሽ አለመረጋጋት ነበር ዛሬ ግን የመንግሥት ትራንስፖርትም ሆነ የመንግሥት መስርያ ቤቶች እየሰሩ ነዉ ሲሉ ሌላ አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።  አንጻራዊ ሰላም በከተማዋ አለ፤ ሰዉ ካልሞተ የመሳርያ ድምፅ ካልተሰማ ሰላም ሆንዋል ብለን እንናገራለን ሲሉም አክለዋል። ጉዳዩን ተከትሎ በአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቤሮ ኃላፊ አቶ ደስ አለኝ ጣሰዉን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም። ይሁንና ባለፈዉ ሳምንት መገባደጃ  በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህርዳር ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግርተከትሎ ዛሬ ይፋ ,ሆነዉ መግለጫ፣  የክልሉ እና የከተማ አስተዳደሩ የፀጥታ ተቋማት ከፌደራል የፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በወሰዱት ህግ የማስከበር ተግባር ኃላፊነት የጎደላቸዉ አካላት፤ በከተማዋ እና በነዋሪዎች ላይ ያቀዱት ትርምስ ሳይሳካ ቀርቷል፤ ፀጥታ አካላት የከተማዋን ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰሩ መሆናቸዉም ተመልክቷል።

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW