1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሰፈሩ ተፈናቃዮች ብሶት

ዓርብ፣ ሐምሌ 12 2016

ከኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሰፈሩ ተፈናቃዮች የእርዳታ እህል በወቅቱ አልደረሰንም አሉ፣ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ደግሞ “አንዳንዴ መዘግየቶች ቢኖሩም የእርዳታ እህል ወደተፈናቃዮች ማጓጓዝ ጀምሪያለሁ” ብሏል፡፡

Äthiopien IDPs in der Region Amhara
ምስል Alemenw Mekonnen/DW

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሰፈሩ ተፈናቃዮች ብሶት

This browser does not support the audio element.

 

ከኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሰፈሩ ተፈናቃዮች የእርዳታ እህል በወቅቱ አልደረሰንም አሉ፣ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ደግሞ “አንዳንዴ መዘግየቶች ቢኖሩም የእርዳታ እህል ወደተፈናቃዮች ማጓጓዝ ጀምሪያለሁ” ብሏል፡፡

በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያቶች በአማራ ክልል በርካታ ወገኖች ለእርዳታ እህል እጃቸውን ዘርግተዋል፣ በክልሉ በድርቅ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ድጋፍ የሚፈልጉ ሲሆን በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ቀደም ሲል በነበሩ ብሔር ተኮር ግጭቶች የተፈናቀሉ ሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖች  በአማራ ክልል በመጠለያ ጣቢያዎችና ከማህበረሰቡ ጋር ተጣምረው ይኖራሉ፡፡በሐይቅ የሚገኙ ተፈናቃዮች የእርዳታ ተማፅዕኖ

በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ከሚኖሩ ተፈናቃዮች መካከል አንዳንዶቹ በቂ የሆነ የምግብ እርዳታ በጊዜው ሊደርሳቸው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ችግር እንደተዳረጉ ይናገራሉ፡፡፡

የተፈናቃዮች አስተያየት

በደቡብ ወሎ ዞን በተለምዶ “ቱርክ” ከሚባል የተፈናቃች መጠለያ ጣቢ አስተያየታቸውን የሰጡን እናት እንዷ ናቸው፡፡

ተፈናቃይዋ እንደሚሉት የእርዳታ እህል ካገኙ ሁለት ወራት አልፈዋል፣ እርዳታ ሰጪ አካላት እንሰታለን እሉ ቢናገሩምምንም የደረሳቸው ነገር እንደሌለ ገልጠዋል፡፡ መፍትሔ እንዳላገኙና የሚሰማቸው አካል እንደሌለ ነው አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡ “ተፈናቃዩ እያለቀ ነው፣ በቅርቡ አንድ እናት በርሀብ ህወታቸው አልፏል፣ ደካማና ህጻናት አሁንም ቢሆን ከመጠለያ አይወጡም” ሲሉ ነው ለውን ችግር ያመለከቱት፡፡ የመጠለያ ጣቢያው ድንኳኖችምእረጁ በዝናብና በነፋስ ጉዳት እደረሰባቸው አንደሆነ ነው የሚያስረዱት፡፡የወለጋ ተፈናቃዮች ሮሮ

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሀን አካባቢ “ወይንእሸት” ከተባለ መጠለያ ጣቢያ የሚኖር ተፈናቃይ በበኩሉ ቀደም ሲል እርዳታ ሰጡ የነበሩ መንግስታዊ ልሆኑ ድርጅቶች ከአካባቢው በመልቀቃቸው የምግብ አቅርቦት ችግሩ ተባብሷል ነው ያሉት፡፡ የእርዳታ እህል አልፎ አልፎ እንደሚቀርብ መለከቱት እኚህ ተፈናቃይ የሚመጣውም በቂ ስለማሆን ሰዎች እንደተቸገሩ አብራርተዋል፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን “ጃራ”የተፈናቃዮች መጠለያ የሚኖሩት ተፈናቃይም የእርዳታ እህል ካገኙ አንድ ወር ማለፉን ለዶቼ ቬሌ በስልክ ገልጠዋል፡፡

አማራ ክልል የሚገኙ የወለጋ ተፈናቃዮች ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ሌላው ሰሜን ሸዋ ደብረብርሐን አካባቢ “ቻይና” በተባለ የተፈናቃዮች ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃይ በበኩላቸው የሚቀርበው የእርዳታ እህል በቂ ካለመሆኑም በላይ ትራቱን የጠበቀ አይደለም ሲሉ ነው ቅሬታቸውን የተናገሩት፡፡

“መንግስት ቀደም ሲል 15 ኪሎ ስንዴ ለአንድ ሰው ያቀርብልን ነበር፣ አሁን ደግሞ ከስንዴ ወደ ቦቆሎ ቀይሮታል፣ ቦቆሎውም እንደ እድል ካላገኘህ አይደርስህም፣ ቦቆሎውም ለምግብ ፍጆታ የማሆን የሚመጣበት ጊዜም አለ ይህም ቢሆን ጊዜውን ጠብቆ አይመጣታም፣ ዘይት የለም፣ ለወት የሚሆን ግብዓት የለም፡፡” ብለዋል፡፡

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች  ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምላሽ

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፕሮግራሞች  ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል፣ እርዳታ ከሚያጓጉዙ ተሸከርካሪዎች ቁጥር በቂ አለመሆን ጋር በተያያዘ የእርዳታ እህል በታቀደው ጊዜ ለተረጂዎች የማይደርስበት ጊዜ እንዳለ ጠቁመው፣ የእርዳታ እህል ከኮምቦልቻ የእርዳታ እህል ማከማቻ መጋዝን የማጓጓዝ ስራ መጀመሩን ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል ያለው የእርዳታ ፈላጊው ቁጥር

በአማራ ክልል በተለያዩ ምክንቶች ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በየወሩ የእርዳታ እህል የሚሰፈርላቸው እንደሆነ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፕሮግራሞች  ኮሚሽን አመልክቷል፡፡

ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW