1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአማራ ክልል የተካሄደው ሰልፍ ምን ይመስል ነበር?

ኢሳያስ ገላው
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 9 2017

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፋኖ እና በመንግሥት ወታደሮች መካከል ያለው ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ በመንግስት የተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ተካሄደ ። የቦንብ ፍንዳታና የጥይት ተኩስ የነበረባቸው ቦታዎች መመልከታቸውም የዐይን እማኞች ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል ።

Äthiopien Dessie 2024 | Friedensdemonstration in Amhara-Region
ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

በአማራ ክልል የተካሄዱ ሰልፎች

This browser does not support the audio element.

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች  በፋኖ እና በመንግሥት ወታደሮች መካከል ያለው ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ በመንግስት የተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ተካሄደ ። ትእይንተ ሕዝቡ ሰላም ለማስፈን አስፈላጊ ነው ሲሉ ለዶይቸ ቬለ የተናገሩ እንዳሉ ሁሉ፤ ሰልፉ በመንግሥት አስገዳጅነት ያለፍላጎት የተካሄደ ነው ያሉም ነበሩ ።  ትእይንተ ሕዝብ የተካሄደባቸው አንዳንድ ቦታዎች የፋኖ ታጣቂዎች ከፈቱት በተባለው ተኩስ ሰልፎቹ ሳይካሄዱ ተበትነዋል ። የቦንብ ፍንዳታና የጥይት ተኩስ የነበረባቸው ቦታዎች መመልከታቸውም የዐይን እማኞች ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል ።  

በመንግስትና በፋኖ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘዉ ጦርነት ተባብሶ ቀጥሏል በሚባልበት በዚህ ወቅት በአማራ ክልል ዋናዋና ከተሞችና ወረዳዎች በመንግስት የተጠራዉ ትእይንተ ሕዝብ ዛሬ ተከናዉኗል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የታደሙት የደሴ ከተማ ኗሪ አቶ ሰሎሞን አሠን ለዶቼቬሌ እንደተናገሩት የተካሄደዉ ትእይንተ ሕዝብ ለህብረተሰቡ የሚጠቅምና ፍላጎቱን በግልፅ ያሳየበት ነዉ ብለዋል ሌላዉ አስተያየት ሰጭ የመተማ ዮሀንስ ከተማ ኗሪ የሆኑት አቶ ስጦታዉ ጫኔ ኅብረተሰብ ፍላጎቱ ሰላም መሆኑን ያሳየበትና ጦርነት ይብቃን ያለበት ዕለት ነዉ ብለዋል ።

በተመሳሳይ ትዕይንተ ሕዝቡ የተካሄደባቸዉ የሰሜን ሸዋ የአንሳሮ ወረዳና የሽዋሮቢት ከተማ ኗሪ የሆኑና ለደህንነታቸዉ ሲባል ስማቸዉ እንዲገለፅ ያልፈለጉ አስተያየት ሰጭዎች ማህበረሰቡ ወደሰልፍ ቦታ በግዴታ ነዉ የተጠራዉ ይላሉ በተለይም የመንግስት ሰራተኞች ጥብቅ ቁጥጥር ተደርጎባቸዋል ሲሉ ሀሳባቸዉን ይገልፃሉ ።

ሰልፎቹ የተካሄዱት በመንግስትና በፋኖ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘዉ ጦርነት ተባብሶ ቀጥሏል በሚባልበት በዚህ ወቅት ነውምስል፦ Esayas Gelaw/DW

በአማራ ክልል የተካሄዱ ትዕይንተ ሕዝቦች በአንዳንድ አካባቢ የቦንብ ፍንዳታና የጥይት ተኩስ የነበረባቸዉ መሆኑን የገለፁልን አስተያየት ሰጭዎች በደሴና ወልድያ የቦንብ ፍንዳታ በመርሳ ከተማ ደግሞ ተኩስ መኖሩን ነግረዉናል ።

የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ከሰዓት በኃላ ባስተላለፉት መልዕክት  ህዝባዊ ሠልፍ የተካሄደባቸዉ አካባቢዎች የከሸፉ የቦንብ ፍንዳታና የተኩስ እሩምታ ያልበገሩት ነበር ብለዋል በተመሳሳይ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንም በወልድያ ከተማ ሁለት ተጠርጣሪዎች ቦንብ ለመወርወር ሲዘጋጁ በመያዝ ምርመራ ላይ ነኝ ሲል በፌስቡክ የትስስር ገፁ ላይ አስነብቧል ።

ኢሣያስ ገላው

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW