ሰሞኑን በአማራ ክልል የተካሄዱ ህዝባዊ ዉይይቶች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች
ማክሰኞ፣ ጥር 28 2016![ባህር ዳር ከተማ፤ የአማራ ክልል መዲና](https://static.dw.com/image/68184968_800.webp)
ማስታወቂያ
በአማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ በዘላቂነት ለመፍታትና አሉ በተባሉ ችግሮች ዙሪያ የፌደራልና የሁሉም ክልሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች ሰሞኑን በአማራ ክልል 15 ያህል ከተሞች ህዝባዊ ውይይት አድርገዋል፡፡
በሕዝባዊ ውይይቱ በክልሉ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አስቸጋሪ ስለመሆኑ፣ የማንነትና የወሰን ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ማግኘት አለመቻላቸው፣ የህገ መንግስት ይሻሻል ጥያቄ በወቅቱ መፍትሔ አለማግኘቱና የተፈናቃዮች ሁኔታና ሌሎችም “ገፊ” የተባሉ ችግሮች በክልሉ ለተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ምክንያት እንደሆኑ በስፋት ተነስተዋል፡፡
ባለስልጣናቱ ማንኛውም ጥያቄ አለኝ የሚል አካልና በተወያዮቹ ለተነሱ ጥያቄዎች መንግስት ለመወያየትና ችግሮቹ አንዲፈቱ በሩ ክፍት መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በውይይቱ ዙሪያ ያነጋገርናቸው አንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች ውይይቱን በአወንታዊ ሲመለከቱት ሌሎች ደግሞ ውይይቶቹ ማዘናጊያና በህዝብ ያልተወከሉ ሰዎች የተሳተፉባቸው መድረኮ ናቸው ሲሉ ተችተዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ