1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል የኢንተርኔት መቋረጥ ያስከተለዉ መጠነሰፊ ችግር

ዓርብ፣ ሐምሌ 5 2016

በአማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታን ተከትሎ በአብዛኛ አካባቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነዉ። የስራ ባህሪያቸው ከኢንተርኔት ጋር ግንኙነት ያላቸው ተቋማትና ግለሰቦች በዚህ ምክንያት ለበርካታ ችግሮች መዳረጋቸውን እያማረሩ ነዉ፡ በክልሉ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መጠናቀቅን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ይጀምራል ተብሎ ነበር።

የኢንተርኔት መቋረጥ ያስከተለዉ መጠነሰፊ ችግር 
የኢንተርኔት መቋረጥ ያስከተለዉ መጠነሰፊ ችግር ምስል Fotolia/dell

በአማራ ክልል የኢንተርኔት መቋረጥ ያስከተለዉ መጠነሰፊ ችግር

This browser does not support the audio element.

በአማራ ክልል የኢንተርኔት መቋረጥ ያስከተለዉ መጠነሰፊ ችግር 


የኢንተርኔት አገልግሎት በአማራ ክልል አገልግሎት ባለመጀመሩ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶች ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ እንደሆነ አንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፣ በተለይ በጤናውና በኢንዳስትሪው ዘርፍ ላይ ጫናው በርትቷል ይላሉ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ሰሞኑን የመስሪያ ቤታቸውን ዓመታዊ አፈፃፀም ሲያቀርቡ ደግሞ የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር እየተወያዩ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ በአማራ ክልል የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ በአማራ ክልል አብዛኛዎቹ አካባቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል፡፡  የስራ ባህሪያቸው ከኢንተርኔት ጋር ግንኙነት ያላቸው ተቋማትና ግለሰቦች በዚህ ምክንት ለበርካታ ችግሮች መዳረጋቸውን ይገልፃሉ፡፡ አስተያየታቸውን ከሰጡን ነዋሪዎች መካከል የደሴ ከተማ ነዋሪ፣ እንዲህ ብለዋል። 


“... ከውጪ ጋር የንግድ ግንኙነት ያላቸው ተቋማት ዜሮ ገብተዋል በዚህ ጉዳይ ላይ፣ እኔ ያለሁበት ተቋም ግዥ የሚፈፅመው ከውጪ ተቋማት ጋር ነው፣ ጨረታም የምንጫረተው በኢንተርኔት ነው፣ ኢንተርኔት ግን የለም፣ ይህ በመሆኑ  ሁለት ጊዜ ጨረታ አውጥተን ግንኙነት የለም፣ ሆቴልም ብንሄድ አንድ ሻ ጠጥተህ 50 ብር ትከፍላለህ፣ ያም ሆኖ የተሟላ አገልግሎት የለም፣ እና የዚህ አንድ ዓመት ኑሮ ኑሮ አይደለም፣ በአጠቃላይ ገበያውን ጎድቶታል፣ ውጪ ያሉ ደንበኞቻችን ግንኙነታችን ደካማ መሆኑን ሲያውቁ ሆን ብለን ያደረግነው ስለሚመስላቸው ቅሬታ ይፈጠርባቸዋል፡፡”
በምዕራብ ጎጃም ዞን የደንበጫ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው የኢንተርኔት መቋረጥ በጤናው ዘርፍ ያለውን የግንኙነት ሂደት ጎድቶታል ብለዋል፣ ወደ ባህር ዳር በመሄድ በአንዳንድ ሆቴሎች አገልግሎቱን ለማግኘት ጥረት ቢደረግም የአገልግሎት ዋጋው ከፍተኛ ነው ነው ያሉት፣ መንግስት የጤናውን ዘርፍ የኢንተርኔት አገልግሎት ዘግቶ ሆቴሎች እንዲጠቀሙ ማድረጉ ራሱ “የሚጣረስ ” ነው ብለውታል፡፡
የደብረማርቆስ ነዋሪ በበኩላቸው ሆቴል ውስጥ አገልግሎቱን ለማግኘት ጥረት ቢደረግም አጥጋቢ አገልግሎት ማግኘት እንደማይቻል ገልጠዋል፡፡


የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው የትምህርትና የስልጠና አማራጮችን ለማግኘት የኢንተርኔት መዘጋት እንቅፋት ፈጥሮብናል ሲሉ ነው አስተያየት የሰጡት፡፡ “ኢንተርኔት አለመኖሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ እድሎች ተወዳዳሪ እንዳንሆን አድርጎናል፣ ማስታወቂያዎችን ኤተህ ስራ መወዳደር አትችልም፣ የኦን ላይን ትምህርቶችን መማር አትችልም፣ እናም ኢንተርኔት ከሚያገኘው ሌለው ኢትዮጵያዊ ጋር ተወዳድረን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚጥስ ነገር ነው፣ እንደሰው መረጃ የማግኘት ነፃነት ይገድባል፣ ከዚያም ባሻገር ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማወቅ አላስቻለንም፡፡” ብለዋል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የመስሪያ ቤታቸውን ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም በማስመልከት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በአማራ ክልል ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንደገና ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር እየተነጋገሩበት እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ በአማራ ክልል ለሁለት ጊዜ የተደነገገው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ ገዜው ከተጠናቀቀ በኋላ የኢንተርኔት አገልግሎት ይጀምራል ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን አገልግሎቱ በተሟላ ሁኔታ አልተጀመረም፡፡ 


ዓለምነው መኮንን
አዜብ ታደሰ 
ፀሐይ ጫኔ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW