1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአማራ ክልል የዳኞች ያለመከሰስ መብት የሕግ ማዕቀፍ ማግኘት

ዓለምነው መኮንን
ሰኞ፣ የካቲት 10 2017

9ኛው የአማራ ክልል ም/ቤት ጉባኤ ለዳኞች ያለመከሰስ መብት የሚሰጥ ደንብ ማጽደቁ ታላቅ እርምጃ መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ገለፁ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እርምጃውን በበጎ ተመልክቶታል። አንድ የሕግ ባለሙያ ወሳኔው እርሳቸውንም እንዳስደሰታቸው ገልጠዋል፡፡

9ኛው የአማራ ክልል ምክርቤት ጉባኤ
9ኛው የአማራ ክልል ምክርቤት ጉባኤምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል የዳኞች ያለመከሰስ መብት የህግ ማዕቀፍ ማግኘት

This browser does not support the audio element.

ሰሞኑን የተካሄደው 9ኛው የአማራ ክልል ምክርቤት ጉባኤ ለዳኞች ያለመከሰስ መብት የሚሰጥ ደንብ ማጽደቁ ታላቅ እርምጃ መሆኑን የሕግ ባለሙያዎች ገለፁ፣ የኢትዮጵያሰብ አዊ መብት ኮሚሽን እርምጃውን በበጎ ተመልክቶታል። የአማራ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን ባካሄደው 9ነኛ መደበኛ ጉባኤ ዳኞች በሚወስኗቸው ውሳኔዎችና በስራዎቻቸው ላይ ያለአግባብ ጣልቃ እንዳይገባባቸውና ከለላ የሚሰጥ ያለመከሰሰ ደንብ (Immunity) አፅድቋል።

የአማራ ክልል ምክርቤት 9ኛ ጉባኤና የነዋሪዎች አስተያየት
በአማራ ክልል የዳኞች ያለመከሰስ መብት የህግ ማዕቀፍ ማግኘት
የአማራ ክልል ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ደሴ ጥላሁን በክልሉ ለዳኞች የህግ ከለላ መስጠት የሚያስችሉ ደንቦች እንዲፀድቁ በተለያዩ ጊዜዎች ጥያቄዎች ሲቀርቡ እንደንበር ጠቁመው አሁን  ጥያቄው ምላሽ መግኘቱን ተናግረዋል። ይህ ሲባል ግን ዳኛ ሲያጠፋ አይቀጣም ማለት እንዳለሆን ተናግረዋል። ዳኞች ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው ሲጠረጠሩ ወይም እጅ ከፍንጅ ሲያዙ ለዳኞች ጉባኤ ማመልከቻ በማቅረብ ሊያዙ ይችላሉ፣ ከዳኝነት ሥራቸው ጋር ተፅዕኖ እንዳይደርስባችው የተሰጠ ያለመከሰስ መብት እንደሆነ አመልክተዋል።  አንድ የህግ ባለሙያ ወሳኔው እርሳቸውንም እንዳስደሰታቸው ገልጠዋል፡፡

9ኛው የአማራ ክልል ምክርቤት ጉባኤምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW


የደንቡ መፅደቅ ዳኞች በነፃነት እንዲሰሩ ይረዳል መባሉ
የአማራ ክልል የዳኞች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ብርሐኑ አሳሳ የተሰጠውን የህግ ከለላ ትርጉም በማስቀደም የደንቡ መፅደቅ ዳኞች በነፃነት እንዲሰሩ እድል የሰጣል ብለዋል።
“ (Immunity) ያለመከሰስ መብት ወሳኔ ሰጪው ከሌሎች ጣልቃገብነት ነፃ ሆኖ ውሳኔውን ገለልተኛ ሆኖ እንዲወስን የሚያደርግ ጠበቃ ማለት ነው፡፡” ነው ያሉት፡፡
አቶ በጊዜው ገነት የተባሉ ዳኛ በበኩላቸው የተሰጠው ውሳኔ ለዳኛው ብቻ ሳይሆን ህብIረተሰቡም ትክክለኛ ፍትህና ፍርድ እንዲያገኝ ያግዘዋል፣ እርምጃው ተግቢ እንደሆንና ዳኞች ሳይሸማቀቁ እንዲሰሩ እንደሚያግዝ አመልክተዋል።ጦርነት በተማሪዎች እና ትምህርት ስርዓቱ ላይ የሚጥለው ጠባሳ


“የአማራ ክልል ውሳኔ መልካም ጅምር ነው” ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው መግለጫ እንዳሰታወቀው “የዳኝነት ነፃነት ለዲሞከራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና ለሰብአዊ መብቶች መከበር መሠረት በመሆኑ የዳኞች ያለመከሰስ መብት የሕግ ከለላ ማግኘቱ በክልሉ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ለስብአዊ መበቶች ጥበቃ ወስኝ ነው፡፡” ብሏል።

9ኛው የአማራ ክልል ምክርቤት ጉባኤምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW


ሌሎች ከልሎች ሊተገብሩት የሚገባ ውሳኔ ስለመሆኑ
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ራኬብ መሰለ በሰጡን ተጨማሪ አስተያየት በክልሉ የዳኝነት ነፃነት እንዲከበር ኮሚሽናቸው ግፊት ሲደረግ እንደነበር አስታውሰው፣ የአማራ ከልል የዳኞችን ደህንነት ለመጠበቅ የወሰደው እርምጃ የሚበረታታ መሆኑን ገልጠዋል፣ ሌሎች ክልሎችም ለዳኞች ጥበቃና ከለላ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። የዳኞች ያለመከሰስ መብት በአገር አቀፍ ደረጃ የህግ ማዕቀፍ ያገኘ በ2013 ዓ ም ሲሆን የኦሮሚያ ክልል ይህን ደንብ ያፀደቀው ደግሞ ከአገር አቀፉ ከ2 ዓመታት በፊት በ2011 ዓ ም እንደነበር ከአማራ ክልል የህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው ከዶ/ር ደሴ ጥላሁን መረዳት ችለናል። ሰሞኑን በተካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት 9ነኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ  በቀረበ ሪፖርት ባለፉት 6 ወራት ብቻ 89 ዳኞች በተለያዩ ምክንያቶች ከስራቸው መልቀቃቸው ተመልክቷል። 


ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW