በአማራ ክልል የ6 ዓመት ህጻንን ያገቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 23 2017እገታ በአማራ ክልል መቀነሱን ፖሊስ ቢገልፅም አንዳንድ ነዋሪዎች ደግሞ "ገና ነው" ይላሉ።
እገታ አሁንም በአማራ ክልል ችግር መሆኑን ነዋሪዎች ገልጠዋል፣ ፖሊስ በበኩሉ ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት የድርጊቱ ፈፃሚዎች በቁጥጥር ሥረ እየዋሉ ነው ብሏል። አንዳንድ ነዋሪዎችም ይህንኑ አረጋግጠዋል። ሰሞኑንም ደግሞ አንድ የ6 ዓመት ህፃን አግተው ማስለቀቂያ ገንዘብ የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
“እገታና ዝርፊያ አልቀንስም” የጎንደር ነዋሪዎች
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል እገታ፣ ዘረፋና የመሳሰሉት ወንጅሎች ህብረተሰቡን ሠላም እንደንሱት ነዋሪዎቹ ይናግራሉ። አንድ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ሰሞኑን በከተማዋ አንድ አካባቢ እገታ መካሄዱን መስማታቸውን አመልክተዋል፣ በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገው እገታም በተለይ በመተማ መስመር አልተሻሻልም ብለዋል።
ሌላ የክተማዋ ነዋሪም ጎንደር ከተማ ወስጥ የህፃን እገታው መካሄዱንና የተሻሻለ ነገር እንደሌለ፣ ህብረተስቡ አሁንም በስጋት ላይ እንደሆን አስረድተዋል።
በአማራ ክልል እገታና ግድደያ ነዋሪውን አማርሯል፡፡
የ6 ዓመት ህፃን ያገቱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ሰሞኑ አንድ ተጠርጣሪ ከሌላ ግብረ አበሩ ጋር በመሆን ቃፍታ ሁመራ “ባዕክር” በተባለ ቀበሌ በቀን ሠራተኛነት ተቀጥሮ የሚሰራበትን ቤተሰቦች የ6 ዓመት ህፃን አግቶ ተሰውሮ እንደነበርና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹ ጥቅም 21/2017 ዓም በጎንደር ከተማ ቀበሌ 16 “ብላጅግ” ከተባል ጫካ ውስጥ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር መሳፍንንት እሸቴ ተናግረዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ግፃኑን አግተው ጎንደር ከተማ በማምጣት 700 ሺህ ብር ካላመጡ ህፃኑን እንደማይለቁት ስልክ በመደወል ሲዝቱ እንደነበር የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር መሳፍንንት እሸቴ ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ ገልጠዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች በንፅፅር ዝርፊያና እገታ ቀደም ሲል ከነበረው ቀንሷል ተብሏል
ከእገታው ጀርባ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ይኑሩ አይኑሩ የሚለውንና ሌሎች ጉዳዮች ካሉ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራዎችን እያካሄደ እንደሆነም ኮማንደር መሳፍነነት አመልክተዋል።
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ቀደም ሲል እገታዎችና ዝርፊያ ይካሔድ እንደነበር የነገሩን አንድ የከሚሴ ከተም ነዋሪ አሁን ችግሮቹ ቀድሞ ከነበረው የተሻለ እንደሆነ ነው ያብራሩት ።
በምዕራብ ጎጃም ዞን የደንበጫ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው በእገታና ዝርፊያ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ቀደም ሲል እርምጃ በመወስዱ እግታና ዝርፊያ ቀንሷል ብለዋል።
እልባት የሚሹት የእገታ ወንጀሎች ነዋሪዉን እያማረሩ መሆኑ
“እገታ እየቀነሰ ነው” የአማራ ክልል ፖሊስ
የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር መሳፈንንት እሸቴ መንግሥትና ህበረተሰቡ ባደርጉት የጋራ ጥረትና ትብብር የድርጊቱ ፈፃሚዎች በህግ ቁጥጥር ሥር እየዋሉ እንደሆን አመልክተዋል።
በክልሉ ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዝ በበርካታ አካባቢዎች እገታ፣ ዝርፊያና መዋከብ ነዋሪውን በእጅጉ አማርሮታል።
ዓለምነው መኮንን
ታምራት ዲንሳ