1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ጎንደር ዞን በሽህዎች የሚቆጠሩ ቤቶች በውሀ ተከበዋል

ዓርብ፣ ነሐሴ 3 2016

የአካባቢው አርስ አደሮች እንደተናገሩት በሰዎች ላይ የሞት አደጋ ባይደርስም እንስሳት በጎርፍ ተወስደዋል፣ የእንስሳቱ የግጦሽ መሬትም ደለል ለብሷል ፡፡የአደጋው ሰለባዎች እንዳሉት ፣የሩዝ ሰብልም በጎርፍ ተጥለቅልቋል፣ በርካታ ቤቶችም በውሀ ተከብበዋል ። መንግስት ከአካባቢው እንዲወጡ ቢጥርም በፀጥታ ችግር ምክንያት ብዙዎቹ መውጣት አልፈለጉም።

Äthiopien I Überschwemmung in Süd-Godder, Amhara-Region
ምስል South Gondar zone Disaster prevention Office/Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ጎንደር ዞን በሽህዎች የሚቆጠሩ ቤቶች በውሀ ተከበዋል

This browser does not support the audio element.

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በሶስት ወረዳዎች በሚገኙ 9  ቀበሌዎች ክረምቱን ተከትሎ እየጣለ ያለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በሺህ የሚቆጠሩ ቤቶች በውሀ መከበባቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ተናግረዋል፣ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፕሮግራሞች ኮሚሽን በበኩሉ በውሀ የተከበቡ ሰዎች ወደ ደረቅ ቦታ እንዲሰፍሩ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡
በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል በደራ፣ በሊቦ ከምከምና በፎገራ ወረዳዎች በሚገኙ 9 ቀበሌዎች ከሐምሌ 20/2016 ዓ ም ጀምሮ እየጣለ ባለው ተከታታይ ዝናብ ምክንያት የጉማራና ርብ ወንዞች ከመጠን በላይ ሞልተው በመፍሰሳቸው ሜዳማ በሆኑ በነኚህ ቀበሌዎች    የሚገኙ ከ6 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተከብበዋል፣ በርካታ ሄክታር የሩዝ ሰብልም ወድሟል፡፡ እንደ አካባቢው አርስ አደሮች አስተያየት፣ በሰዎች ላይ የሞት አደጋ ባይደርስም እንስሳት በጎርፍ ተወስደዋል፣ የእንስሳቱ የግጦሽ መሬትም ደለል ለብሷል ብለዋል፡፡በሶማሌ ክልል የጎርፍ መጥለቅለቅ ፤ ድሬ ዳዋ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ተከስተዋል

የአርሶ አደሮች አስተያየት

በደራ ወረዳ የጣና ዲንቢሶ አርሶ አደር አቶ ቀኜ አለባቸው ጎርፍ ያስከተለውን ጉዳት አስመልክተው ለዶቼ ቬሌ አብራርተዋል፡፡ እንደ አቶ ቀኜ፣ ሰሞኑን የጣለውን ዝናብ ተከትሎ ከፍተኛ ጎርፍ ተከስቷል ብለዋል፡፡ የእንስሳት መኖ ወድሟል፣ የሩዝ ሰብልም በጎርፍ ተጥለቅልቋል፣ በርካታ ቤቶችም በውሀ ተከብበዋል ነው ያሉት፡፡በሊቦከምከም ወረዳ የሽናጨው ቀበሌ አርሶ አደር አቶ መልካሙ እሸቴ በበኩላቸው ጎርፉ በሰብልና በእንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱን አስረድተዋል፡፡

በደቡብ ጎንደር ዞን በውሀ የተከበበ አካባቢምስል South Gondar zone Disaster prevention Office/Alemnew Mekonnen/DW


ሌላ የሊቦከምከም ወረዳ አርሶ አደር ጎርፉ ባስከተለው መጥለቅለቅ ቤተሰቦቻቸውንና ከጉዳት የተረፈ የምግብ ቁሳቁሶችን በአልጋ ላይ ማስቀመት መገደዳቸውን በስልክ ለዶይቼ ቬሌ አመልክተዋል፡፡
ሁሉንም የእህል ዓይነቶች ጎርፍ ወስዷቸዋል፣ ውሀው አሁንም አልሸሸም፣ ወደፊትም የባሰ ችግር ይደርሳል በሚል ስጋት መኖሩን አስረድተዋል፡፡ “አልጋ ሰርተን ህፃናቱንም እህሉንም በዚ ላይ አስቀምተናል፡፡” ብለዋል፡፡ መንግስት ከአካባቢው እንዲወቱ ጥረት እያደረገ ቢሆንም ባለው ወቅታዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት ብዙዎቹ መውጣቱን እንዳልፈለጉ እኚሁ አስተያየት ሰጪ ገልጠዋል፡፡በኢትዮጵያ ከፍተኛ ዝናብ የሚጠበቅባቸው ቀጣይ ሁለት ወራት

ጎርፉ ያስከተለው ጉዳት

የደቡብ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አበባው አየነው ብሊቦ ከምከም፣ ደራና ፎገራ 9 ቀበሌዎች በጎርፍ መጎዳታቸውንና ከ6 ሺህ በላይ ቤቶች በጎርገፍ መጥለቅለቃቸውንና ከ4ሺህ 330 ሄክታር በላይ የሩዝ ሰብል በጎርፍ መውደሙን ተናግረዋል፣ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ወደ ደረቃማ ቦታዎች ለማስፈር ቦራዎች መመረጣቸውንም ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፕሮግራሞች ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል በጎርፍ የተከበቡ ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲወጡ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና አስፈላጊው ግብዓት መዘጋጀቱን አብራርተዋል።፡በመገባደድ ላይ ባለው በ2016 ዓም የክረምቱ ዝናብ ባስከተለው የተፍጥሮ አደጋ ከ275 ሰዎች ሞተዋል

በደቡብ ጎንደር ዞን በውሀ የተከበበ አካባቢምስል South Gondar zone Disaster prevention Office/Alemnew Mekonnen/DW

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አስተያየት

የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ የጎርፍ ጉዳትን ለመከላከል በዓመቱ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አስታውሰው አሁን የተከሰተውን ጎርፍ ለመቀልበስም እየተሰራ እንደሆነ ገልጠዋል፡፡

የክልሉ አደጋ መከላከል ኮሚሽን  ማሳሰቢያ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርና ሌሎችም አካባቢዎች በሚጥለው ከባድ ዝናብ የመሬት መንሸራተትና ጎርፍ መከሰቱን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፕሮግራሞች ኮሚሽን አመልክቶ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW