1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

በአሜሪካ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ ጆ ባይደን በይፋም ባይሆን ፓርቲያቸውን ተሰናበቱ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 14 2016

ካማላ ሐሪስ እና በፕሬዝዳንታዊው ምርጫ አጣማሪያቸው ቲም ዋልዝ ዕጩነታቸው በይፋ የሚታወጅበት የአሜሪካ ዴሞክራቲክ ፖርቲ ብሔራዊ ኮንግረስ እየተካሔደ ነው። በመጀመሪያው ቀን ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በይፋም ባይሆን ፓርቲያቸውን ተሰናብተዋል። በንግግራቸው ፕሬዝደንቱ ስሜታዊ ነበሩ። ለምን የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ አበበ ፈለቀ ማብራሪያ አለው።

ካማላ ሐሪስ እና ጆ ባይደን
ካማላ ሐሪስ በቀጣዩ ምርጫ ጆ ባይደንን በመተካት ይወዳደራሉምስል J. Scott Applewhite/AP Photo/picture alliance

በአሜሪካ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ ጆ ባይደን በይፋም ባይሆን ፓርቲያቸውን ተሰናበቱ

This browser does not support the audio element.

ካማላ ሐሪስ በመጪው ዓመት የሚካሔደው ምርጫ በይፋ ዕጩ መሆናቸው የሚወጅበት የዴሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ የሁለተኛ ቀን ላይ ደርሷል። በዛሬው መርሐ-ግብር የቀድሞው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

የጉባኤ የመጀመሪያ ቀን መርሐ-ግብር ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በይፋም ባይሆን ከፓርቲው የተሰናበቱበት ነው። ደፋፊዎቻቸው "ጆ እንወድሀለን" ብለው ይፋም ባይሆን ስንብት አድርገዋል። ተንታኞች እንደሚሉት ጆ ባይደን በመድረኩ ያሰሙት ንግግር ቢያንስ በዚህ ወቅት ሊያደርጉት ያቀዱት አልነበረም። ባይደን ከውድድሩ ራሳቸውን ከማግለላቸው በፊት ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን የመወዳደር ፍላጎት ነበራቸው።

 ካማላ ሐሪስ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቢመረጡ ምን አይነት ኤኮኖሚያዊ እንድምታ ይኖረዋል?

በንግግራው በምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት ሊያከናውኗቸው ቃል የገቡ ጉዳዮችን እየጠቃቀሱ የፕሬዝደንትነት ዘመናቸውን አሞጋግሰዋል። አንድ ሰዓት ገደማ በዘለቀ ንግግራቸው "እንደ ብዙዎቻችሁ ልቤን እና ነፍሴን ለዚህች ሀገር ሰጥቺያለሁ " ያሉት ባይደን በደጋፊዎቻቸው በደጋፊዎቻቸው ከፍ ባለ ድምጽ  "እናመሰግለን ጆ " ተብለዋል። 

ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በንግግራቸው ስሜታዊሆነው ታይተዋልምስል Mike Segar/REUTERS

ትላንት በመጀመሪያው ቀን ንግግር ያደረጉት ባይደን ከሺካጎ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ተመልሰዋል። ካማላ በሚቀጥለው ዓመት ለሚካሔደው ምርጫ የሚኒሶታ አገረ ገዢ ቲም ዋልዝን በአጋርነት መርጠዋል። ምርጫውን ካሸነፉ ዋልዝ ምክትል ፕሬዝደንት ይሆናሉ።

 ባይደን አሜሪካውያን ዴሞክራሲያቸውን እንዲጠብቁ ጠየቁ

በሺካጎ በመካሔድ ላይ የሚገኘውን የአሜሪካ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ኮንግረስ በተመለከተ አበበ ፈለቀ የሚከተለውን ማብራሪያ በስልክ ሰጥቷል። ሙሉውን ማብራሪያ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

አበበ ፈለቀ
እሸቴ በቀለ
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር 
      
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW