በአሮሚያ ይፈጸማል የተባለው የጅምላ እስር
ሐሙስ፣ ሰኔ 20 2016የታሰሩ የህብረተሰብ ክፍሎች መበራከት
ለደህንነታቸው ስባል ስሜ ይቆይ ብለው አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ አንድ የጊምቢ ከተማ ነዋሪ የበርካታ ታሳሪዎችን ስም ዝረዝር ጠቅሰው ብያንስ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ በጅምላ ታሰሩ ያሏቸውን የ150 ሰዎች ስም ዝርዝር መያዛቸውን አስረድተዋል፡፡ “የታሰሩ ሰዎች ከባለፈው ሃሙስ ብቻ ብንቆጥር በዚህ አንድ ሳምንት ብያንስ ከ150 በላይ ይሆናሉ፡፡ ስያስሩአቸው የሚጠይቁአቸው ልጆቻችሁ ጫካ ነው ያሉት፡፡ እነዚያን ሳታመጡአቸው አትገቡም ነው የሚሏቸው፡፡ አንድ ታጣቂ ከአከባቢው መንግስት ላይ ያመጹ የተባሉ ታጣዎች አባል መሆኑ ከተረጋገጠ አባት፣ እናት፣ እህት እና ወንድም በሙሉ ይታሰራሉ፡፡ በዚህ የሚዛመድ ባይኖር እንኳ የነዚያ የታጠቁ የተባሉ አሳዳጊም ቢሆን ያስራሉ፡፡ አሁንም እነሱን አስገቡያቸው፡፡ አለበለዚያ አትለቀቁም ነው የሚሏቸው” ብለዋል፡፡ያለሕግ አግባብ የቀጠለዉ የኦነግ አመራሮች እስ,ር
ታሳሪዎች እዲፈቱ የሚጠየቁት
አስተያየት ሰጪው እንደሚሉት ለታጣቂዎቹ ወላጆች እና ቤተሰቦች ይህን ማድረግ ቀላል አይደለም፡፡ “እነዚህ ልጆች እድሜያቸው ብያንስ 18 እና ከዚያ በላይ ነው፡፡ እንደ ህግ ሊያስጠይቃቸው ያልተገባ ነበር፡፡ ጉዳዩ ወላጆችን አስጠይቆ በእስር ላይ ሊያንገላታቸው ያልተገባ ነበር” ብለዋል፡፡
አስተያየጣቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪም በርካታ ቤተሰቦቻቸው በዚሁ ተመሳሳይ ምክንያት መታሰራቸውን አስረድተዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዋ የታሰሩትን ዘመዶቻቸውን ከመንግስት ስራ እናባርራቸዋለን የሚሉ ዛቻዎችን እንደሚደርስባቸው ገልጸዋል፡፡ የታሳሪዎችን ቁጥርም ከ300 እስከ 400 የሚደርሱ ብለዋል፡፡ “በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት፡፡ በጊምቢ 04 ቀበሌ ብቻ የታሰሩ ወደ 300 – 400 ይሆናሉ፡፡ የታሰሩም ምንም ምቹ ባልሆነ ሁኔታ፤ መጸዳጃ እንኳ ችግር በሆነበት፤ ሴት ወንዱ አንድ ላይ ነው አዳራሽ ነገር ውስጥ የታጎሩት፡፡ ልጆቻቸው ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር መሆናቸው ከታወቀ በከተማው ያለ ሰው በሙሉ አይቀርም ይታሰራል ነው የሚሉት፡፡ በጸጥታ እጦት ጉዳዩ ላይ ምንም እጃቸው የሌለ ሚስኪን ማህበረሰብ ሁላ ነው የሚሰቃየው፡፡ የተሻለ ቦታ እንኳ ብታሰሩ መልካም ነበር” ብለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡የምዕራብ ወለጋ ግድያ እንዲቆም የሲቪክ ማሕበራት ማሳሰባቸው
“የታጣቂዎች አባል የሆነው ልጃቸው መሞቱ ከተረጋገጠ ወላጆቻቸው ይለቀቃሉ”
አስተያየት ሰጪዋ በመንግስት አካላት የሚጠየቁትን ጥያቄ መመለስም ሆነ መተግበር ለወላጆች የሚቻልም አይለም ይላሉ፡፡ “የታጣቂ ቡድኑን የተቀላቀሉት ልጆች ለቤተሰቦቻቸው እንኳ አይደውሉም፡፡ ቤተሰብም ልጆቻቸው የት እንዳሉ አያውቁም፡፡ የ70-80 ዓመት አሮጊት እንኳ ታስረዋል፡፡ ከታሰሩ በኋላ አሁን ትናንት 12 ሰዎች ተለቀዋል፡፡ እነሱም የተለቀቁት ታጣቂ ቡድኑን ተቀላቅለው የነበሩ ልጆቻቸው መሞታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡ ልጆቻቸው በህይወት አለ ተብሎ ከታመነ ግን ልጆቻችሁን እስክትመልሱ ከዚህ አትወጡም ብለው በዚያው አስረውአቸዋል፡፡ አገር እንዲጠፋ ህዝብ እንዲዘረፍ የሚያደርጉ ልጆቻችሁ ስለሆነ እነሱን ከመለሳችሁ ሀገር ሰላም ይሆናል መልሱአቸው ወደ ቤት አስገቡአቸው ይሏቸዋል፡፡ ማስፈራሪያም ይደርስባቸዋል፡፡ ግን ለቤተሰብ ይህን ማድረግ ቀላል አይደለም” ብለዋል፡፡
ነዋሪዎቹ አማረው ስላነሱት ድርጊት መፈጸም አለመፈጸሙን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ለጊምቢ ከተማ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ክፍሉ ዋጋሪ የእጅ ስልካቸው ላይ ደውለን ስንጠይቃቸው ከጢቂት ደቂቃ በኋላ ብትደውሉ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እሰጣችኋለሁ ብሉም በቀጠሮያችን መሰረት መልሰን ስንደውልላቸው ስልካቸው በመዘጋቱ መልሰን ልንገኛቸው አልቻልንም፡፡በጉጂ ዞኖች ተፈጸሙ የተባሉ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች
ከጢቂት ሳምንታት በፊት በኦሮሚያ ክልል በተለይም በጉጂ አከባቢ ይፈጸማሉ ያሏቸው ሰብዓዊ ጥሰቶች ላይ የዳሰሳ ጥናት ያካሄደው የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል (ካርድ) የጅምላ እና የዘፈቀደ እስሮች በክልሉ በስፋት ይፈጸማሉ ማለቱ ይታወሳል፡፡
ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሀመድ
ፀሀይ ጫኔ