1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ኃይለኛ ንፋስ በአሶሳ ያደረሰው ጥፋት

ዓርብ፣ ሚያዝያ 7 2014

የኩርሙክ ወረዳ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ አሸናፊ ወዳጀ በወረዳው ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ የነዋሪው መኖሪያ በቶች፣የሀይማኖትና መንግስት ተቋማት መውደማቸውን ለዶቼቬለ አረጋግጠዋል፡፡ በስምንት ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ አብዛኛዎቹ የአርሶ አደር ቤቶች መፍረሳቸውንም አብራርተዋል፡፡ በአደጋው 1400 የሚደርሱ ነዋሪዎች ተጎጂ መሆናቸውንም አክለዋል፡፡

Ato Tarekegn Tasisa
ምስል፦ Negassa Desalegn /DW

ኃይለኛ ንፋስ በአሶሳ ያደረሰው ጥፋት

This browser does not support the audio element.

 

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ፣ ባምባሲና መንጌ በሚባሉ ወረዳዎች ሰሞኑን ንፋስ ቀላቅሉ በጣለው ዝናብ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ነዋረዎችና ባለስልጣናት ተናገሩ፡፡ በአደጋው በርካታ መኖሪያ ቤቶች መፍረሳቸውም ተጠቁሟል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል። እስካሁን  2300 የሚደርሱ ሰዎች ከሁሉም ስፍራ በአደጋው ሳቢያ መፈናቀላቸውንም አመልክቷል።፡ በኩርሙክ ወረዳ ብቻ 8 በሚደረሱ ቀበሌዎች ቤቶችን ማፍረሱንም ወረዳው  ገልጸዋል፡፡ በመተከል ዞን 270ሺ ለሚደርሱ ዜጎች ለ5ኛ ዙር ድጋፍ ማድረጉን ሰሞኑን የክልሉ አደጋ ስጋት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ 

የአሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሙላት ማስረሻ  በወረዳቸው በርካታ መኖሪያ ቤቶች በኃይለኛ ንፋስ  መፍረሳቸውን ለዲዳቢሊው ተናግረዋል፡፡ ከ3 መቶ በላይ ቤቶች በ7 ቀበሌዎች ውስጥ እንደፈረሱ የተናገሩት ነዋሪው ከፈሰረሱት ቤቶች በተጨማሪም በቁም እንስሳት ላይም ጉዳት መድረሱን አብራርተዋል፡፡ አስቸኳይ  ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል፡፡

የኩርሙክ ወረዳ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ አሸናፊ ወዳጀ በወረዳው  ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ የነዋሪው መኖሪያ በቶች፣የሀይማኖትና መንግስት ተቋማት መውደማቸውን ለዲዳቢሊው አረጋግጠዋል፡፡ በስምንት ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ አብዛኛዎቹ የአርሶ አደር ቤቶች መፍረሳቸውንም አብራርተዋል፡፡ የጉዳት መጠኑም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው 1400 የሚደርሱ ነዋሪዎች ተጎጂ መሆናቸውንም አክለዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ንፋስ የቀላቀለው ዝናብ በተለይም በኩርሙክ ወረዳ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ በአሶሳ ዞን ስር በሚገኙት ባምባሲና መንጌ በሚባሉ ወረዳዎችም ጉዳት ማድረሱን ገልጸው በአጠቃላይ በደረሰው ጉዳት 2ሺ የሚደርሱ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን አክለዋል፡፡ በባምባሲ ወረዳም መኖሪያ ቤቶች ጨምሮ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች  በንፋሱ ምክንያት ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ጠቁመዋል፡፡ የደረሰው ጉዳትም ከፍተኛ መሆኑንና ለሰብአዊ እርዳታ ሁሉም ድጋፍ እንዲያድርግ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ተፈናቅለው በመተከል ዞን የተለያዩ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ከ40ሺ በላይ ኩንታል እህል ድጋፍ ማድረጉንም ለዲዳቢሊው አብራርተዋል፡፡ ዜጎች በአሁኑ ጊዜ ወደ ቀአቸው ተመልሰው መኖርና በእርሻ ልማት ለመሳተፍ ለኮሚሽኑ ጥያቄዎችን እያቀረቡ እንደሚገኙ ጠቅሰው በአካባቢው የጸጥታ ሁኔታ ወደ ቀደመ ሰላም ሲመለስ ዜጎች እንዲቋቋሙ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በዞኑ የተወሰኑ ወረዳዎች ተጠልሎ የሚገኙ ነዋሪዎች ዕርዳታ እንደ ተቋረጠባቸው በተለያዩ ጊዜያት ሲገልጹ ቆይቷል፡፡

በክልሉ  ከ440ሺ በላይ በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ ዜጎች እንደሚገኙም የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው ወደ መጠለያ ጣቢያ ከሚገቡት በተጨማሪም ከአጎራባች ክልሎችም ወደ ክልሉ የሚገቡ ዜጎች መኖራቸውን የክልሉ አደጋ ስራ ስራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገልጸዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ 

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW