1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአብዛኛው ደቡብ ወሎ፣ በተወሰኑ የሰሜን ወሎ እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች ኤሌክትሪክ ተቋርጧል

ኢሳያስ ገላው
ሰኞ፣ ሚያዝያ 6 2017

በአማራ ክልል በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ በተፈጸመ ሥርቆት ደሴ፣ ኮምቦልቻ እና ወልዲያን በመሳሰሉ ከተሞች የኤሌክሪክ አገልግሎት መቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአካባቢው ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። አብዛኛው ደቡብ ወሎ እንዲሁም በተወሰኑ የሰሜን ወሎ እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች አገልግሎቱ ተቋርጧል። ፋብሪካዎች ሥራቸው ተስተጓጉሏል።

Äthiopien Diebstahl Energie Infrastruktur
በአማራ ክልል በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ በተፈጸመ ሥርቆት ደሴ፣ ኮምቦልቻ እና ወልዲያን በመሳሰሉ ከተሞች የኤሌክሪክ አገልግሎት መቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአካባቢው ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ።ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

በአብዛኛው ደቡብ ወሎ፣ በተወሰኑ የሰሜን ወሎ እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች ኤሌክትሪክ ተቋርጧል

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆት በባለፉት ሰባት ወራት ዉስጥ ብቻ 50 ሚልዮን ብር በላይ ዉድመት መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመለክታል። በአማራ ክልል ከባለፈዉ የሰሜኑ ጦርነት መገባደድ በኃላ የመብራት ኃይል ምሰሶዎችን ትኩረት ያደረገ ስርቆት ከመባባሱ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ የመብራት መቆራረጥ የፋብሪካ ባለቤቶችና በአምራች ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች የስራ መስተጓጐል እንደገጠማቸዉ ይናገራሉ።

“የመብራት ጉዳይ ሰሞኑን ዛሬ ከነጭራሹ ትናንት ከነ ጭራሹ ነዉ የጠፋዉ አሁን ነገ ካልመጣ አላዉቅም የሚመጣበት ቀን አይታወቅም አሁን ምርት ማምረት አልቻልንም የተመረተዉንም ለማሰራጨት ዉሀ ያስፈልጋል ዉሀዉም አይሰራም ከዚህ ጋር የተገናኘ ነዉ ያለ መብራት ምንም የሚሰራ የለምና ቁመናል”የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ50 ሚሊዮን ብር ንብረት ተሰረቀበት

ከትናንት ጀምሮ በተቋረጠዉ የመብራት አገልግሎት በርካታ የደቡብና ሰሜን ወሎ ከተሞች እንዲሁም ከፊል ሰሜንሸዋ አካባቢ የመብራት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆኖ በተለይም በኢንደስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ ያሉ የፋብሪካ ባለቤቶች በተደጋጋሚ መብራት መቆራረጥ ለኪሳራ መዳረጋቸዉን ይናገራሉ።

“በጣም ከፍተኛ ነዉ እኛ የምናመርተዉ ስንዴዉም ከመፈጨቱ በፊት ታጥበዋለህ ከዚያ ጎተራ ዉስጥ ታስገባዋለህ ከዚያ የሚፈለግበት ሰአት አለ ያንን ሰአት ጠብቀህ ካልፈጨህዉ ከፍተኛ ኪሳራ ነዉ ያለዉ ያዉ ለጊዜዉ ግምቱን ባልነግርህም ከፍተኛ ተፅኖ ነዉ ያለዉ”

132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የሀይል ማስተላለፊያ ምሰሶ ላይ በተፈፀመ ስርቆት የተቋረጠዉ የኤሌትሪክ አገልግሎት አሁንም ወደ አገልግሎት ባለመመለሱ  በዕለታዊ ክዋኔያቸዉ ላይ ጫና ማሳደሩን ለዶቼቨለ አስተያየታቸዉን የሰጡ ተገልጋዮች ይናገራሉ። 

በኢትዮጵያ በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆት በባለፉት ሰባት ወራት ዉስጥ ብቻ 50 ሚልዮን ብር በላይ ዉድመት መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

“በጣም ከባድ ነዉ ከዚህ በፊት መቆራረጥ ነበር አሁን ደግሞ ከጭራሹ ጠፋ መስራት አልቻልንም ልጂ አሳዳጊ ነን በኔ በኩል በጣም በጣም ነዉ ከባድ የሆነብኝ አሁን ላይ እጄ ላይ ምንም ብር የለም ምንም ሳልሰራ ነዉ የዋልኩት አሁን ቁጭ ብየ ወደ ቤት ልሄድ ነዉ”

በኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ ሪጂን 1 የትራንስሚሽን ሰብስቴሽን  ኦፕሬሽን ዳይሬክተ የሆኑት አቶ በድሩ አህመድ በኃይል ማስተላለለፊያምሰሶ ላይ በተፈፀመ ዝርፊያ በርካታ አካባቢዎችና ፋብሪካዎች ከስራ ዉጭ ሆነዋል ይላሉ።

በአማራ ክልል በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረግ ዝርፊያ መጨመር

“አሁን መብራት የተቋረጠባቸዉ ያዉ ኮምቦልቻ ሙሉ በሙሉ ነዉ 15 ኪሎ ቮልት 66 ኪሎ ቮልት ደግሞ ደሴንና ወልድያን የሚያስጠቅም ዉጫሌን መርሳን 132 ኪሎ ቮልት ወደ አቀስታ መካነ ሰላም ወግዲ ሳይንት ተንታ ወደ ወረኢሉ ሽፋን የሚሰጥ በሌላ መስመር አለም ከተማ ጃማ ሚዳ ሰሜን ሸዋ ፊጥራ የሚባሉ አሉ ምርት ታዘዉ እራሱ ምርታችን እንዳናመርት አደረጋችሁ ያሉ አሉ”

በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለዉ የኃይል ማስተላለፊያ ምሰሶዎች ላይ የሚደርስ ዝርፊያ አጥፊዎች በአግባብ የሚጠየቁበት ባለመሆኑ ስርቆቱ መቆም አልቻለም ተብሎል

መሰረተ ልማትን የሚሰርቅ ሰዉ በዋስ መብት እየተባለ ይፈታል በየአካባቢዉ ማለት ነዉእጂ ከፈንጂ እራሱ ተይዞ መሰረተ ልማትን አዉድሞይህንን ማህበረሰብ በድሎ በቀላሉ 24 ታሰሮ የሚፈታበት በዋስ በአምስት ሽህ የሚፈታበት አለ ተቋሙ ግን አሁን በሰአት ምንያህል ይህንን ሀይል ባለመሸጡ የሚያጣዉ በቢልየንስ ነዉ የሚገባዉ የህጉ ላይ ጠበቅ ማለት ያስፈልጋል”

ኢሳያስ ገላው

እሸቴ በቀለ

ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW