በአዉሮጳ ኅብረት ተቃዉሞ የገጠመዉ የአሜሪካ የ 28 ነጥብ የሰላም እቅድ
ሰኞ፣ ኅዳር 15 2018
ማስታወቂያ
በአዉሮጳ ኅብረትና ዩክሬን ተቃዉሞ የገጠመዉ የአሜሪካ የ 28 ነጥብ የሰላም እቅድ
ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሩስያ በዩክሬንየምታካሂደዉን ጦርነት ለማስቆም ያወጣችዉን ባለ 28 ነጥብ የሰላም እቅድ የአዉሮጳ ኅብረት ተቃወመዉ። ኅብረቱ የራሱ ያለዉዉን የሰላም አማራጮች ይፋ አድርጓል። በአውሮጳ ውስጥ የሚገኙ ፖለቲከኞች እና ተንታኞች የዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሪን ሰላም ያመጣል ስትል የሰላም እቅድ ስታዘጋጅ ከአውሮጳ ህብረት እና ከዩክሬን ጋር ሳትመካከር ነዉ ብለዉ ያምናሉ። ዩናይትድ ስቴትስ ከዩክሬይን ይልቅ ከሞስኮ ጋር የበለጠ ወዳጅነት እንዳላትም ይነገራሉ።
በአውሮጳ ኅብረት እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተነሱት የሰላም እቅዶች፣ ልዩነቶች እና ውዝግቦች ምንድን ናቸዉ? የአዉሮጳ ኅብረት መቀመጫ ብረስልስ ላይ የሚገኘዉን የዶቼ ቬለ ዘጋቢ ገበያዉ ንጉሴን አነጋግረናል። በሌላ በኩል 7ኛው የአውሮጳ ህብረት እና የአፍሪቃ ህብረት የሁለት ቀናት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ አንጎላ መዲና ሉዋንዳ ላይ ዛሬ ጀምሯል። ይህ ሁለቱ አህጉራት የጋራ ጉባኤ በመክፈቻዉ የአውሮጳ ህብረት እና የአፍሪቃ ህብረት አጋርነት 25ኛ ዓመትን አክብሯል።
ገበያዉ ንጉሴ / አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ