በአውሮፕላን አደጋ ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ነጻ የህግ አገልግሎት
ሐሙስ፣ መጋቢት 12 2011ማስታወቂያ
መጋቢት 1፣2011 በረራ በጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች ቤተሰቦች የህግ አገልግሎት ለመስጠት መንቀሳቀስ መጀመራቸውን አሜሪካን የሚገኝ አንድ የህግ ጉዳዮች ቢሮ እና አንድ ኢትዮጵያዊ የህግ ባለሞያ አስታወቁ። ፍሬድማን ሩቢን የተባለው የህግ ቢሮ እና ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሞያ ሼክስፒር ፈይሳ ለDW እንደተናገሩት ለሟች ቤተሰቦች ነጻ የህግ አገልግሎት ለመስጠት ነው የተስማሙት። ያነጋገራቸው የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ