1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአይሮፕላን አደጋ ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የተደረገው ጸሎት

ማክሰኞ፣ ጥር 18 2002

ትናንት ከሊባኖስ ዋና ከተማ ከቤይሩት አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሜዲቴራንያን ባህር ላይ ወድቆ በተፈጠፈጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለሞቱት ኢትዮጵያውያን ተሳፋሪዎች ሁሉ ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ስርዓተ ጸሎት ተደረገ።

ምስል AP

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብጹእ አቡነ ይስሀቅ ሌሎች ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት በተካሄደው የጸሎት ስርዓት ላይ አደጋው አሳዛኝና አስደንጋጭ መሆኑን በመግለጽ ለሟቾች ቤተሰቦች የማጽናኛ ቃል አሰምተዋል። ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ በስራ ከሚገኙባት ደቡብ አፍሪቃ የላኩት የሀዘን መግለጫ መልዕክት ተነቦዋል።

ታደሰ እንግዳው /አርያም ተክሌ/

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW