1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአዲሱ የትግራይ ጊዜያዊ ም/ቤት በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ ተሳታፊ አይደለም

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሐሙስ፣ የካቲት 27 2017

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች አካላት በመሆን በመሰረተው ምክርቤት፥ በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ እንዲሁም የትግራይ ሐይሎች ተወካዮች እየተሳተፉ አይደለም። ሙስሊሙ ማሕበረሰብ በምክርቤቱ መቀመጫ እንዲኖረው ተወስኗል።የክልሉየምክርቤቱ ምክትል አፈጉባኤ በተቻለ መጠን ሁሉ አካታች ለመሆን ተሰርቷል ብለዋል

የአዲሱ የትግራይ ጊዜያዊ ምክር ቤት ምስረታ
የአዲሱ የትግራይ ጊዜያዊ ምክር ቤት ምስረታምስል፦ Million Haileselassie/DW

በአዲሱ የትግራይ ጊዜያዊ ምክር ቤት በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ ተሳታፊ አይደለም

This browser does not support the audio element.

በትግራይ የተቋቋመው አዲሱ ግዜያዊ ምክርቤት፥ የመቀመጫ ቁጥር በመጨመር አዳዲስ አባላትን እንዲቀላቀሉ ወሰነ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክር ቤት የክልሉ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ በምክርቤቱ መቀመጫ እንዲኖራቸው የወሰነ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የመንግስት ሰራተኞች እና የንግድ ዘርፍ ማሕበራት ምክርቤቱ እንዲቀላቀሉ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል። በዚህ ምክርቤት በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ እና የትግራይ ሐይሎች ተወካዮች እየተሳተፉ አይደሉም።በትግራይ ሁሉን አካታች ምክር ቤት እንዲቋቋም ተቃዋሚው ባይቶና ጥሪ አቀረበ

መጀመርያ ላይ አማካሪ ምክርቤት ተብሎ ተመስርቶ፥ በኃላ ላይ የአዋጅ ማሻሻያ በማድረግ የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ምክርቤት የሚል ስያሜ ተሰጥቶት እየቀጠለ ያለው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ተቋማት ያከተተው ካውንስል፥ ትላንት ባካሄደው ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ የምክርቤቱ የመቀመጫ ቁጥር በመጨመር አዳዲስ አባላት እንዲካተቱ አድርጓል። ምክርቤቱ የክልሉ ንግድ ማሕበረሰብ ተወካዮች እና የመንግስት ሰራተኞች ማሕበር እንዲካተቱ ያደረገ ነው።

የአዲሱ የትግራይ ጊዜያዊ ምክር ቤት ምስረታ

 ከዚህ በተጨማሪ የትግራይ ሙስሊም ማሕበረሰብ በምክርቤቱ ውክልና እንዲኖራቸው የቀረበ ጥያቄ በ27 የድጋፍ ድምፅ፣ በ14 ተቃውሞ እና በሌላ 14 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ የሙስሊም ማሕበረሰብ ተወካዮች እንዲኖሩ ወስኗል። ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ ቅሬታዎች በማቅረብ ራሱን ከምክርቤቱ አግልሎ የነበረው ተቃዋሚው ፓርቲ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፥ ያቀረብኳቸው ማሻሻያዎች ተቀባይነት አግኝተዋል በማለት ወደ ካውንስሉ ተመልሷል። የተለያዩ የፖለቲካ ሐይሎች፣ ሲቪክ ማሕበራዊ እና ሌሎች የማሕበረሰብ ክፍሎች በማካተቱ በኩል፥ ከምክርቤቱ አባላት የተለያዩ ሐሳቦች ተሰንዝረዋል።መቋጫ ያጣው የሕወሓትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፍጥጫ

በትግራይ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሆነው ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ በበኩሉ ግልፅ ባልሆነ አሰራር በምክርቤቱ አለመካተቱ አንስቶ ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን፥ ሌሎች ሲቪክ ማሕበራት እንዲሁ በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክርቤት እንዲካተቱ ጥያቄ ቀርቧል። ለነዚህ የተለያዩ የውክልና ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የምክርቤቱ ምክትል አፈጉባኤ የሆኑት ዶክተር ደጀን መዝገበ፥ በተቻለ መጠን ሁሉ አካታች ለመሆን ተሰርቷል ብለዋል።"ካልቻሉ አሁን ከስልጣን መልቀቅ አለባቸው" ተቃዋሚዎች

በዚህ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች አካላት በመሆን የመሰረተው ምክርቤት፥ በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ እንዲሁም የትግራይ ሐይሎች ተወካዮች እየተሳተፉበት አይደለም።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW