በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ የሰዎች ህይወት ያለፈበት ግጭት
ዓርብ፣ ጥር 13 2014ማስታወቂያ
ትናንት በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ እና ኦሮሚያ ክልል ቡራዩ ከተማ አዋሳኝ አካባቢ የጥምቀት በዓል አክብረው ታቦታት ወደ መንበር የሚመልሱ ምዕመናን እና የፀጥታ ኃይሎች መኃል በተፈጠረው ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በርካቶች መጎዳታቸውን የአይን እማኞች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የሟቾቹ ቁጥር ዛሬ ሶስት መድረሱን የሚገልጹት የአይን እማኞች ምናልባትም ክፉኛ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የሟቾች ቁጥሩ ከዚህም ሊጨምር ይችላል ይላሉ። በትናንትናው እለት በፀጥታ ችግር የተስተጓጎለው የወይብላ ማሪያም ታቦታትን ከጥምቀተ ባህር ወደ መንበር የመመለስ ሂደት ዛሬ ከፍተኛ የጸጥታ ኃይሎች እና የእምነቱ ተከታይ ምዕመናን በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ የዛሬውንና የትናንቱን ሁነት ተከታትሎ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ስዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ