በአዲስ አበባ የታክሲዎች ከፊል የስራ ማቆም አድማ
ሰኞ፣ ግንቦት 8 2003ማስታወቂያ
የዛሬ ሳምንት ሰኞ የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ፤ የአዲስ አበባ ታክሲዎችን ስምሪትና የዋጋ ተመን የሚያሳይ አዲስ መመሪያ አዋጣ። መመሪያው አርብ ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ ሆነ። አርብ በተወሰነ ደረጃ ዛሬ ደግሞ ከፊል አዲስ አበባን የሸፈነ የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ተደረገ። ዘጋቢያችን ታደሰ እንግዳው ያነጋገራቸው አንዳንድ የታክሲ አሽከርካሪዎች፤ ገንዘብ ተቀባዮችና ተራ አስከባሪዎች እንደሚሉት መመሪያው ጥቂቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ ነው። ዛሬ አዲስ አበባ በከፊል ጭር ብላ ነው የዋለችው። መንግስት የተፈጠረው ችግር ጊዜያዊ ነው። ዘላቂ መህትሄ እየፈለኩለት ነው ይላል።
ታደሰ እንግዳው
መሳይ መኮንን
ሂሩት መለሰ