1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ አበባ የገና በዓል ድባብና ገበያው

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 29 2014

በአዲስ አበባ በርካቶችን በሚያሰባስበው ትልቁ የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች ገበያ በሾላ አንድ ጠና ያሉ ጎልማሳ ሰው በጎዳናው ዳር ተቀምጠው እንቁላል በሚሸጡበት ወቅት ሸማቾችን የሚጠሩበት ድምጽ ጎልቶ ይሰማል፡፡ ሸማቹም ጎራ እያለ የአቅሙን ያህል እየሸመተ ይሄዳል፡፡ ሌላ የማማረር ድምጽም ይሰማል፡፡

 Ethiopian charismas market in Addis Abeba
ምስል Seyoum Getu/DW

በአዲስ አበባ የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ የእርድ እንስሳት ዋጋ ቀንሶ ታይቷል

This browser does not support the audio element.

በአዲስ አበባ የበዓል ድባብና ገበያው

በአዲስ አበባ በዘንድሮ ገበያ በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ቅናሽ ባይስተዋልም በእርድ እንስሳት ላይ መጠነኛ ቅናሾች ማስተዋላቸውን ሸማቾችና ነጋደዎች ገለጹ፡

የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ የከተማዋን የበዓል ድባብና ገበያውን ቃኝቶ ተከታዩን ዘገባ አድርሶናል፡፡

ይህ ድምጽ በአዲስ አበባ በርካቶችን በሚያሰባስበው ትልቁ የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች ገበያ በሾላ አንድ ጠና ያሉ ጎልማሳ ሰው በጎዳናው ዳር ተቀምጠው እንቁላል በሚሸጡበት ወቅት ሸማቾችን ሚጠሩበት ነው፡፡ ሸማቹም ጎራ እያለ የአቅሙን ያህል እየሸመተ ይሄዳል፡፡ ሌላ የማማረር ድምጽም ይሰማል፡፡ ከወትሮ ንሯል የተባለው የዶሮ ዋጋ፡፡ አንድ አውራ ዶሮ ለመግዛት ከ800-1000 ብር ያስወጣል ይላሉ ሸማቾች፡፡ አለፍ አልኩኝ፡፡ በዓል አድማቂ ቄጠማ እና ሌሎች መሰል ጉዝጓዝን ይዘው የተቀመጡ እናት ተመለከትኳቸው፡፡ የዋጋ ጭማሪ የተጫጫነው ህይወት የበኣልን መንፈስ እንዳጠፋባቸው ከፊታቸውም ከንግግራቸውም ይስተጋባል፡፡

በዚያው በሾላ ገበያ በቅቤ ንግድ ላይ የተሰማራችው ሰላም ብርሃኑ ደግሞ በዚያ እንኳ ያን ያህል ጭማሪ እንደሌለው ነው የምትናገረው፡፡

በአዲስ አበባ ለበዓላት የኢንስሳት ገበያ ግዙፉ በሆነው የካራ ገበያ ተገኝቻለሁ፡፡ ለቁጥር የሚታክቱ ከመካከለኛ እስኪ ግዙፍ የቁም እንስሳት ይሸመትበታል፡፡ ለቅርጫው፣ ለሆቴሉ እንዲሁም ለግል ፕሮግራም የሚሸምቱት ከነጋዴውና አቅራቢ አርሶ አደሩ ጋር በቀንስ አልቀንስም ሲሟገቱም ይስታዋላል፡፡ አብዱ አህመድ ወደ ጎጃምና ወሎ አከባቢዎች እየተመላለሱ ሰንጋዎችን ለመዲናይቱ ከሚያቀርቡት ነጋዴ ናቸው፡፡ እኔም ስለ ዘንድሮ ገበያ እና አቅርቦቱ ጠየኳቸው፡፡ እሳቸውም ይመልሳሉ፡፡ በተለይም በወሎ በኩል የከረመው ጦርነት አቅርቦቱን በእጅጉ ጎድቶት ተስተውሏል፡፡ 

አቶ አብዱን ስለ ሰንጋ በሬዎቹ ዋጋም ጠይቄያቸዋለሁ፡፡ 

ሌላው ከጂማ እና ወለጋ አከባቢ ለእርድ የሚውሉ እንስሳትን በማምጣት ለሸማቹ ሚያቀርበው ነጋዴም ጠይቄ ተቀራራቢ ምላሽ ሰጥተውኛል፡፡ 

ሽመልስ አበባ ደግሞ አርሶ አደር ናቸው፡፡ ከለገዳዲ የእርድ ሰንጋን ቀልበው ነው ወደ ገበያው ይዘው የመጡት፡፡ የዘንድሮ ገበያ ለሻጭ አይሆንም ሲሉም አማረዋል፡፡

ከዚያ አቅራቢያ የመጡ መኮንን አበበ የተባሉ ሌላው አርሶ አደር ደግሞ ወደ እንስሳት ገበያው ብቅ ያሉት ለቅርጫ በሬ ለመግዛት ነው፡፡ 

በዘንድሮ ገበያ በነጋደውና ሸማቹ ቀንሷል የሚል ቃላት የተጠራበት ሌላው ገበያ የእርድ በጎች ገበያ ነው፡፡ ለሸመታ ወደ ገበያው ብቅ ያለው ታምራት ነጋሽ እና ከደብረ ብርሃን አካባቢ አምጥቶ በጎችን የሚሸጠው እንድሪስም ስለ በግ ገበያ ተመሳሳይ ሃሳብ ነው የሰጡኝ፡፡

ዋጋም አሁን ጋብ ብሎ መታየቱም ገበያተኞቹ ይመሰክራሉ፡፡ ሁለቱም በኪሎ 25 ብር ብቻ ያስወጣሉ ነው የሚባለው፡፡ ሲጠቃለልም መዲናይቱ አዲስ አበባ በሰሜን ኢትዮጵያው ከፍቶ በቆየው ጦርነት ማግስ ሆና በምታከብረው የመጀመሪያው ትልቅ በኣል ገና በዋዜማ ቀናቱ የትራፊክ መጨናነቁ፣ እንደ ሁል ጊዜው ባሆንም በየገበያው አላሳልፍ የሚለው ድባብ ተስተናግዶባታል፡፡ ስለዳያስፖራዎች ወደ አገር ቤት መምጣት መገናኛ ብዙሃኑ አጉልተው ማንሳታቸው እና ከተማው በሙሉ በአገሪቱ ባንድራ በየአከባቢው ማሸብረቋም ሌላው የበኣል ድባብ የጠራው ክስተት ሆኖ ተስተውሏል፡፡  

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW