1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ አበባ የገና ዋዜማ የበዓል ግብዓቶች ግብይት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2017

ነገ ማክሰኞ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ( የገና በዓል ) ይከበራል።በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ቦታዎች ባደረግነው የበዓል ግብዓቶች ግብይት ቅኝት ገበያው የአቅርቦች እጥረት እንደሌለበት ከሸማቾችና ሻጮች ሰምተናል።ለእርድ የሚሆኑ ከዶሮ እስከ ፍየል፣ ከበግ እስከ የቀንድ ከብት በስፋት የቀረበ ሲሆን የሸማች ፍላጎት መቀነሱን ግን ተገንዝበናል።

Äthiopien I Addis Abeba - Märkte, während sich Christen auf das Weihnachtsfest vorbereiten
ምስል Solomon Muchie/DW

የበዓል የገበያ ሁኔታ በአዲስ አበባ

This browser does not support the audio element.

በአዲስ አበባ የገና ዋዜማ የበዓል ግብዓቶች ግብይት 


ነገ ማክሰኞ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ( የገና በዓል ) ይከበራል።በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ቦታዎች ባደረግነው የበዓል ግብዓቶች ግብይት ቅኝት ገበያው የአቅርቦች እጥረት እንደሌለበት ከሸማቾችና ሻጮች ሰምተናል።ለእርድ የሚሆኑ ከዶሮ እስከ ፍየል፣ ከበግ እስከ የቀንድ ከብት በስፋት የቀረበ ሲሆን የሸማች ፍላጎት መቀነሱን ግን ተገንዝበናል።//

መንፈሳዊ ክብረ በዓላት ዓመት በዓመት ሲመጡ ገበያው፣ እንቅስቃሴው፣ ልውውጡ ይደራል። ለነገው የገና በዓልም ይኼው ድባብ ዛሬ ሰኞ በጉልህ ይታያል። እንደ አቅም የግብዓቶች ሸመታው ይደምቃል።ሸማቹ አምስት ሊትር ዘይትን በ1300፣ አንድ ኪሎ ግራም ሽንኩርት ከ 75 እስከ 85 ብር፣ አንድ ፍሬ እንቁላል ከ11 ብር ጀምሮ በዛሬው የዋዜማ ግብይት ሲገበያይ ተመልክተናል።

"ሽንኩርት ከ 75 ጀምሮ እየሸጥን ነው" ብሏል አንድ ለገጣፎ መውጫ አካባቢ ያነጋገርነው ነጋዴ።ጠጅ፣ ማር እና መሰል የባሕል መጠጦችን የሚቸረችረው ወጣት ነጋዴ ሸማቹ አቅም ያጠረው ስለመሆኑ ነግሮናል።

"ሽንኩርት ከ 75 ጀምሮ እየሸጥን ነው" ብሏል አንድ ለገጣፎ መውጫ አካባቢ ያነጋገርነው ነጋዴምስል Solomon Muchie/DW

በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና፤ የበዓል ገበያን ማረጋጋት

"የማር ጠጅ አለ፣ ማር አለ፣ የጣዝማ ማር አለ። ዋጋው  ተመጣጣኝ ነው። የኑሮ ውድነቱ ስላለ ብዙም አይደለም" [ግብይቱ]። 

ዶሮ እና ክብረ በዓላት አይነጣጠሉም። የውጭ ዝርያ ያለው ዶሮ በሾላ እና አባዶ ገበያዎች ከ 400 እስከ 500 ብር፣ የሐበሻው ደግሞ ከ900 እስከ 1500 ብር ይሸጣሉ። ቅቤና አይቡም ቢሆን ውስን የዋጋ ጭማሪ ታይቶበታል። "ለጋው ቅቤ 950፣ መካከለኛው 850፣ በሳል 800፣ ቆጮ 200 ብር" ይሸጣል። ብላናለች ሾላ ገበያ ውስጥ ያገኘናት ነጋዴ።

የዋጋ ውድነት የተጫነው የበዓል ገበያ

የካ የቁም እንሥሳት ግብይት ማዕከል ዛሬ ተቀዛቅዞ ነው የዋለው። አርብ ዕለት ግን ጥሩ ሥጋ ያላቸው በሬዎች ማዕከሉን ሞልተውት እንደነበር ከሻጭ ነጋዴዎች አንደኛው ነግሮናል። "ግብይት ዛሬ ውድም አይደለም፣ ርካሽም አይደለም። መካከለኛ ነው"። ከፍተኛ እስከ 300 ሺህ፣ ዝቅተኛ እስከ 45 ሺህ አለ"። እንደ ምልከታችን ከሆነ የፍየልና የበግ አቅርቦቱ ሰፊ ነው።  በዚያው መጠን ግን ገዢው ሸማች እጅ ያጠረው ይመስላል።

የካ የቁም እንሥሳት ግብይት ማዕከል ዛሬ ተቀዛቅዞ ነው የዋለውምስል Solomon Muchie/DW

"አቅርቦቱ ነፍ ነው። አለ። ገብቷል። በአራቱም ማዕዘን ይገባል። ትንሽ ሰዉ አቅም ያጣ ይመስላል። ለምሳሌ ፍየል እስከ 25 ሺህ ብር አለ። ትንሽ ጠቦት እስከ 8 ሺህ። በግ ደግሞ ከ 7 ሺህ እስከ 20 ሺህ ብር አለ"።በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ሥፍራ ተሰጥቶት የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት - የገና በዓል ከመንፈሳዊ ዋጋው በተጨማሪ ከፍተኛ የንግድ ልውውጥ ምንጭ የሆነም ጭምር ነው።የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዓሉ "ያለምንም የፀጥታ ሥጋት እንዲከበር የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር የሚያስችል በቂ ዝግጅት" ማድረጉን ዛሬ አስታውቋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW