1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአፅዋማት የታጠረው የዘንድሮው አዲስ ዓመት መግቢያ

ዓርብ፣ መስከረም 3 2017

የዘንድሮ አዲስ ዓመት በፆም ቀን መዋሉ በተለይ የኦርቶዶክስ ክርስትና በሚከተሉ አማኞች ዘንድ በዓሉን አንድ ወት በሆነ የእርድ ስነስርዓት ለመፈፀም አላስቻላቸውም። አንዳንዶቹ በዋዜማው እርድ ሲያከናውኑ፣ ሌሎች ደግሞ በበዓሉ ቀጣይ ቀን ዛሬ እርድ ፈፅመዋል፣ ብዙዎቹ ደግሞ ከቅዳሜ ጀምሮ እርድ ለማከናወን ቀጠሮ የያዙ ናቸው።

የቁም እንስሳት ገበያ
በዓል ሲቃረብ በኢትዮጵያ ገበያ የቀንድ ከብቶች፣ የበግ እና የዶሮ ዋጋ ጭማሪ ያሳያልምስል Solomon Muche/DW

በአፅዋማት የታጠረው የዘንድሮው አዲስ ዓመት መግቢያ

This browser does not support the audio element.

አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በዓላትን በእርድ ነው የሚቀበሉት፡፡ የዚህ ዓመት አዲስ ዓመት መግቢያ የዋለው በእለተ ረቡዕ ነው፡፡ ይህ ቀን ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አማኞች ዘንድ የፆም እለት በመሆኑ እርድ ለማከናወን አላስቻለም፡፡

ቀጣዩ እለት ሐሙስ የፍስክ ቀን ቢሆንም 3ኛው ቀን አርብ በመሆኑ  የ2017 ዓ ም አዲስ ዓመት በዓል ለእርድ አልተመችም ይላሉ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንድ የሐይማኖት መምህር እንደዚህ ዓይነት አጋጣሚዎች  አልፎ አልፎ እንደሚከሰቱ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም አንዳንዶቹ የ2017 ዓ ም መግቢያን ቀድመው በዋዜማው በእርድ የተቀበሉት ሲሆን ሌሎች ደግሞ ዛሬን መርጠዋል፣ ቀጣዩ ቀን አርብ መሆኑ ያልተመቻቸው ደግሞ ከቅዳሜ ጀምሮ እርድ ለማከናወን ቀጠሮ የያዙ ናቸው፡፡ በመሆኑም አንዳንዶቹ እለቱን “ለእርድ ያልተሰበሰበና የተበተነ” ሲሉ ጠርተውታል፡፡

በኦሮሚያ የጸጥታ ፈተና ባለባቸው አከባቢዎች የበዓል ይዞታ

አንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ በሰጡት አስተያየት በዓሉ በፆም ቀን መዋሉ እንግዳ ለማስተናገድ እንኳ አይመችም ሲሉ ገልፀውታል፡፡ እኚህ አስተያየት ሰጪ በበዓል ወቅት እርድ ደስታን እንደሚሰጥ ተናግረዋል በበዓል ጊዜ ፣ “እንግዳ ሲመጣብህም ሽሮ ከምታቀርብ ስጋ ጠባብሰህ ብታቀርብ ደስ ይላል፡፡ ” ነው ያሉት፡፡ ትናንት እንግዶች እንደነበሩባቸው የነገሩን እኚህ አስተያየት ሰጪ በዚህ ወቅት ሽሮ መጋበዝ ምቾት እንደማሰጥ ተናግረዋል፡፡ በዓሉን ለማድቅ በዓሉ በፍስክ ቀን ቢሆን ተመራጭ ይሆን እንደነበር አስረድተዋለል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ገና ለእርድ የሚሆን በግም ሆነ ፍየል ያልገዙ ናቸው ቀጣዩን ቅዳሜ በመጠበቅ ብለዋል እኚሁ አስተያየት ሰጪ አንድ የደሴ ከተማ ነዋሪ በሰጡን አስተያየት አብዛኛው ሰው የእርድ ስነ ስርዓት በዋዜማው ማክሰኞ እለት ማከናወኑን አመልክተው፣ ሌሎች ደግሞ ቅዳሜን እየጠበቁ እንደሆነ ገልጠዋል፡፡

በዓላት ሲከበሩ ኢትዮጵያውያን እንደ አቅማቸው ዶሮ፣ በግ እና በሬ ያርዳሉ፤ አሊያም በቅርጫ ሥጋ ይካፈላሉምስል Alemnew Mekonnen/DW

በዓሉ ረቡዕ ስለነበር ሐሙስ እርድ እንደሚከናወን አመልክተው፣ አንዳንድ ሰዎች ሐሙስ በሁለቱ አፅዋማት መካከል በመሆኑ እንደማመቻቸው በመጠቆም ብዙዎች እርድ ወደ ቅዳሜ አዙረውታል ሌሎች በርከት ሉት ደግሞ በበዓሉ ዋዜማ ማክሰኞ እረድ ፈፅመዋል ነው ያሉት፡፡

የአዲስ ዓመት የበዓል የሥጋ ተዋጽዖ ግብይት በአዲስ አበባ

ሌላ አስተያየት ሰጪ “መጽሐፍ የሚለው ለፆም አድሉ ነው” ሲሉ ይገልፁና እርድን በተመለከተ ግለሰቦች በፈለጉበት የፍስክ ቀን ማረድ እንደሚችሉ ተናግረዋል፣ የዚህ ዓመት በዓል የዋለው በአፅዋማት መካከል በመሆኑ ሰዎች በተከታታይ ቀናት ስጋን ለመመገብ ምናልባት ለእርድ ቀዳሜን ምርጫቸው ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ “ከፆም ቀናት ወጪ በዚህ ቀን እረድ፣ በዚህ ቀን አትረድ” የሚል ነገር እንደሌለም ገልጠዋል፡፡

አዲስ ዓመት በፆም ቀናት ለምን እንደሚውሉ የሐይማኖት አባት አስተያየት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባኪ ወንጌልና በክብራን ቅዱስ ገብረኤል የአብሻክር ተማሪ፣ መምህርምህረት አብ መራቸው ለዶቼ ቬሌ እንዳሉት የዚህ ዓይነት አጋጣሚዎች በየ76 ዓመቱ 11 ጊዜ በዓሉ  አርብ ወይም ረቡዕ ይውላል፡፡

ሥጋ መመገቡ ሳሰሆን ዋናው ቁም ነገር መፀለይ፣ አምላክ ዓመቱን ሰላም እንዲያደርገው መለመንና ዓመቱ የበረከት ጊዜ እንዲሆን መጠየቅ ነው ብለዋል መምህር ምህረት አብ፡፡

ዓለምነው መኮንን
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW