1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአፋር ክልል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

ቅዳሜ፣ ጥር 24 2017

ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ምሽት በአፋር ክልል ኤሊዳዓር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ስምንት ሰዎች መሞታቸውንና በርካቶች ቆስለዉ ዱብቲ ሆስፒታል መግባታቸዉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአካባቢዉ የጎሳ አስተዳዳሪ ልጂ የሆነዉ ሀመዱ አሊ ጀዋር የመጀመሪያው የድሮች ጥቃት ረቡዕ ምሽት 12 ሰዓት መፈጸሙን ገልጿል።

Ukraine-Krieg - Krieg der Drohnen | Kampfdrohne im Iran
ምስል፦ Iranian Army Office/Zuma/picture alliance

በአፋር ክልል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል

This browser does not support the audio element.

ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ምሽት በአፋር ክልል ኤሊዳዓር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ስምንት ሰዎች መሞታቸውንና በርካቶች ቆስለዉ ዱብቲ ሆስፒታል መግባታቸዉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።   የአካባቢዉ የጎሳ አስተዳዳሪ ልጂ የሆነዉ ሀመዱ አሊ ጀዋር የመጀመሪያው የድሮች ጥቃት  ምሽት 12 ሰዓት መፈጸሙን ገልጿል።

´´ ሰዎቹ የተጎዱት ከትናንትናዉ ቀደም ያለ ቀን ላይ ነዉ ምሽት 12 ሊሆን ፀሀይ ልትገባ የሶላት ዑዱ በሚያደርጉበት አካባቢ ሰዓት ላይ ነዉ በድንገት መጥታ ድሮኗ ተኩሳ ሦስት ሰዎች ገድላ ሄደች´´በአማራ ክልል የቀጠለዉ የድሮን ጥቃት

በዕለቱ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል የሚሉት አቶ ሀማዱ አሊ በመጀመሪያዉ ጥቃት የሞቱ ሦስት ሰዎችን ሊቀብሩ በተሠበሰቡ ሠዎች ላይ ከምሽቱ 4 ሰዓት በተወሰደዉ ሁለተኛ ጥቃት 5 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል ይላሉ

´´ማታ አራት ሰዓት ላይ የነዛ ሰዎች ቀብር የሚፈፀምበት ቦታ  ላይ ማለት ነዉ ቀጥታ መታች አምስቱ ወዲያዉኑ ህይወታቸዉ አለፈ አምስቱን ከድምበር አንድ ሁለት ኪሎ ሜትር አምጥተን መንገድ የሚገባበት ባጃጅ  ጠርተን ሆስፒታል አስገብተናል ዱብቲ ሆስፒታል ነዉ ያሉት´´

ድሮኖች በስቪሎች ላይ እያደረሱት ያለውን ጥቃት

በአካባቢዉ በጂቡቲ መንግስት ተደጋጋሚ ጥቃት ስለመፈፀሙ

ይህን መሰል ጥቃት በተደጋጋሚ በአካባቢው በጅቡቲ መንግስት መከላክያ ሰራዊት ይፈፀምብናል የሚሉት የአካባቢዉ ኗሪ እስሜኤል አሊ በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች የስጋ ዘመድ መሆናቸውን ገልጸዋል።

´´ይህ ችግር በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለ ችግር ነዉ አዲስ አይደለም ከዛሬ ስድስት ወር ገደማ ድንበር ጥሰዉ ገብተዉ በኤሊዳዐር ወረዳ ኤሊዳር ቀበሌ አርዳ የሚባል ጣቢያ  ድረስ መጥተዉ የጂቡቲ መከላክያ ሰራዊት የበርካታ ንፁሃን ኗሪዎችን መኖሪያ ቤት አቃጥለዉ ጉዳት አድርሰዉ ወጥተዉ ከድንበር ሄደዋል ማታ ሁለት ጊዜ ነዉ የድሮን ጥቃት የተፈፀመዉ በዚህም ጥቃት በመጀመሪያ ሦስት ተገደሉ እነዛን ሰዎች ለመቅበር በቀብር ስነስርአት የነበሩ ዜጎች ላይ መልሰዉ በፈፀሙት ጥቃት  በድምሩ 8 ንፁሀን አርብቷደር ዜጎች ተገድለዋል ማህበረሰቡ የኔም ነዉ ችግሩንም በቅርበት የማዉቅ የሞቱትም የኔ የስጋ ዘመዶቼ ናቸዉ´´

በጂቡቲ እና ኢትዮጵያ ድንበር መካከል የምትገኘዉ ሲያሩ ቀበሌ ያሉ አርብቶ አደሮች በተደጋጋሚ ለግጦሽ ፍለጋ በድንበር አካባቢ ይንቀሳቀሳሉ የሚሉት አስተያየት ሰጭ ይህ አሁን የተወሰደዉ የድሮን ጥቃት አስደንጋጭ ነዉ በማለት ይናገራሉ

´´ለግጦሽ ፍለጋ እነዚያም ወደዚያ ይሄዳሉ እነሱም ይመጣሉ አንድም ቀን የጂቡቲ መንግስት ከከተማ ወጥቶ የሚያዉቅ መንግስት አይደለም አሁን ሦስት ጊዜ ነዉ የድሮን ጥቃት የተደረገዉ በአንድ ሌሊት ´´

ሰሜን ሸዋ ዞን ቀዎትና ሞላሌ ወረዳዎች በድሮን በተከፈተ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ

የጂቡቲ መንግስትን የሚቃወሙ ታጣቂዎች በአካባቢዉ መንቀሳቀስ

ለደህንነታቸው ሲባል ሰማቸዉ እንዳይገለፅ የፈለጉ አስተያየት ሰጭም በአካባቢው የጂቡቲ መንግስትን የሚቃወሙ ታጣቂዎች ስለሚንቀሳቀሱ ጥቃቱ ለነሱ የተደረገ ሣይሆን አይቀርም በማለት ይገልፃሉ ሌሎች ደግሞ በአካባቢዉን ማዕድን ለመጠቀም ካለ ፍላጎት የመጣ ነዉ ይላሉ።

´´የነርሱ የራሳቸዉን አማፂ ነዉ የሚሉት እዛዉ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ድንበር ስለሆነ የሁለታችንም ድንበር ነዉ ለማምለጥ ለመግባት ይመቻቸዋል ፍሪጅ ነዉ የሚሏቸዉ የሚጠሩበት ስም ያዉ በኛ አማፂ ነዉ የምንለዉ እና ይወጣሉ ይገባሉ በዚያ አካባቢ´´ ´´ ማዕድን አለ አከል የሚባል አካባቢና እዛ ያሉ የነርሱ ታጣቂዎች ስላሉ እነዛን ፍለጋ በማለት ነዉ ነገሩን የሚፈፅሙት እነዛን ተቃዋሚዎች ፍለጋ ብለዉ ነዉ ጥቃት የሚያደርሱት  ´´

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜም በጉዳዮ ላይ በኢትዮጵያ ሆነ በጂቡቲ መንግስት የተባለ ነገር የለም።

ኢሳያስ ገላው

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW