1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሰው የአብዴን አቤቱታ

ሐሙስ፣ ሰኔ 3 2013

በአፋር ብሔራዊ ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ የሚንቀሳቀሰው የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ምርጫ አስፈፀሚዎች በአካባቢው የሌሉና ዕድሜያቸው ለመምረጥ ያልደረሰ ሕጻናትን በመራጭነት መዝግቧል ሲል ከሰሰ። ጉዳዩን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢያቀርቡም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ ፓርቲው አመልክቷ። የክልሉ ምርጫ ቦርድ ኃላፊ ቅሬታው አልደረሰኝም ይላል። 

Karte Äthiopien englisch

የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አቤቱታ

This browser does not support the audio element.

የአብዴን ሊቀመንበር አቶ ሀሰን መሀመድ ሰሞኑን ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት በአፋር ብሔራዊ ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ ያሉ የምርጫ አስፈፃሚዎች በልዩ ወረዳው ገዢ ፓርቲ ግፊት ከአካባቢ በለቀቁ፣ በሕይወት በሌሉና ዕድሜያቸው ለምርጫ  ባልደረሱ ሕጻናት ስም የምርጫ ካርድም እንዲወጣ አድርገዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክተው 10 ገፅ ማመልከቻ ግንቦት 18/2013 ዓ ም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢያስገቡም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኙ ነው አቶ ሀሰን የተናገሩት። ሁኔታው እልባት ካላገኘ ከምርጫው ለመውጣት እንደሚገደዱም አመልክተዋል። በአፋር ብሔራዊ  ክልል የአርጎባ ልዩ ወረዳ ገዢ ፓርቲ፣ የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አህዴድ) ሊቀመንበር አቶ አሊ ዘይኑ ተጠይቀው በጥቅሉ ድርጊቱ እንዳልተፈፀመና ዝርዝርና የተደራጀ ምላሽ የሚሰጡት ግን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንደሆነ በስልክ አስረድተዋል። የአፋር በየሄራዊ ክልል ምርጫ ቦርድ ኃላፊ አቶ ጣሀ አሊ የቅሬታ ሪፖርቱ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል፡፡ የአገር አቀፍ ፖለካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር አብዱልቃድር አደም በበኩላቸው አብዴን ያቀረበው ክስ ከመራጮች ጋር የተያያዘ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ጉዳዩን በዋናነት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚፈታው መሆኑን ነው የገለፁት፡፡ አርጎባ ብሔረሰብ በአፋርና በአማራ ክልሎች በሁለት ልዩ ወረዳዎች ይተዳደራል፡፡

ዓለምነው መኮንን 

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW