1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በአፍሪቃ የግብርና ምርት እንዲጨምር አፍሪቃ ህብረት አሳሰበ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 16 2014

አጀንዳዎችን ለማሳካት፣ የፈጠራ ችሎታ ካላቸው መንግሥታት፣ የንግድ እና የሥነ ጥበብ ሰዎች ጋር ተባባሪ መሆን ያስፈልገናል። በስሪላንካ እንዳየነው፣ ዜጎች ምግብ ካጡ እና ከተራቡ፣ አስተማማኝ የሆነ ነገር ሲያጡ እና ተስፋ ሲቆርጡ ሰላም እና ደህንነት ሊኖር አይችልም።

Äquatorialguinea AU Treffen in Malabo
ምስል፦ AFP/Getty Images

የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ ያስፈልጋል

This browser does not support the audio element.

በዛምቢያ መዲና ሉሳካ ለአራት ቀናት የተካሄደዉ እና ባለፈዉ እሁድ የተጠቃለለዉ  41ኛው የአፍሪቃ ህብረት ስብሰባ የአህጉሪቱ የምግብ ዋስትና ዋና አጀንዳ ነበር። በአፍሪቃ አህጉር የተመጣጠነ ምግብን የመቋቋም ችሎታ መገንባት በሚል ርዕስ  ስር፤ ጉባዔዉ የሰብዓዊ ካፒታልን እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብሎም አካባቢያዊ አሠራሮችን ማፋጠን በአህጉሪቱ ቀጣይነት ያላቸው የምግብ ችግሮችን አጉልቶ ያሳየ ነበር።

በአፍሪቃ ቀንድ ለከታታይ ሦስት ዓመታት የተከሰተዉ የዝናብ እጦት እና ድርቅ፣ በጎርጎረሳዉያኑ 2020 የተከሰተዉ የአንበጣ መንጋ፣ በኢትዮጵያ የትግራይ ግጭት፣ የCOVID-19 ወረርሽኝ ኢኮኖሚያዊ ቀዉስ፣ እና በዩክሬን የተከሰተው ጦርነት፣ በአፍሪቃየምግብ ሥርዓት ላይ ጫና እያሳደሩ ጉዳዮች ናቸዉ፤ በመሆናቸዉ የአፍሪቃ ህብረት በስብሰባዉ የተመለከታቸዉ ነጥቦ ናቸዉ።

ምስል፦ Salim Dawood/AFP/Getty Images

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደገለጸው ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረረቧ በፊት ማለትም በጎርጎረሳዉያኑ 2021 በአፍሪቃ 278 ሚልዮን ያህል ህዝብ በቂ ምግብ አያገኙም ነበር ። የአፍሪቃ ህብረት የግብርና የኤኮኖሚ እና ዘላቂ ልማት ኮሚሽነር አምባሳደር ጆሴፋ ሳኮ በስብሰባዉ ላይ በዓለም ላይ ያለውን የምግብ ዋስትና ሁኔታ አስከፊ ሲሉ ገልፀዉታል።

«በ2021 በኮቪድ 19 ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ በረሃብ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 828 ሚሊዮን ከፍ ብሏል ። የኮቪድ ወረርሽኝ መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ በዓለማችን የረሃብተኛዉ ቁጥር ወደ 150 ሚሊዮን ገደማ ጨምሯል።  በዓለም ላይ ከፍተኛ የሚባሉት የጥራጥሪ ፣ ነዳጅና ማዳበሪያ አምራች ሁለት ሃገራት ጦርነት መግጠማቸዉ ሌላዉ ችግር ነዉ። በአሁኑ ወቅት እየተጋፈጥን ያለነዉ የዩክሬኑን ጦርነት ዳፋ ነዉ። አህጉራችን በዉጭ ምርቶች ላይ ጥገኛ እንደሆነ እናውቃለን። የአፍሪቃ ህብረት እንደመሆናችን እና ይህ  የምንፈለግነው አጀንዳ ከሆነ፣ እራሳችን ለራሳችን ለማምረት መነሳት አለብን ። ይህን ለማድረግ ሁሉ ነገር አለን። ስለዚህም ከዉጭ ምግብ ማስገባታችን ልናቆም ይገባል።»

የአፍሪቃ ህብረት ስብሰባን ያስተናገደችው ዛምቢያ ሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት የምግብ አለመረጋጋትን ለመዋጋት የግብርና ምርታማነትን እንዲያሳድጉ ጠይቃለች። የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃኬይንዴ ሂቺሌማ ሃገራት የአህጉሩን የእርሻ አቅም ወደ ዕድገት በመቀየር ረሃብንና የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለማስወገድ የሚያደርጉትን ጥረት እንዲፋጥኑ  አሳስበዋል። ሂቺሌማ ለልዑካኑ "ከዝናባማው ወቅት ባሻገር የአገሮቻችን ምግብ የማምረት ችሎታችን  እንድናሻሽል ማድረግ አለብን" ብለዋል። «ይህ ማለት የመስኖ አገልግሎት  ተገቢ በሆነ ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ ማለት ነው፤ በአገሮቻችንና በአህጉራችን ያለውን የዉኃ ሃብት ወደ ከፍተኛ መጠን መጠቀም ማለት ነው።» ሲሉ ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት የተመረጡትና ከቀድሞው የዛምብያ መንግሥት 17.3 ቢሊዮን ዶላር ያገኙት ሂቺሌማ፤ ሃገራቸዉ የምግብ እጥረትን ለመዋጋት በሚደረገዉ ዓለማቀፍ ትግል ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለማድረግ ማቀድዋን ተናግረዋል። እንደ አብዛኞቹ የአፍሪቃ አገሮች ሁሉ የዛምቢያ ኢኮኖሚም በአብዛኛው በግብርናና በግብርና ገበያ ላይ የተመሰረተ ነው። እንደ የዓለም ባንክ ገለጻ፣ የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት 20% ገደማ እና ወደ ውጭ ከሚላከው ገቢ ውስጥ 12% ያህሉ  በግብርና ምርት ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነዉ።

ከዚህም በተጨማሪ ከዛምቢያ ሠራተኞች መካከል ወደ 70 በመቶ የሚጠጋው በግብርናዉ ዘርፍ በመቀጠር በገጠራማ አካባቢዎች ለሚኖሩ አብዛኞቹ ሰዎች ዋነኛ የገቢ ምንጭ ሆኗል። በዛምቢያ መዲና ሉሳካ በተካሄደዉ ስብሰባ ላይ የቀድሞዎቹና የወቅቶቹ የአፍሪቃ መንግሥት መሪዎች እና ታዋቂ አፍሪቃዉያንን ጨምሮ ምዕራብ አፍሪቃዊ አባት ያላቸዉ ብሪታንያዊዉ የፊልም ተዋናይ ኢድሪስ ኤልባ ንግግር አድርገዋል። 

የቀድሞዉ የምግብ ዋስትና ተሟጋች ብሪታንያዊዉ የፊልም ተዋናይ ኢድሪስ ኤልባ "እኔ በጣም ኩሩ የአፍሪቃ ልጅ ነኝ" ሲሉ ኤልባ በቪዲዮ አማካኝነት ስብሰባዉ ላይ ንግግር ያደረጉት። 

«በእነዚህ ጊዜያት አጀንዳዎችን ለማሳካት፣ የፈጠራ ችሎታ ካላቸው መንግሥታት፣ የንግድ እና የሥነ ጥበብ ሰዎች  ጋር ተባባሪ መሆን ያስፈልገናል ብዬ አስባለሁ። በስሪላንካ እንዳየነው፣ ዜጎች ምግብ ካጡ እና ከተራቡ፣ አስተማማኝ የሆነ ነገር ሲያጡ እና ተስፋ ሲቆርጡ ሰላም እና ደህንነት ሊኖር አይችልም።»

ምስል፦ AFP/Getty Images

የወቅቱ የአፍሪቃ ህብረት ፕሬዝዳንት የሆኑት የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሪዎቹ የአፍሪቃ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ክልልን (AfCFTA) የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ክልል ተግባራዊነት እውን እንዲሆን እና ንግድን ለማስፋፋትና ውህደትን ለማጎልበት መስማማታቸዉን ገልፀዋል። ማኪ ሳል ከዚህ በተጨማሪ የህብረቱ አባል ሀገራት የኢንዱስትሪ መስፋፋትን በማጎልበት የውህደት ሂደቱን እንዲያፋጥኑና በጥሬ እቃዎች ላይ እሴት እንዲጨመር ጥሪ አቅርበዋል።

ሉሳካ ዛምቢያ የተካሄደዉ የህብረቱ ስብሰባ አፍሪቃ እንደ ሌላው የዓለም ክፍል ሁሉ በርካታ ቀውሶች በገጠሟት ወቅት የተካሄደ በመሆኑ በከባቢ አየር ንብረት ለውጥ፣ የኮቪድ ተኅዋሲ ስርጭትን መግታት፣ብሎም ለረሃብና ግጭት መፍትሄ ማግኘት የሚሉት ርዕሶች ህብረቱ በዋናነት የተነጋገረባቸዉ ጉዳዮች ነበሩ። በሌላ በኩል ተሰብሳቢዎቹ በዩክሬን እተካሄደ ያለው ጦርነት እና መሪዎች ወደፊት ስለሚከተሉት መንገድ እንዲያስቡበት የተለያዩ ሃሳቦች የቀረቡበት መድረክም ነበር። 

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW