ትኩረት በአፍሪካ፤ በአፍሪካ ሰላም የማስከበር ተግዳሮቶች፤ ህገወጥ የነዳጅ ንግድ በናይጀሪያ
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 19 2017
በአፍሪካ ሰላም የማስከበር ተግዳሮቶች
የጎረጎሳውያኑ 2024 አመት ለአፍሪካ ባብዛኛው የግጭትና ጦርነት ግዜ ሆኖ ነው ያለፈው። በምራብ አፍሪካ በተለይ በሳህል አካባቢ፤ በመካከለኛው አፍሪካና በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በሱዳን ደም አፋሳሽ ጦርነቶችና ግጭቶች ሲካሂዱ ነው የቆዩትና አሁንም እየተከሂዱ ያሉት። ግጭቶቹን ለማስቆምና ሰላም ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶችም አንድም አናሳ ናቸው ወይንም ደግሞ ዘላቂነታቸው አስተማማኝ ያልሆኑኑና መረጋጋትን ለማስፈን ያቃታቸው ናቸው። የዶቼቬሌዋ ማርቲና ስክዊኮስኪ የጠመንጃ ላንቃ ከተዘጋ ወይንም የተኩስ ማቆም ስምምነት ከተደረገ በኋላ የሚፈጠረውን ሰላም ለማጽናት ያሉ ተግዳሮችን ዘርዝር አድርጋ ጽፋ ለዶቼቭለ አቅርባለች።
የተለመዱት የሰላም ማስከበሪያ ዘዴዎች ውጤታማ አለመሆን
ማርቲና ስክዊኮስኪ በዘገባዋ በአፍርካ በሚካሄዱ ግጭቶች የተኩስ ማቆም ስምምነት ተደርጎም እንኳ ሰላምን ማሰፈንና ማጽናት ቀላል አለመሆኑን በደቡብ አፍርካ የደህንነት ጥናት ተቋም በእንግሊዝኛ ምህጻሩ አይ ኤሴ ኤስ ዳይሬክተር የሆኑትን ሚስተር ጃኪ ሲልየርን ጠቅሳ አስነብባለች። “ ነባሮቹ የሰላም ማስከበሪያ ዘዴዎችና ሺምግልናዎች ውጤት እያስገኙ አለመሆናቸው ተረጋግጧል” ማለታቸውን በመጥቀስ ፤ አፍሪካውያን ምንም እንኳ በሰላም ማስከበር ጥረትና ግጭት አፈታት ሂደት አለማቀፉ ማህብረሰብ ሚና ቢኖረውም እራሳቸው አፍርካውያን ሀላፊነቱን መውሰድ ያለባቸው መሆኑን ማስገንዘባቸውን አንስታለች።
የሰላም ማስከበር ስልቶች ዉጤታማ ያልሆኑባቸው ምክንያቶች
ጸሀፊዋ የሰላም ማስከበሩ ስራ ለምን ውጤማ ሊሆን እንዳልቻለም ባለሙያዎችን አነጋግራና በጽሁፋዋ ጠቅሳ አስፍራለች። የተለያዩ ፍላጎቶች መኖር ብቻ ሳይሆን ፍላጎቶቹን ማቀራረብ አለመቻሉ አንዱና ዋናው ተግዳሮት እንደሆነ በመጥቀስም ለምሳሌ በቅርብ አመታት በማሊ፣ ቻድ ሱዳን ቡርኪና ፋሶንና ጊኒ የወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት መደረጉንና በኢትዮጵያ፣ የመካከለኛው አፍርካ ሪፑብሊክና ጊኒ ቢሳዎ ደግሞ መንግስት የመለወጥ ፍላጎቶች እንደነበሩሩ፤ በሁሉም፤ ግን ግጭቶቹ እንዳይፈጠሩ ወይም በግዜ እንዲቆሙና ሰላም እንዲፈጠር ያልተቻለው በፍላጎቶች መብዛትና ማቀራረብ አለመቻል ምክንያት እንደሆነ አጽናኦት ሰታ ገልጻለች። በመሆኑም እንደጸሀፊዋ አስተያየት አንዱና ዋናው የሰላም ማስከበር ፈተና የግጭት ተዋንያኑ መብዛት ብቻ ሳይሆን የፍላጎታቸው ሊቀራረብ አለመቻሉ ነው። ። ሰላም የአንድ አካል ጥረት ብቻ ሳይሆን የበርካታ የአካባቢ፤ ብሄራዊ፤ ውስጣዊና ውጫዊ አካላት መስተጋብርና ተሳትፎ ውጤት ነው የምትለው ማርቲና ፤ የእነዚህ ፍላጎቶች መቀራረብ አለመቻል የሰላም ማስከበር ሂደት ትልቁ ፈተና ነው ።በጸሀፊዋ አስተያየት በአፍሪካ ቀንድ አገሮች መካከል ያሉ ውጥረቶችም ከአካቢያዊ ውዝግቦችና ውስጣዊ ቅራኔዎች የሚመነጩ ናቸው። በሱዳን ከአንድ አመት በላይ የዘለቀውና ሚሊዮኖችን አፈናቅሎ አገሪቱንን እያወደመ ያለው ጦርነት ሊቆም ያልቻለውም በዚሁ የተዋኒያኑ ፍላጎት አለመቀራረብ መሆኑን ማርቲና አክላ ገልጻለች።፡ በግጭት ውስጥ ያሉ መንግስታትና አለማቀፍ ተዋንያን ትኩረት መለያየትም አንዱ የሰላም ማስከበር ወይም ማስፈን ስራት ተግዳሮት ነው፡፤ መንግስታት ለግዛታዊ አንድነትና ሉአላዊንት ትኩረት ሲሰጡ አለማቀፍ ተዋንያን ደግሞ በሰባዊ መብትና በተለይም በአናሳ ህዝቦች መብት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ እንደባለሙያዎቹ አስተያየትና ማርቲና ስክዊኮስኪ እንደጻፈችው።፡ ይህ ያእቀራርብና ትኩርት ልዩነት የሰላም ማስፈን ስራን ስኬት ይፈታትነዋል በማለት ለምሳሌም በቅርቡ በዴሞክራቲክ ጎንጎና ሩዋንድ መካከል ሊደረግ የነበረው ድርድር በዚሁ የትኩረት ልዩነት ምክንያት ድርድሩ ሳይጀመር የቆረ ስለመሆኑ ተጠቅሷል።
አመጽና አክራሪነት ሊበራከቱ የሚችሉባቸው ምክኒያቶች
ጸሃፊዋ የደብብ አፍካን የጥናት ተቋም ጥናት ጠቅሳ እንዳሰሰፈረችው ፤ አመጽና አክራሪነት በኢኮኖሚ መገለል፤ በአስቸጋሪ የዴሞክራሲ ሽግግርና በመንግስታት መከላካያቸውን ለማዘመን አለመቻል ምክንያት ሊስፋፋ ይችላል። ሚስተር ጃኪ ሲልየር የዚህ አክራሪና አማጺ ሀይሎች መበራከት የሚያስክትለውን ሲገልጹ “ በእርግጠኝነት ነባሩ የሰላም ማስከበር ዘዴ እየሰራ አይደለም።። የዚህ ሀይል ውጤማ አለመሆንና የአክራሪዎች መስፋፋት በብዙ ቦታዎች የሩሲያ ዋግነር ግሩፖች አይነቶቹን ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች ወደ አህጉሩ እንዲገቡ በር ከፍቷል። አፍሪካ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ፣ አውሮፓና ቻይና መካከል ብቻ ሳይሆን እንደተባበሩት ኤሚሪቶችና ቱርክ የመሳሰሉ አዳዲስ ሀይሎችም መፎካክሪያ መሆኑን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት ለአፍሪካ ችግሮች ቀደሚ መሆን ስለማስፈለጉ
የአፍርካ መንግስታት ለሚሰጡ ማስጠንቀቂያዎች ፈጥነው መልስ አለመስጠታቸውና ጣልቃ በመግባት መፍትሄ ለመስጠት ዳተኛ መሆናቸው ችግሩን ያወሳስበው መሆኑም ተገልጿል። በተጨማሪም ማርቲን ቀድሞ የመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ተወካይ የነበሩትን ሀናህ ቴትህን ጠቅሳ እንዳሰፈረችው፤በአፍሪካ ብዙዎቹ ተቃዋሚ አማጺ ሀይሎች ግልጽ የፖለቲካ አጀንዳ የሌላቸው መሆኑ የድርድርና ሰላም የመፍጠሩን ስራ አስቸጋሪ አድርጎታል። ባጠቃላይም ባለሙያዎቹ እንደገለጹትና ማርቲን በጽሁፏ እንዳሰፈረችው በአህጉሩ ላለው ችግር ያፍርካ ህብረት ቀዳምዊ ደራሽና መፍትሄ አፈላላጊ መሆን ይኖርበታል። የአፍርክ ህብረት ሃላፊነቱን እንዲወጣ ግን እራሱንም ማሻሻል አለበት ነው የተባለው። የአፍሪካ ህብረትና የመንግስታቱ ድርጅት ከአካባቢ ድርጅቶች ጋር ተቀናጅተው ሲሰሩ አይታዩም በማለት ይህም በግንኑነቶቻቸው መካከል ክፍተት የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።
በመንግንስታቱ ድርጅት የሰላም ስምምነቶች መረጃ ከሆነ በዓለም ዙሪያ ከተደረጉ የሰላም ስምምነቶች 42% የሚሆኑት በአፍርካ የተደረጉ ሲሆኑ፤ ከነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ያልስመሩ ወይም በክፊል ብቻ የስመሩ መሆናቸው ተገልጿል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለሙያዎቹ በተለይ በዚህ አሸባሪዎችና አክራሪዎች በተስፋፉበት ዘመን የሰላም አስከባሪ ሀይል ሽብርን ለመታገልና ለማጥፋት አይነተኛ ዘዴ ሊሆን እንደማይችልም ማርቲና ስኩዎስኪ የባለሙያዎችን አስተያየት አክላና ጠቅሳ በጽሁፏ አስፍራለች።
ህገወጥ የነዳጅ ዘይት ንግድ በናይጀሪያ
የናይጀሪይ የጸጥታ ሀይሎች በአገሪቱ በሚካሄደው ህገወጥ የነዳጅ ዘይት ንግድ ላይ ጥብቅ እርምጃ የወሰዱ መሆኑን ሚሚ ሜቶና ኤኬሪ ንጉትያዝ በጻፉትና ለደበብሊው በድረሰው ዘገባ ተገልጿል። በተወሰዱ እርምጃዎችም 56 የማከማቻ ቦታዎች የፈራርሱ መሆኑ ታውቋል።
በአፍርካ ትልቅ የነዳጅ ክምችትን ሀብት ያላት አገር ናይጀሪያ፤ መጥነ ሰፊ የነዳጅ ስርቆትና በነዳጅ መተላለፊያ ቧንቦዎቿ ላይም ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስባት አገር በመሆንም ትታወቃለች። የፖሊስና ወታደራዊ ሀይሎች በቅርቡ ባደረጉት አሰሳና በወሰዷቸው እርምጃዎች ከ1.2 ሚሊዮን ሊትር ያልተጣራ ነጃጅ ዘይት ክምችት፤ አስራምስት ህገወጥ የነዳጅ ማጣሪያዎች በጫካ ተደብቀው ያገኙ መሆኑን አስታውቀዋል። አስራ ሰባት ተጠርጥራዎች የታሰሩ መሆኑንና በርክታ ተሽከርካሪዎችና የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ መሳሪያዎችም የተወረሱ መሆኑም ተገልሷል። ከ2009 እስከ 2020 ድረስ ናይጀሪያ ግምቱ 46 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን 620 ሚሊዮን በርሜል ያልተጣራ ነዳጅ ዘይት በስርቆትና መዝበራ ያጣች መሆኑን ያገገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት አያያዝና ቁጥጥር የሚከታለውን ቢሮ መረጃ ጠቅሰው ጸሀፊዎቹ በመጣጥፋቸው አስፍረዋል።
ለምን ህገወጥ የነዳጅ ዘይት ንግድ ተስፍፋ?
ጸሀፊዎቹ በናይጀሪያ የነዳጅ ዘይት ስርቆት አዲስ አለመሆኑን በመጥቀስምበተለይ የነዳጅ ሀብትባለጸጋው የዴልታ አካባቢ ዋናው የዚህ ወንጀል እምብርት መሆኑን አስታውቀዋል። ሚስተር ኡማሩ አህማዱ የተባሉ የፋይናንስ ባለሙያ እንደገለጹትና ለDW እንደደረሰው አስተያየት ከሆነ፤ መንግስት በተለይ በነዚህ የነዳጅ ሀብት በሚገኝባቸው አካባቢዎች የኢኮኖሚ ፍትህ ካላሰፈነ በስተቀር ስርቆት አይቆምም። “ እነዚህ ህዝቦች ምንም አይነት መሰረተ ልማት የላቸውም፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ድጋፍ አያገኙም። አክባቢያቸው ፍጹም ወድሟል፤ ምንም አይነት መተዳደሪያም የላቸውም”” በማለት በዚህ ሁኔታ ያለ ህዝብ ከመስረቅና ከመዝረፍ ሊቆጠብ አይችልም ብልለዋል።፡የናይጀሪያ መንግስት የህዝቦቹን መሰረተ ልማት በማሟላትና ህዝቡን ከተፈጥሮ ሀብቱ ተጠቃሚ በማድረግ ብቻ ችግሩን ለማስወገድ እንደሚቻል ሚስተር ኡማሩ አክለው አስታውቀዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የናይጀሪያ ባለስልጣናትና ፖለቲከኞችም የነዳጅ ዘይት ስርቆትን ከሚያካሂዱ ወንጀለኞች ጋር የሚተባበሩና ጥቅም የሚካፈሉ በመሆናቸው መንግስት ይህንን ችግርም ማስወገድና የተፍጥሮ ሀብት አስተዳደሩን በብቃት መምራት መቻል ይኖርበታል፤ እንዲሁም ለአካባቢ ጥበቃ ደህንነት ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል በማለትም ጽሀፊዎቹ ለዚህ ሁሉ ግን የፖለቲካ ቁርጠኘት የሚያስፈግ መሆኑን ጠቁመው ጽሁፋቸውን ደምድመዋል።
ገበያው ንጉሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር