1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ሃገራዊ አንድነት ላይ የተካሄደው ውይይት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 23 2016

በዚሁ የበይነ መረብ ጉባኤ ላይ፣በንግድ፣ በፍልሰት፣በከተማዎች መስፋፋት እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ወደ ኢትዮጵያ ፈልሰው በመምጣት በተለያዩ ቀዬዎች በመስፈር፣የነዋሪውን የዘር ሃረግ የተቀላቀሉትና የተቀየጡት ታላላቅ የነገድ ዘርፎች፣ለኢትዮጵያውያን አብሮነትና ለአገር ግንባታ የከፈሉትን ድርሻ የሚዳስስ ውይይት በታዋቂ ምሁራን ተካሂዷል።

የኢትዮጵያዊነት የተሰኘዉ አወያይ መድረክ አርማ
መንበሩን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገዉ ኢትዮጵያዊነት የተሰኘዉ አወያይ መድረክ አርማምስል Tariku Hailu /DW

በኢትዮጵያ ሃገራዊ አንድነት ላይ የተካሄደው ውይይት

This browser does not support the audio element.

 

የኢትዮጵያንn አንድነት የሚያገለብቱ ተከታታይ ትምህርታዊ ጉባኤዎችን ማካሄዱን እንደሚቀጥል መንበሩን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገዉ ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ድርጅት አስታወቀ።የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር እርቁ ይመር ፣በኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴቶች ላይ በተካሄደ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያዊነት ስነልቦና እየተዳከመና እየተመናመነ በመምጣቱ፣ ተከታታይ ትምህርታዊ ዝግጅቶችን ማካሄድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።ኢትዮጵያዊነት የዜጎች ማስከበሪያ ጉባኤ፣" ኢትዮጵያዊነት የአብሮነት እና የጥንካሬ ምሥጢር" በሚል ርዕስ ያካሄደውን ተከታታይ ጉባኤ አጠናቋል።

የተዳከመው የኢትዮጵያዊነት ስነልቦና

በኢትዮጵያዊያን የጋራ እሴቶች ላይ አትኩሮ ሰሞኑን በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ዶክተር እርቁ ባደረጉት ንግግር፣ በግንዛቤ ማነስና በተሳሳተ ትርክት ምክንያት፣የኢትዮጵያዊነት ስሜት እየተዳከመ መምጣቱን ተናግረዋል።"እንደዚህ ዐይነት ዌቢናሮችን የምናዘጋጀው፣ የኢትዮጵያዊነት ስነልቦና እየተዳከመና እየተመናመነ በመምጣቱ፣ያ ደግሞ አሁን ያለንበትን ችግር ይፈጥራል ከሚል ነው።"ሊቀመንበሩ እንዳሉት፣በአሁኑ ወቅት ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ማሳወቅ ስለሚገባ፣ከምሁራን ከፍተኛ ሚና ይጠበቃል።

 

ትምህርታዊ ጉባዔዎች

በድርጅታቸው በኩል፣ የኢትዮጵያን ሃገራዊ አንድነትና መግባባትን ለማጎልበት የሚረዱ ተከታታይ ትምህርት ጉባኤዎችን ለማካሄድ መወጠኑን አመልክተዋል።በዚሁ የበይነ መረብ ጉባኤ ላይ፣በንግድ፣ በፍልሰት፣በከተማዎች መስፋፋት እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ወደ ኢትዮጵያ ፈልሰው በመምጣት በተለያዩ ቀዬዎች በመስፈር፣የነዋሪውን የዘር ሃረግ የተቀላቀሉትና የተቀየጡት ታላላቅ የነገድ ዘርፎች፣ለኢትዮጵያውያን አብሮነትና ለአገር ግንባታ የከፈሉትን ድርሻ የሚዳስስ ውይይት በታዋቂ ምሁራን ተካሂዷል። 

የዜጎች ኃላፊነት

በጎንደር ዩኒቨርስቲ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ባሻ ታአ፣ለኢትዮጵያ አንድነትና ውሕደት እያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅበትን ድርሻ መወጣትእንደሚገባው አሳስበዋል።"አንድነት ውሕደት የመሳሰሉ ጉዳዮች፣ ከሰማይ የሚወርዱ አይደሉም።እያንዳንዱ ዜጋ በተቻለ መጠን የሚፈልግበትን የሚጠበቁበት ኃላፊነት ተወጥቶ፣የሃገሩን ደህንነት መጠበቅና ማሳደግ አለበት።"

 

የኢትዮጵያውያን አንድነት ጉዳይ እጅግ የሚያሳስብ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት ፕሮፌሰር ባሻ፣ አገሪቱ አንድነቷ እንደተከበረና ታላቅነቷ እንደተጠበቀ እንድትቆይ የኢትዮጵያዊነት ድርጅት እያደረገ ላለው ከፍተኛ ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።የኢትዮጵያ አንድነት የመነጨው፣ከዜጎቿ የሥነልቦና ጥንካሬ፣ከሕዝቦቿ  ጀግንነት እንደሆነም አስረድተዋል።

ፕሮፌሰር  ባሻ፣የህዝቦች ፍልሰት በኢትዮጵያ ምን ይመስል እንደነበር፣ለሃገር ግንባታና  ለብሔራዊ መግባባት ያበረከተውን አስተዋጽኦ አስመልክተው ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

"ከፍልሰት ጋር የሚመጣ፣ አሁን እንደምናየው ብዝሃነት ነው።ብዝሃነት ደግሞ ምን ይፈልጋል? አንድነትን ነው።አንድነት ደግሞ አብሮነትን ነው የሚፈልገው። እነዚህ በጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የነገሱ ናቸው።ሕዝቡ በአንድነቱ የሚኮራ የሚተባበር የሚተጋገዝ፣አብሮ የሚኖር ሕዝብ ነው።"

በዚሁ ጉባዔ ላይ፣በኢስት ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትና ተመራማሪነት ሲያገለግሉ ቆይተው አሁን በጡረታ ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ሙላቱ ውብነህ፣የከተማ ልማትና ዕድገት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ውሕደት የነበረውን ድርሻ የተመለከተ ዳሰሳ አቅርበዋል።የስነ ፍጥረት እና የባህል ጥናት ተመራማሪው ዶክተር ዮሐንስ ዘለቀ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያዊያንን የዘር ሐረግ፣ከስነፍጥረት፣ ከሃይማኖት፣ ከታሪክና ከባህል አንጻር የሚፈትሽ ጥናት ለጉባዔተኞቹ አቅርበው ውይይት ተካሄዶበታል።

ታሪኩ ኃይሉ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

 

 

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW