የፕሬስ ነጻነትአፍሪቃ
በኢትዮጵያ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የበረታው ጫና
እሑድ፣ ኅዳር 6 2019
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ በመገናኛ አውታሮች ላይ የሚደርሰው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየበረታ ነው ። ከሰሞኑ እንኳን ሦስት ዐሥርተ ዓመታት ግድም ያስቆጠረው ሪፖርተር ጋዜጣ «ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የሚጻረሩ ይዘቶችን አሠራጭቷል» በሚል በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ መታገዱ ተሰምቷል ።
ከዚያ ቀደም ብሎ በየጊዜው የተለያዩ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ሲታሰሩ ሌሎች ደግሞ ሲዋከቡ ተስተውሏል ። የዶይቸ ቬለ የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ወኪል ጋዜጠኞች ፈቃድ አሁንም ድረስ እንደታገደ ነው ። እነዚህ ለአብነት ያህል የተጠቀሱ ናቸው ።
ኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙኃን ነጻነት መስፈርቶች ከዓለም 180 አገራት መካከል 148 ደረጃ ላይ ቁልቁል እንደምትገኝ እና ኹኔታውም እጅግ አሳሳቢ እንደኾነ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን (RSF) ሚያዝያ 23 ቀን፣ 2018 ዓም ያወጣው ዘገባ ይጠቁማል ።
ለመኾኑ የመገናኛ አውታሮች ላይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጫናው የበረታበት ምክንያቱ ምን ይኾን? የዛሬው ውይይት ዋነኛ ትኩረት ነው ። ሦስት እንግዶች የጋበዝንበትን ሙሉውን ውይይት ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ