በኢትዮጵያ ምርጫ ውስጥ የሴቶችን ጥቅም እና ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ድምጽ ይሰማል?
ቅዳሜ፣ ግንቦት 22 2018
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከቀን ወደ ቀን እየተቃረበ ሰአታት ብቻ ቀርተውታል። ከተሞች በፖስተሮች እና በተለያዩ የዲጂታል ስክሪኖች አሸብርቀው ሰንብታዋል ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን እዚም እዛ አድርገውየጥሞና ግዜያቸው ላይ ደርሰዋል አርምሞ ላይ ናቸው ።
ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ግርግር በስተጀርባ፣ በዝምታ የምትታዘብበልቧ ብዙ ጥያቄዎችን የያዘች ግማሽ የሀገሪቱ አካል አለች በልዩ መነጽር በእሷ አይን እየቃኘች። የሀገሪቱን ቀጣይ አቅጣጫ ለመወሰን በደጃፋችን ለይ በሚገኘው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ወቅት ሴቶች በምርጫው መሳተፍ ያለባቸውብዙ ምክንያቶች አሉ። በዘንድሮው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከተመዘገበው ጠቅላላ መራጭ ውስጥ የሴቶች ቁጥርታሪካዊ የተባለለትን ቁጥር ተመዝግቦዋል ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡት መካከል ባርካታ ሴቶች የምርጫ ካርድ ወስደዋል። በተለይ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ባሉ የኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች የሴት መራጮች ምዝገባ ቁጥርይበልጥ ንቁና ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተነግሮዋል ዛሪ ይህ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በልዩ መነጽር፣ በእሷ ዓይን እናየዋልን። የሴቶች የምርጫ ካርድ የፖለቲካ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን፣ በቀጥታ ከዕለት ተዕለት ህይወታቸው ጋር የተያያዘነው።
የዕለት ተዕለት የኢኮኖሚው ውላፈን የሚገርፋቸው በመሆኑ ፣ የዋጋ ንረት በቀጥታ የሚያርፈው በእነሱ ትከሻ ላይ ነው። ድምፅ የሚሰጡት የኑሮ ውድነትን የሚያቃልል፣ እና የገበያ መረጋጋትን እንዲመጣ ከመሻጣቸው በተጨማሪ በሀገሪቱበተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችና የጸጥታ መደፍረሶች ቀዳሚ ተጎጂዎች እናቶችና ሴቶች ናቸው።
የወሊድ ጤናአገልግሎት፣ የሕፃናት ክትባት፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ እና የትምህርት አቅርቦት ጉዳዮች ከሴቶች ህይወት ጋር በቀጥታየተቆራኙ ናቸው።ሁለተኛውና ትልቁ ጥያቄ ደግሞ ለእርስዋ ጤና እና አካላዊ ደህንነት ነው አንዲት እናት ልጇን ወልዳበሰላም የምታሳድግበት ፣ እስዋም ሆነች ልጆችዋ ያለ ስጋት በሰላም ወጥተው የሚገቡበት ሰላማዊ ጎዳና ያስፈልገናልይላሉ ። ይህ ለሴቶች የቅንጦት ጥያቄ አይደለም፤ የህልውና እና የህይወት ጉዳይ እንጂ
ምንም እንኳን ድምፀ ለመስጠት የተመዘገቡትሴቶች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ባለው የኑሮ ፈተናምክንያት "ድምፅ ብሰጥም ለውጥ አይመጣም" በሚል የተስፋ መቁረጥ ስሜት ዝምታን በመምረጥ፣ በምርጫው ዕለትድምፅ ለመስጠት ላይወጡ የሚችሉ ሴቶች ቁጥር ትንሽ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት
ሐና ደምሴ
እሸቴ በቀለ