1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

በኢትዮጵያ ባለው ቀውስና በአሜሪካ አማራጭ ፖሊሲዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

ዓርብ፣ ሰኔ 28 2016

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም እርምጃው እንዲወስድ ጥሪ ቀረበ። የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ማኀበራት ምክር ቤት አባላት ይህን ጥያቄ ያቀረቡት፣፣ከዩናይትድ ስቴትስ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት/ሴኔት/ አባላት ጋር፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

USA I Blick nach New York
ምስል Lokman Vural Elibol/AA/picture alliance / AA

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም እርምጃው እንዲወስድ ጥሪ ቀረበ

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ ባለው ቀውስና በአሜሪካ አማራጭ ፖሊሲዎች ላይ የተካኼደ ውይይት

 

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም እርምጃው እንዲወስድ ጥሪ ቀረበ።

የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ማኀበራት ምክር ቤት አባላት ይህን ጥያቄ ያቀረቡት፣፣ከዩናይትድ ስቴትስ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት/ሴኔት/ አባላት ጋር፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ውይይት  ላይ ነው።

ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ፣በአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት/ሴኔት/፣ሰሞኑን በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ላይ በተካሄደው በዚሁ ውይይት ላይ፣ በአሜሪካ የሚገኙ ሰባት የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ማኀበራት መሳተፋቸው ተገልጿል።

በአሜሪካ ወገን ደግሞ፣ስድስት የህግ መወሰኛ  ምክር ቤት አባላት መሳተፋቸውን፣በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ማኀበራት ምክር ቤት ሊቀመንበር አቶ መስፍን መኮንን ለዶይቸ ቨለ አስታውቀዋል።

«የኢትዮጵያውያን አንድነት ለኢትዮጵያ ሰላምና ዕድገት ድርጅት» የሰላም ጥረት

ጦርነት የማስቆም ጥሪ

በዚሁ ውይይት፣ በኢትዮጵያ ስላለው ቀውስ እና ስለ አሜሪካ የፖሊሲ አማራጮች ገለፃ መደረጉን አቶ መስፍን ተናግረዋል።

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ መቅረቡን የገለጹት ሊቀመንበሩ፣ ማዕቀቦችንና ሕገ መንግስታዊ ማሻሻያ ላይ ያተኮረ ስትራቴጂ እንዲከተል ዐሳብ መቅረቡንም ጠቁመዋል።

የሲቪክ ማኀበራቱ ቀጣይ ተግባራት

አቶ መስፍን፣  ቀጣይ እንቅስቃሴያቸውን በተመለከተ እንደሚከተለው አስረድተዋል።

"ሴናተሮቹ  አሁን እነሱ እጅ ላይ ነው ያለው። የሚቀጥለው እርምጃችን ምንድን ነው  የንዑስ ክፍሉን  ማነጋገር ነው። ከእዛ የሴኔቱ የውጭ ግንኙነት የሚሪላንድ ሴናተር ካርዲን ይባላሉ።ብዙ ዓመት ከእርሳቸው ጋር ግንኙነት አለን።በእርሳቸው ግፊት አንድ ዐይነት ውጤት እንዲያመጣ እየሰራን ነው።"ከእዛ ሌላ ደግሞ በምክር ቤቱ ኮንግረስማን ክሪስ የሚባሉ፣ በእርሳቸውም በኩል አንዳንድ ትልልቅ ስራ እየተሰራ ነው።"

ሊቀመንበሩ እንደሚሉት፣ከአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት ጋር  በተካሄደው ውይይት፣የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የቀጠለውን ግጭት ችላ ስለማለቱ፣እንዲሁም ተጨማሪ አለመረጋጋትን ማስወገድ ሲቻል እርምጃ አለመውሰዱ ስህተት መሆኑ ተነስቷል።

የአሜሪካን ኢትዮጵያውያን ሕዝብ ጉዳይ ኮሚቴ(ኤፓክ) ጥሪ

"አንድ ጥያቄ ያቀረቡት ምንድነው?' የዩኤስ መንግስት እስካሁን ምን አድርጓል? እስካሁን ድረስ ምን ሰማችኹ? የተደረገ ዝግጅት አለ?' የሚል ጥያቄ ነው ያቀረቡት፤ በጣም ትልቅ ጥያቄ ነው። እኛ ግን ምንድነው ያልነው በዩክሬን እና በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ጦርነት ብዙ ተይዞ ትኩረት የተደረገው በእዛ ላይ ነው።ግን ዋናው ነገር እኛ ያልናቸው፣ይህንን ዝም ብሎ እንዳላዩ ማለፍ ትልቅ ትልቅ ስህተት ነው። ወደፊት የዩኤስ መንግስትን የሚያስጠይቅ ነው።እንደዚህ ሰው ሲገደል ሲጨፈጨፍ፣ ከየሚኖርበት ቦታ ሲፈናቀል፣ ይህ በብዙ ዓመት በላይ የመጣ ነገር ነው።"

በውይይቱ ላይ የተገኙት ሌላኛዋ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ምክር ቤት አባል ወይዘሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታ በበኩላቸው፣የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ ለአሜሪካ እንደራሴዎች በሚገባ ማስረዳት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

"የእኛን እኛ ነን፣ ማለት ኢትዮጵያውያን በየቦታው ያለን ይህንን ድምጽ መሆን ያለብን፤እኛ ገልጸን አስረድተን ጨርሰናል ወይ?እኛው ላይ ነው ችግሩ ያለው አሁንም እና ስለዚህ በተቻለ መጠን በየኮንግረስ አባላቱ በየሴናተሩ እየሄድን ማስረዳት አለብን አሁንም።"

ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

ሁሉን አቀፍ ውይይትና እርቅ

በኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት እልባት እንዲያገኝ ዩናይትድስቴትስ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደምትችል በተገለጸበት በዚሁ ዉይይት፣ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣አስቸኳይና ሁሉን አቀፍ ውይይትና እርቅ ያስፈልጋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ማኀበራት ምክር ቤት አባልና የግሎባል ዐማራ ጥምረት የዲፕሎማቲክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ጽጌረዳ፣ በሴኔቱ የተደረገው ውይይት ቀጣይ ሁታዎች በተመለከተ የሚከተለውን ተናግረዋል።

"ይህ በአውሮፓም ነው በዚህም ነው፣ በቅንጅት የሚሰራ ስራ ነው።

በቀጣይነት የሴኔት ውይይት ሊኖር ይችላል።ከእዛም በላይ ንዑስ ኮሚቴዎችን የምናነጋገርበት እና በተለይ በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች የምንሰራው ከፍተኛ ሥራ ይኖረናል።እና የዲፕሎማሲው ስራ አንድ ላይ መቀናጀት አለበት።

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በተካሄደው ውይይት ዙሪያ፣ ዋሺንግተን ዲሲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተያየት ለማግኘት ጥረት ብናደርግም፣ምላሽ አላገኘንም።

ታሪኩ ኃይሉ

ታምራት ዲንሳ 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW