1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ መልሶ በረራ መጀመር እና የፈጠረው መረጋጋት

ማክሰኞ፣ ጥር 26 2018

ከአምስት ቀናት ገደማ የበረረራ መቋረጥ በኋላ ዛሬ ጠዋት ብቻ ሁለት በረራዎች ከአዲስ አበባ መቀሌ እና ከመቀሌ አዲስ አበባ መደረጉን የአይን እማኞች እና የበረራው ተጠቃሚዎች ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል፡፡

በኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ ትግራይ መልሶ በረራ መጀመር የተፈጠረው መረጋጋት
በኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ ትግራይ መልሶ በረራ መጀመር የተፈጠረው መረጋጋትምስል፦ Seyoum Mekonnen/DW

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ መልሶ በረራ መጀመር እና የፈጠረው መረጋጋት

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ላለፉት አምስት ቀናት ግድም አቁሞት የነበረውን ወደ ትግራይ ክልል የሚያደርገውን በረራ ዛሬ መልሶ መጀመሩን መንገደኞች ተናገሩ፡፡

ከአምስት ቀናት ገደማ የበረረራ መቋረጥ በኋላ ዛሬ ጠዋት ብቻ ሁለት በረራዎች ከአዲስ አበባ መቀሌ እና ከመቀሌ አዲስ አበባ መደረጉን  የአይን እማኞች እና የበረራው ተጠቃሚዎች ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል፡፡

በአየር መንገዱ በረራ መጀመርም ከሰሞኑ ተስተውሎ የነበረው ውጥረት መርገቡንና በነዋሪዎች ዘንድ አሁን መረጋጋት መፈጠሩንም መንገደኞቹ እና ነዋሪዎች በአስተያየታቸው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግን ስለበረራው መቋረጥም ሆነ አሁን መልሶ መጀመር ያለው ነገር አልተሰማም፡፡

የበረራው መልሶ መጀመር

ለቤተሰብ ጥየቃ ከሚኖሩበት አዲስ አበባ ከተማ ወደ መቀሌ ማምራታቸውን ገለጸው አስተያየታቸውን ባለፈው ዓርብ ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ማህሌት የተባሉ መንገደኛ፤ የደርሶ መልስ ትኬት በቆረጡት መሰረት ትናንት ሰኞ በኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ ቤተሰቦቻቸው አዲስ አበባ የመመለስ እቅድ የነበራቸው ቢሆንም ባለፉት አምስት ቀናትየአየር በረራው መቋረጡን ተከትሎ መጨነቃቸውን ገልጸውልን ነበር፡፡ “ትኬቱን ከቆረጥኩ ሁለት ሳምንት ሆኖኛል፡፡ የደርሶ-መልስ ትኬት ቆርጬ ነው ወደ መቀሌ የመጣሁት” ያሉን አስተያየት ሰጪዋ መንገደኛ የየብስ ትራንስፖርት አማራጭም ስመለከቱ ቆይተው እንደዋዛ ግን የማይገኝ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ዛሬ ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጦት የነበረውን የመቀለ በረራውን መልሶ በመጀመሩ ለነገ የአየር በረራው ትኬታቸውን ማሰናዳታቸውን የገለጹት መንገደኛዋ አስተያየት ሰጪ እንደ አከባቢው ማህበረሰብም አሁን ላይ እፎይታ መገኘቱን ነው ያስረዱት፡፡ “ዛሬ የእኔ ዘመድ ከዚህ ተነስታ በበረራው አዲስ አበባ ገብታለች” ያሉን አስተያየት ሰጪያችን “ትናንት የየብስ ትራንስፖርት በመፈለግ” ብዙ ጊዜያቸውን ብያጠፉም አየርመንገዱ በረራ ጀምሯል መባሉን መስማታቸውን ተከትሎ ለነገ በረራ በአየር መንገዱ ኦፕሬተሮች የበረራ ተራ እንደተያዘላቸው ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት ከመቀሌ በ3፡30 በረራው ከመቀሌ ተነስተው በኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን የገለጹት ሌላኛዋም አስተያየት ሰጪ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በረራው መጀመሩን አረጋግጠውልናል፡፡ “አዎ በረራው ተጀምሯል በ3፡30 በረራ ተነስቼ 5፡00 አከባቢ አዲስ አበባ ገብቻለሁ” የሚሉት መንገደኛዋ አስቀድሞም ጠዋት ላይ ሌላም በረራ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በረራው መጀመሩን አረጋግጠውልናል፡፡ “አዎ በረራው ተጀምሯል ምስል፦ Seyoum Mekonnen/DW

 የበረራው መጀመር የፈጠረው እፎይታ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አከባቢው በረራ ሊጀምር ነው የመባሉ ጭምጭምታ ከተሰማበት ትናንት ማታ ጀምሮ ዛሬ ደግሞ በገቢራዊነት በረራው ጠዋት መጀመሩን ተከትሎ በማህበረሰቡ ዘንድ እፎይታን ፈጥሯል የሚሉት አሁን መቀሌ የሚገኙት አስተያየት ሰጪ በህዝቡም ዘንድ መረጋጋት ታይቷል ሲሉ ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡ “አሁን የታዘብኩት ሰው አእምሮ ትንሽ እፎይ ማለቱን ነው” ያሉን ማህሌ የተባሉ አስተያየት ሰጪ፤ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከነበረው አንጻር አሁን ላይ በብዙ ዘርፍ ህዝቡ ዘንድም ሆነ ገቢያው ላይ መጠነኛ መረጋጋት ታይቷል ነው ያሉን፡፡ የበረራው መቋረጥ የበርካቶችን እቅድ ያፈረሰና ብዙዎችን ያስጨነቀም ነበር በማለት አሁን ግን የበረራውን መጀመር ተከትሎ መንገደኞችም ሆኑ መደበኛ የአከባቢው ነዋሪዎች ዘንድ እፎይታ ታይቷልም ብለዋል፡፡

ዮናስ የተባሉ  ሌላው አስተያየት ሰጪ የመቀሌ ነዋሪ ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ አሁን ላይ ያለው ሁኔታ ሰው ላይ መረጋጋት የሚታይበት ነው በማለት ይህም በዋናነት በአየር ትራንስፖርት መጀመር መረጋገጡ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ “አሁን ሰው ተረጋግተዋል፤ ነገሮች ላይ ተስፋ ታይተዋል” ያሉን አስተያየት ሰጪ ከሰሞኑ በትራንስፖርት፣ በንግዱ እና ባንኮች አከባቢ ታይቶ የነበረው መዋከብ መጠነኛ ያሉት መረጋጋት እየተስተዋለባቸው እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

ከሰሞኑ ትግራይ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች ላይ በተለያዩ ግንባሮች ውጊያ መከፈቱን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተፋላሚዎች ግጭቱን በማቆም ወደ ሰላማዊ ንግግድ እንዲመለሱ ጠይቀው ነበር፡፡

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርም በተለይም በምዕራባዊ ትግራይ አከባቢ ተከፍቶ የነበረውን ጦር በማውጣት ለሰላም ጊዜ መስጠት ማስፈለጉን እንደሚያምንበት ፍንጭ የሰጠ መግለጫ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW