1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የቀጠለው ውዝግብ

ሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2016

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ምንም አይነት የጦርነት እና የግጭት ፍላጎት የላትም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። "ፍላጎታችን ሰላም እና ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስም ያልጠቀሱት አካል "ኢትዮጵያን ለመድፈር ሲፈልግ አንዴ ሳይሆን ሥር ጊዜ ማሰብ ይኖርበታል" ብለዋል።

ፎቶ ማህደር፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ፎቶ ማህደር፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ምስል Fana Broadcasting Corporate S.C.

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የቀጠለው ውዝግብ

This browser does not support the audio element.

የቀጠለው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውዝግብ

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ምንም አይነት የጦርነት እና የግጭት ፍላጎት የላትም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

"ፍላጎታችን ሰላም እና ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስም ያልጠቀሱት አካል "ኢትዮጵያን ለመድፈር ሲፈልግ አንዴ ሳይሆን ሥር ጊዜ ማሰብ ይኖርበታል" ብለዋል።
 

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለዶቼ ቬለ ማብራሪያ የሰጡ ሁለት የፖለቲካ ተንታኞች ቀጣናው ላይ ጦርነት ሊያስነሳ የሚችል ነገር እንደሌለ ገልፀው፣ በሀገራቱ መሪዎች መካከል የጦርነት ድባብ ያለ የሚያስመስል የቃላት ልውውጥ የበዛው የሀገር ውስጥ ችግሮች ሲበዙ ጫናውን ውጫው የማድረግ የተለመደ ስልት ስላለ ነው ብለዋል። 
 

በኢትዮጵያ እና በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ መካከልየተፈጠረው ወቅታዊ የግንኙነት መሻከር የየሀገራቱ መሪዎች ስለ ሀገራቸው ሉዓላዊነት፣ ራስን ስለመከላከል እና ብሔራዊ ጥቅም በብዙ እንዲናገሩ አድርጓቸዋል። የኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ "ግብፅሞቃዲሾ ስለመጣ ወደ ኢትዮጵያ ወረራ ይፈፅማል ብሎ የሚያስብ ካለ ሞኝ ነው" ሲሉ ሰሞኑን ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደግሞ ኢትዮጵያ የጦርነትም ሆነ የግጭት ፍላጎት እንደሌላት ትናንት ተናግረዋል።

 

የፖለቲካ ተንታኞች አስተያየት

ኢትዮጵያ ከራስ ገዝ ሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው የባሕር በር ማግኛ የመግባቢያ ስምምነት ክፉኛ ያስቆጣት ሶማሊያ ከግብጽ ጋር የጀመረችው ግንኙነት ውጥረቱን ቢጨምረውም በቀጣናው ጦርነት ሊቀሰቅስ የሚችል እንዳልሆነ ግን አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የዓለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ተንታኝ ያብራራሉ።

"ጦርነትን ለማካሄድ የሚያስችለ መሠረታዊ ነገሮች አልተሟሉም" በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ዶክተር ሙዐዝ ግደይ እንደሚሉት ግን ጉዳዩ በተቃራኒው ሊሆን ይችላል። "ኢትዮጵያ በዚህ መልኩ [ከሶማሊላንድ ጋር የፈረመችውን የመግባቢያ ስምምነቱን ማስቀጠል ላይ ከፀናች] እገፋበታለሁ ካለች ወደ ወታደራዊ ግጭት ሊሄድ ይችላል"።
 

አንካራ፤ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አል ሲሲ እና የቱርኩ ፕሬዚዳንት ታይብ ኤርዶጋንምስል Murad Sezer/REUTERS

ሰሞኑን የጦር መሣሪያ የጫኑ ሁለት የግብጽ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሞቅዲሾ መድረሳቸው፣ በቀጣይ በሶማሊያ ከሚሰማራው ጥምር ሰላም አስከባሪ ኃይል ጋር ተያይዞ የሚታዩ ውዝግቦች፣ ከኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መሪዎች እያደጉ የመጡ ጠንካራ ንግግሮች ጋር ተደማምረው በዚህ ቀጣና ጦርነት የሚቀሰቅስ ድባብ ያለ አስመስሎታል።  የፖለቲካ ተንታኙ ግን በዚህ አይስማሙም።

"ሀገር ውስጥ ያልተመቹ ሁኔታዎች በሚኖሩበት ጊዜ ያንን ወደ አንድነት ለማምጣት የሚቀረጽ ስልት ነው"  

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን እያሸማገለች የምትገኘው ቱርክ በአንካራ ያደረገችው ሁለት ዙር የውይይት መድረክ ውጤት አልባ በመሆኑ ለሦስተኛ ዙር ንግግር ለመስከረም 7 ቀጠሮ መያዟ ይታወቃል።

 

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW