1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሔደ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 24 2011

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት ዘላቂነት በህግ የታገዘና የስምምነታቸው ጭብጥም ግልጽ ሊደረግ ካልቻለ ስጋት የሚደቅን ነው ተባለ። ትስስራቸው ቀጣናውን ወደ ሰላምና መረጋጋት እንዲመራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውም እንዲያድግ ከዚህ በፊት በነበረው ጦርነት ለተፈጸሙ ህግን የጣሱ ችግሮች የካሳ ጥያቄ ኮሚሽኑ ተግባራት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበሩም ተጠይቋል።

Saudi Arabien Äthiopien und Eritrea schließen Freundschaftsvertrag
ምስል picture-alliance/AP Photo/SPA

ውይይቱን ያዘጋጀው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት ዘላቂነት በህግ የታገዘና የስምምነታቸው ጭብጥም ግልጽ ሊደረግ ካልቻለ ስጋት የሚደቅን ነው ተባለ። የሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻሻሉን ተከትሎ ትስስራቸው ቀጣናውን ወደ ሰላምና መረጋጋት እንዲመራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውም እንዲያድግ ከዚህ በፊት በነበረው ጦርነት ለተፈጸሙ ህግን የጣሱ ችግሮች የካሳ ጥያቄ ኮሚሽኑ ተግባራት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበሩም ተጠይቋል።

ግንኙነቱ መታደስ ከጀመረ ወዲህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ እንቅስቃሶ ኤርትራ ተጠቃሚ እንደሆነችና ከስጋት ነጻ የሆነች ኢትዮጵያን ለፍጠር ህጋዊ ቅቡልነት ያለው መንግስት መትከል እንደሚገባም ሁለቱን ሃገራት በተመለከተና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የውይይት መርሃ ግብር ላይ ተመላክቷል።

የሁለቱ ሃገራት የወደብ አጠቃቀምም እንደገና ሊጤን የሚገባውና ግንኙነታቸው የቀጣናውን ፖለቲካ የውጭ ተጽእኖ ለመመከት በሚያስችል ሁኔታ መምራት የሚያስችል ግልጽ የፖሊሲ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይገባልም ተብሏል። በውይይቱ የኤርትራ ስደተኞች ጉዳይም ለሃሳብ ልውውጥ የቀረበ ነበር።

ሰለሞን ሙጬ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW