በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የዉጭ ጉዳይ ሚ/ር መግለጫ
ዓርብ፣ ኅዳር 11 2013ማስታወቂያ
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል እያከናወነችው ላለው ሕግ የማስከበር ተግባር ለጎረቤት ሀገራቱ ጥሩ ግንዛቤ የተፈጠረበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ሀገራቱ ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን፣ ጣልቃ እንደማይገቡና ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ምሰሶ መሆኗን ያረጋገጡበት ነበር ብሏል። በሱዳን በኩል ሸሽተው የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስም ሱዳን ትብብር እንደምታደርግ ማሳወቋም በመግለጫው ተነግራል። የግብፅና የሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድን በተመለከተም የሁለቱ ሀገራት ልምምድ በኢትዮጵያ ኪሳራ እንደማይሆን ኢትዮጵያ እንደምታምንና ሱዳንም ደቡብ ሱዳንም ይህንን እንደሚያራምዱ ለኢትዮጵያ ማረጋገጣቸው በመግለጫው ተገልጿል።
ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ