1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውሮፓ ቻምበር ጥያቄ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 3 2016

ግልፅነትን፣ ፍትሓዊነትን እና ቀልጣፋ የመሬት አስተዳደርን በማስፈን ኢንቨስትመንትን እና የኢኮኖሚ ልማትን የሚያበረታታ ግልፅና ወጥነት ያለው ፖሊሲ መዘርጋት እንዱ ለመንግሥት ከቀረቡ ሀሳቦች መካከል ነው።

ቻምበሩ ካቀረባቸዉ ሐሳቦች ባለሐብቶች መሬት የሚያገኙበትን ሐሳብ የሚጠቁመዉ ይገኝበታል
የአዉሮጳ ቻምበር ለኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበዉ የመርሕ አማራጭ ይዘት ይፋ ሲሆንምስል Solomon Muche/DW

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውሮፓ ቻምበር ጥያቄ

This browser does not support the audio element.

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት የንግድ ማህበር በኢትዮጵያ ( የአውሮፓ ቻምበር ) በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በአበባ ልማት እና ሌሎች የግብርና ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የሚሠሩ የአውሮፓ ባለሃብቶች በሚያፈሱትመዋዕለ ንዋይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በሀገሪቱ ለኢንቨስትመንት መሬት ከማግኘት ጋር በተያያዘ በግሉ ዘርፍ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት ለዘርፉ የተመቻቸ ሁናቴ መፍጠር እና የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ ዛሬ ይፋ ያደረገው ሰነድ ዋና ዓላማ መሆኑን አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ቻምበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ባሕሩ ተመስገን በ 2005 ዓ.ም ወጥቶ የነበረው ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሬት የሚወሰድበት ዐዋጅ ከ 2011 ወዲህ በሌላ ዐዋጅ መተካቱ ችግር ማስከተሉን ገልፀዋል።ግልፅነትን፣ ፍትሓዊነትን እና ቀልጣፋ የመሬት አስተዳደርን በማስፈን ኢንቨስትመንትን እና የኢኮኖሚ ልማትን የሚያበረታታ ግልፅና ወጥነት ያለው ፖሊሲ መዘርጋት እንዱ  ለመንግሥት ከቀረቡ ሀሳቦች መካከል ነው። "መሬትን በተመለከተ የፌዴራልና የክልል መንግስታት ቅንጅቶችን ማጎልበት፣ የፀረ-ሙስና ርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ እና ግልጽነት ያለው የመሬት መዝገብ ማዘጋጀት፣ የካሳ ክፍያን ለማስላት መመሪያዎችን መፍጠር" ማሻሻያ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች ናቸው።

የአዉሮጳ ቻምበር በኢትዮጵያ-አርማ ምስል Solomon Muche/DW

 

የፀጥታ ችግር የፈጠረው አደጋ

የገጠር መሬት አጠቃቀም ዐዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት እየተደረገበት ነው። ይህ ዐዋጅባለሃብቶችየበለጠ ልማት የሚያከናውኑበትን መሬት የማግኘት ዕድል ይፈጥርላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ይሁንና የፀጥታ ችግር የዘርፉ ፈተና መሆኑ ተገልጿል።አብዛኞቹ ችግሮች ትክክል መሆናቸውን የገለፁት በግብርና ሚኒስቴር የመሬት ሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ አበባው አበበ ካሳን በተመለከተ በባለሃብቶች የሚቀርበው ክስ ግን ተገቢ አይደለም ብለዋል።

የኢትዮጵያኢንቨስትመንት ኮሚሽን መሬትን በተመለከተ ያለው ችግር ቀላል አለመሆኑን ያምናል። የድህረ ኢንቨስትመንት እንክብካቤ ማድረግ የኮሚሽኑ የቀጣይ ሥራ መሆኑን ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የተቋሙ የሥራ ኃላፊ ገልፀዋል።የአውሮፓ ኢንቨስትመንት የንግድ ማህበር ( የአውሮፓ ቻምበር ) ኢትዮጵያ ውስጥ በልዩ ልዩ የልማት ዘርፎች የተሰማሩ 180 አባላት ያሉት ተቋም ነው።

ሰሎሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሔር 

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW