1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ታሪክአፍሪቃ

በኢትዮጵያ የታሪክ ትርክት ላይ ያተኮረው የውይይት መድረክ

ዓርብ፣ መጋቢት 29 2015

የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማሰባሰብ በኢትዮጵያ የታሪክ ትርክት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ

Äthiopien Addis Abeba | Ethiopian Civil Society Organization for Election (CECOE)
ምስል Hanna Demisie/DW

በኢትዮጵያ የታሪክ ትርክት ላይ ውይይት ተካሄደ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማሰባሰብ በኢትዮጵያ የታሪክ ትርክት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ። እስካሁን ባለው የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያሉ አተያዮች ላይ ትኩረቱን ባደረገው የውይይት መድረክ ፣ ኢዚማ ፣ አብን፣ኦነግ፣ ኦፊኮ፣ የሲዳማ ህዝብ  እና ሌሎችም የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥት ተቋማት፣ የሲቪክ ማሕበራት እንዲሁም ምሁራን ተሳትፈዋል።

በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ከ 175 በላይ ሀገር በቀል የሲቪክ ማሕበራትን አቅፎ የያዘው ነው የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ። በመድረኩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ፣ የታሪክ መጽሐፍ ሀያሲ እና «የድንቁርና ጌቶች» የተሰኘው መጽሐፍ ጸሐፊ በሆኑት በአቶ ብርሀኑ ደቦጭ አማካኝነት አከራካሪ ነው በተባለው በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የተጻፉ አተያዮችን በተለያየ ክፍል በማስቀመጥ በዝርዝር ቀርበዋል። የሀገር ታሪክ ፣ የመንግሥት ታሪክ፣ የብሔር ታሪክ የጎሳ/ዘር  ታሪክ ሁሉም የራሱ ታሪክ ይኖረዋል ያሉት አቶ ብርሀኑ፤ ብሔራዊ ታሪክ ማለት እነኚህ ሁሉ በጋራ የሚቀመጡበት መሆኑን አስረድተዋል። እንዲህ አይነቱ ሥራ ብዙ ነገር እንደሚፈልግ፤ በተጨማሪም ጊዜ ፣ እውቀት፣ ልምምድ፣ ንግግር እና  የሀሳብ ልውውጥም ይፈልጋል ብለዋል። በመድረኩ የተሳተፉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያሉትን አተያዮች በተለያየ ክፍል በማስቀመጥ ለታዳሚዎቹ በቀረበበት የውይይት መድረክ «’በኢትዮጵያ ታሪክ ብቻውን ተለይቶ የሚወጣ ብሔር የለም፤ ግራም ነፈሰ ቀኝ ይህችን ሀገር ለመሥራት ሁሉም ድርሻውን አበርክቷል፤ እሱ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ደም ጭምር ተዋጥቶባታል» ተብሎዋል።

አንድም «ሀገር በየቦታው በደም እየታጠበ ስለታሪክ የምናውራበት ጊዚ በርግጥ አሁን ነው ወይ?» « የተጠራንበት እና አሁን የምንነጋገርበት ጉዳይ ለየቅል ነው» የሚል እና «የተነሳው ጉዳይ ትልቅ ሆኖ ሳለ በግማሽ ቀን መውሰኑ አግባባ አይደለም» በሚሉ የታዳሚዎች ጥያቄም አስተያየትም የቀረበበት የግማሽ ቀን ውይይት  ታዳሚዎች በጋራ የተስማሙበት ጉዳይ ቢኖር እንዲህ አይነቱ መድረክ በሚመለከታቸው አካለት እየተዘጋጀ ቢቀርብ እና ይመለከተኛል የሚል ወገን ሁሉ ቢሳተፍበት ለችግራችን መፍትሄ ያመጣል የሚል ነው።

የመርሃ ግብሩ አወያይ የሕግ ባለሙያው አቶ ደበበ ኃይለ ማሪያም ታዳሚዎች በታሪካዊ ዳራ ላይ ለመወያየት ላሳዩት ፍላጎት እሚያበረታታ እንደሆነ እና ወደፊት ለሚዘጋጁት ተከታታይ እና ተመሳሳይ መድረኮች እንደመነሻ  እንደሚሆን ተናግረዋል።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW