በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ፍላጎትና አቅርቦት
እሑድ፣ ኅዳር 1 2006ማስታወቂያ
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ የዉሃ ሀብትን ለኤሌክትሪክ ማመንጫነት ለማዋል በየቦታዉ ከተጀመሩት እንቅስቃሴዎች ባሻገር፤ የንፋስ እና ፀሐይ ኃይል እንዲሁም የከርሰ ምድር እንፋሎትን ለኤሌክትሪክ ምንጭነት ሥራ ላይ ማዋል መጀመሩ ሀገሪቱ በዘርፉ በቂ አቅርቦት እንዲኖራት እንደሚያስችል ይታመናል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንም የአቅርቦት እጥረት የለም ባይ ሲሆን ፤ ለጎረቤት ሀገር ማለትም ለጅቡቲ ሽያጭ መጀመሩ ተገልጿል። ድርጅቱ እንደሚለዉ የሚሸጠዉ ከሀገር ዉስጥ ፍጆታ ሲተርፍ ብቻ ነዉ። በተቃራኒዉ የሀገር ዉስጥ ደንበኞቹ ኤሌክትሪክ እንደሚቆራረጥ፤ ዋና ከተማ አዲስ አበባን ጨምሮ፤ ሰዓታት ቀርተዉ ለቀናትም እንደሚጠፋባቸዉ ይናገራሉ። አቅም እያለ ለምን ይቋረጣል? ዶይቼ ቬለ ባለሙያዎችን ጋብዞ ያወያየበት ርዕሰ ጉዳይ ነዉ። ዝርዝሩን ከድምፁ መረጃ ያድምጡ!
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ